ትንቢተ ኢሳይያስ 25

AMHNIVአማርኛ12 ጥቅሶች2:37 አዳምጥ
አዳምጥ 2:37 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፣ ድንቅ ነገር፣ በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና።

2ከተማዪቱን የድንጋይ ክምር አድርገሃታል፤ የተመሸገችውንም ከተማ አፈራርሰሃታል፤ የተመሸገችው የባዕድ ከተማ ከእንግዲህ አትኖርም፤ ተመልሳም አትሠራም።

3ስለዚህ ብርቱ ሕዝቦች ያከብሩሃል፤ የጨካኝ አሕዛብ ከተሞችም ይፈሩሃል።

4ለድኻ መጠጊያ፣ በጭንቅ ጊዜ ለችግረኛ መጠለያ፣ ከማዕበል መሸሸጊያ፣ ከፀሓይ ትኵሳትም ጥላ ሆነሃል። የጨካኞች እስትንፋስ፣ ከግድግዳ ጋር እንደሚላጋ ማዕበል ነውና፤

5እንደ ምድረ በዳም ትኵሳት ነው። የባዕድን ጩኸት እረጭ ታደርጋለህ፤ ትኵሳት በደመና ጥላ እንደሚበርድ፣ የጨካኞችም ዝማሬም እንዲሁ ጸጥ ይላል።

6የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ፣ ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ የምግብ ግብዣ፣ የበሰለ የወይን ጠጅ ድግስ፣ ማለፊያ ጮማና ምርጥ የወይን ጠጅ ያዘጋጃል።

7በዚህም ተራራ ላይ፣ በሕዝብ ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣ በመንግሥታት ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል፤

8ሞትንም ለዘላለም ይውጣል። ጌታ እግዚአብሔር ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፤ የሕዝቡንም ውርደት ከምድር ሁሉ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።

9በዚያን ቀን እንዲህ ይባላል፤ “እነሆ፤ አምላካችን ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን፤ እርሱም አዳነን፤ እግዚአብሔር ይህ ነው፤ በእርሱ ታመንን፤ በማዳኑም ደስ ይበለን፤ ሐሤትም እናድርግ።”

10የእግዚአብሔር እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋል፤ ነገር ግን ጭድ ከጭቃ ጋር እንደሚረገጥ፣ ሞዓብም እንዲሁ ይረገጣል።

11ዋናተኛ ሲዋኝ እጁን እንደሚዘረጋ፣ በውስጡ ሆነው እጃቸውን ይዘረጋሉ፤ ጌታ በእጃቸው ተንኰል ሳይታለል፣ ትዕቢታቸውን ያዋርዳል።

12ከፍ ብሎ የተመሸገውን ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፤ ወደ ታች ያወርደዋል፤ ወደ ምድር አውርዶም ትቢያ ላይ ይጥለዋል።

ማብራሪያ

25:1-5 ይህ የይሁዳውያንን ከምርኮ መዳን ቢያሳይም፣ ከዚህም አልፎ፣ ክርስቶስ በመንፈሳዊ ጠላቶቻችን ላይ ለተቀዳጃቸው ድሎችና ለሚያምኑ ሁሉ ላዘጋጃቸው መጽናኛዎች ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን ምስጋና ይጠቁማል። እውነተኛ እምነት የጌታን ምስክርነት በቀላሉ ያምናል፤ የተስፋ ቃሉንም ለመፈጸም በራሱ እውነት ላይ ይደገፋል። እግዚአብሔር ትዕቢተኞችንና ራሳቸውን የጠበቁትን ኃያላን እንደሚያደክም፣ እንዲሁ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትንና በእርሱ ላይ የሚታመኑትን ደካሞችን ያበረታታል። እግዚአብሔር ሕዝቡን በየትኛውም ሁኔታ ይጠብቃል። ጌታ በእርሱ የሚታመኑትን ከጨቋኞች ትዕቢት ይጠብቃል። የእነርሱ ትዕቢት የባዕዳን ጩኸት ብቻ ነው፤ በቀን አጋማሽ እንደሚያቃጥል የፀሐይ ሙቀት ነው። ነገር ግን ፀሐይ ስትጠልቅ ወዴት ይሄዳል? ጌታ ሁልጊዜም የተቸገሩ አማኞች መሸሸጊያ ነበር፣ ሁልጊዜም ይሆናል። መሸሸጊያ ካዘጋጀላቸው በኋላ፣ ወደዚያ እንዲሸሹ ያስተምራቸዋል።

25:6-8 ንስሐ የገቡ ኃጢአተኞችን በደግነት መቀበል በአዲስ ኪዳን ብዙ ጊዜ ለግብዣ ይመሰላል። የተጠሩት እንግዶች ሁሉም ሰዎች ናቸው፤ አይሁድም አሕዛብም ጭምር። በወንጌል ውስጥ ልብን የሚያበረታና ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ፤ ለኃጢአት ኩነኔ ሥር ላሉትና ስለ ኃጢአታቸው ለሚያዝኑ ሁሉ የተገባ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG አቤቱ፥ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናለሁ። አማርኛ ENGNIV O Lord, you are my God; I will exalt you and praise your name, for in perfect faithfulness you have done marvelous thin… English BCV ኦ እግዚኣብሄር፥ ንስኻ ኣምላኸይ ኢኻ፤ ልዕል ልዕል ከብለካ ንስምካውን ክውድሶ እየ፤ ነቲ ናይ ጥንቲ ዘደንቕ ምኽሪ፥ ብፍፁም ተኣማንነት ፈፂምካዮ ኢኻሞ። ትግርኛ GAZBIB Yaa gooftaa, ati Waaqayyo koo ti, ani sin galateeffadha, maqaa kees nan jajadha; wanta dur akeeki isaa qopheeffame, isa… Afaan Oromoo BCV GIZ እግዚአብሔር አምላኪየ እሴብሐከ ወኣነብብ ለስምከ እስመ ገበርከ መንክረ ግብረ ወእሙነ ኮነ ምክረ ትካት። giz GAZGAZ Yaa gooftaa, ati Waaqayyo koo ti, ani sin galateeffadha, maqaa kees nan jajadha; wanta dur akeeki isaa qopheeffame, isa… Afaan Oromoo BCV aksum ኦ እግዚኣብሄር፥ ንስኻ ኣምላኸይ ኢኻ፤ ልዕል ልዕል ከብለካ ንስምካውን ክውድሶ እየ፤ ነቲ ናይ ጥንቲ ዘደንቕ ምኽሪ፥ ብፍፁም ተኣማንነት ፈፂምካዮ ኢኻሞ። ትግርኛ SWAHSUV Ee Bwana, wewe u Mungu wangu; Nitakutukuza na kulihimidi jina lako; Kwa kuwa umetenda mambo ya ajabu, Mashauri ya kale,… Kiswahili