ትንቢተ ኢሳይያስ 1

AMHNIVአማርኛ31 ጥቅሶች5:41 አዳምጥ
አዳምጥ 5:41 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፣ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ፤

2ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሮአልና፤ “ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመፁብኝ።

3በሬ ጌታውን፣ አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤ እስራኤል ግን አላወቀም፤ ሕዝቤም አላስተዋለም።”

4እናንተ ኀጢአተኛ ሕዝብ፣ በደል የሞላበት ወገን፣ የክፉ አድራጊ ዘር፣ ምግባረ ብልሹ ልጆች ወዮላችሁ እግዚአብሔርን ትተዋል፤ የእስራኤልን ቅዱስ አቃለዋል፤ ጀርባቸውንም በእርሱ ላይ አዙረዋል።

5ለምን ዳግመኛ ትመታላችሁ? ለምንስ በዐመፅ ትጸናላችሁ? ራሳችሁ በሙሉ ታሞአል፤ ልባችሁ ሁሉ ታውኮአል።

6ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጒራችሁ ጤና የላችሁም፤ ቍስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤ አልታጠበም፤ አልታሰረም፤ በዘይትም አልለዘበም።

7አገራችሁ ባድማ፣ ከተሞቻችሁ በእሳት የተቃጠሉ ይሆናሉ፤ ዐይናችሁ እያየ፣ መሬታችሁ በባዕድ ይነጠቃል፤ ጠፍም ይሆናል።

8የጽዮን ሴት ልጅ በወይን አትክልት ውስጥ እንዳለ ዳስ፣ በዱባ ተክል ወስጥ እንደሚገኝ ጐጆ፣ እንደ ተከበበም ከተማ ተተወች።

9የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር።

10እናንተ የሰዶም ገዦች፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሰዎች፤ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ።

11“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምኔ ነው?” ይላል እግዚአብሔር። “የሚቃጠለውን የአውራ በግና የሰቡ እንስሳትን ስብ ጠግቤአለሁ፤ በበሬ፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም ደስ አልሰኝም።

12በፊቴ ለመቅረብ ስትመጡ፣ ይህን ሁሉ እንድታመጡ፣ የመቅደሴን ደጅ እንድትረግጡ ማን ጠየቃችሁ?

13ከንቱውን መባ አታቅርቡ፤ ዕጣናችሁን እጸየፋለሁ፤ የወር መባቻ በዓላችሁን፣ ሰንበቶቻችሁን፣ ጉባኤያችሁንና በክፋት የተሞላውን ስብሰባችሁን መታገሥ አልቻልሁም።

14የወር መባቻችሁንና የተደነገጉ በዓሎቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፤ መታገሥም አልቻልሁም።

15እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፣ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤

16ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤

17መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፣ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ።

18“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።

19እሺ ብትሉ፣ ብትታዘዙም የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤

20እምቢ ብላችሁ ብታምፁ ግን ሰይፍ ይበላችኋል።” የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።

21ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደሆነች ተመልከቱ ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፣ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤ አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነ

22ብርሽ ዝጎአል፣ ምርጥ የወይን ጠጅሽ ውሃ ገባው፤

23ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጒቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።

24ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤ “በባላንጣዎቼ ላይ ቍጣዬን እገልጣለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።

25እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፣ ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ ጒድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።

26ፈራጆችሽን እንደ ጥንቱ፣ አማካሪዎችሽንም እንደ ቀድሞው እመልሳለሁ፤ ከዚያም የጽድቅ መዲና፣ የታመነች ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።

27ጽዮን በፍትሕ፣ በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ።

28ዐመፀኞችና ኀጢአታኞች ግን በአንድነት ይደቃሉ፤ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።

29“ደስ በተሰኛችሁባቸው የአድባር ዛፎች ታፍራላችሁ፤ በመረጣችኋቸውም የአትክልት ቦታዎች ትዋረዳላችሁ።

30ቅጠሉ እንደ ጠወለገ ወርካ፣ ውሃም እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁ።

31ብርቱ ሰው እንደ ገለባ፣ ሥራውም እንደ ብልጭታ ይሆናል፤ ሁለቱም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋው የለም።

ማብራሪያ

1:1-9 ኢሳይያስ ማለት 'የእግዚአብሔር ድነት' ሲሆን፣ እርሱ ስለ አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስና ስለ ድነቱ እጅግ አብዝቶ የተነበየ ነቢይ በመሆኑ ይህ ስም እጅግ ተስማሚ ነው። ራሳቸውን የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሉ ሰዎች፣ ሕይወታቸውና ምቾታቸው ከእግዚአብሔር የአባትነት እንክብካቤና ቸርነት የመነጨ መሆኑን አላወቁም ወይም አላስተዋሉም። እጅግ ብዙ ሰዎችስ በነፍሳቸው ጉዳይ ምንኛ ግድ የለሾች ናቸው! በሃይማኖት የምናውቀውን አለማጤን፣ ልናውቀው የሚገባንን እንደማናውቅ ያህል ክፉ ነው። ክፋቱ ሁሉን አቀፍ ነበር። እዚህ ጋር ንጽጽር ከታመመና ከበሽታ አካል ተወስዶ ቀርቧል። በሽታው ለሞት የሚያሰጋ ነበር። ከእግር ጫማ እስከ ራስ ድረስ፤ ከዝቅተኛው ገበሬ እስከ ታላቁ መኳንንት ድረስ ጤናማ ነገር የለም፣ መልካም መርሕ የለም፣ ሃይማኖትም የለም፤ ምክንያቱም የነፍስ ጤና ይህ ነውና። የአዳም ውድቀት አሳዛኝ ውጤቶች የሆኑ ጥፋትና ብልሹነት ብቻ እንጂ ሌላ ምንም የለም። ይህ ክፍል የሰውን ልጅ ተፈጥሮ ሙሉ በሙሉ መበላሸት ይገልጻል። ኃጢአት ንስሐ ሳይገባ ሲቀር፣ እነዚህን ቁስሎች ለመፈወስም ሆነ ገዳይ የሆኑ ውጤቶችን ለመከላከል ምንም አይደረግም። ኢየሩሳሌም የበሰሉ ፍራፍሬዎችን ለመጠበቅ እንደሚሠሩት ኩምቢዎች ወይም ጎጆዎች ተጋልጣና ጥበቃ የሌላት ነበረች። እነዚህ በምሥራቅ አገሮች ፍራፍሬዎች የሰዎች የበጋ ምግብ ትልቅ ክፍል የሚሆኑበት ቦታ አሁንም ይታያሉ። ጌታ ግን በኢየሩሳሌም የራሱ የሆነ አነስተኛ የቅሬታ ክፍል (የተረፉ) ደጋግ አገልጋዮች ነበሩት። እንዳንጠፋ የእግዚአብሔር ምሕረት ነው። ክፉው ባሕርይ በሁላችንም ውስጥ አለ፤ ኢየሱስና የሚያቀድሰው መንፈሱ ብቻ ወደ መንፈሳዊ ጤና ሊመልሱን ይችላሉ።

1:10-15 ይሁዳ በረሃማ ሆና ነበር፣ ከተሞቻቸውም ተቃጥለው ነበር። ይህም ቅጣቱን እንዲያነሳላቸውና በኃጢአታቸው እንዲቀጥሉ ፈቃድ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ለመደለል ያህል መሥዋዕቶችንና ቁርባኖችን ለማቅረብ ቀሰቀሳቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ። አማርኛ ENGNIV The vision concerning Judah and Jerusalem that Isaiah son of Amoz saw during the reigns of Uzziah, Jotham, Ahaz and Hez… English BCV ብነገስታት ይሁዳ ብዖዝያንን ኢዮኣታምን ብኣካዝን፥ ብዘመን ሕዝቅያስን፥ ወዲ ኣሞፅ ኢሳይያስ ብዛዕባ ይሁዳን ኢየሩሳሌምን ዝረአዮ ራእይ። ትግርኛ GAZBIB Mul'anni Isaayaas ilmi Amoz bara Uziyaa, Yotaam, Ahaazii fi Hisqiyaas mootota Yihudaa turanitti waa'ee Yihudaa fi waa'e… Afaan Oromoo BCV GIZ ራእይ ዘርእየ ኢሳይያስ ወልደ አምጽ ዘርእየ በእንተ ይሁዳ ወበእንተ ኢየሩሳሴም በመንግሥተ ዖዝያን ወኢዮአታም፤ ወአካዝ ወሕዝቅያስ እለ ነግሡ በይሁዳ። giz GAZGAZ Mul'anni Isaayaas ilmi Amoz bara Uziyaa, Yotaam, Ahaazii fi Hisqiyaas mootota Yihudaa turanitti waa'ee Yihudaa fi waa'e… Afaan Oromoo BCV aksum ብነገስታት ይሁዳ ብዖዝያንን ኢዮኣታምን ብኣካዝን፥ ብዘመን ሕዝቅያስን፥ ወዲ ኣሞፅ ኢሳይያስ ብዛዕባ ይሁዳን ኢየሩሳሌምን ዝረአዮ ራእይ። ትግርኛ SWAHSUV Haya ni maono ya Isaya, mwana wa Amozi, aliyoyaona katika habari za Yuda na Yerusalemu, siku za Uzia na Yothamu na Ahaz… Kiswahili