ትንቢተ ኢሳይያስ 18

AMHNIVአማርኛ7 ጥቅሶች1:59 አዳምጥ
አዳምጥ 1:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በኢትዮጵያ ወንዞች ዳር ለምትገኝ፣ ፉር ፉር የሚሉ ክንፎች ላሉባት ምድር ወዮላት!

2ይህችውም መልእክተኞችን በባሕር፣ ከወንዞች ማዶ በደንገል ጀልባ የምትልክ ናት። እናንት ፈጣን መልእክተኞች፤ ረጃጅምና ቈዳው ወደ ለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ወደሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ወደማይገባ፣ ወንዞች ምድሩን ወደሚከፍሉት መንግሥት፣ ሂዱ!

3እናንት የዓለም ሕዝቦች፣ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፣ በተራሮች ላይ ምልክት ሲሰቀል ታዩታላችሁ፤ መለከትም ሲነፋ ትሰሙታላችሁ።

4እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤ “ጸጥ ብዬ እቀመጣለሁ፤ ከማደሪያዬም በፀሓይ ሐሩር እንደሚያ ብረቀርቅ ትኵሳት፣ በመከርም ሙቀት እንደ ደመና ጠል ሆኜ እመለከታለሁ።”

5ከመከር በፊት የአበባው ወቅት ሲያልፍ፣ አበባው የጐመራ የወይን ፍሬ ሲሆን፣ የወይን ሐረጉን ተቀጥላ በመግረዣ ይገርዘዋል፤ የተንሰራፋውንም ቅርንጫፍ ቈራርጦ ያስወግደዋልና።

6ሁሉም በተራራ ላይ ለሚኖሩ ነጣቂ አሞሮች ለዱርም አራዊት ይተዋሉ፤ አሞሮች በጋውን ሁሉ ሲበሉት ይባጃሉ፤ የዱር አራዊትም ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ።

7በዚያን ጊዜ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፣ ረጃጅምና ቈዳው ከለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ከሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ከማይገባ፣ ወንዞችም ምድሩን ከሚከፍሉት መንግሥት፣ ገጸ በረከት ይመጣለታል፤ ገጸ በረከቱም የሚመጣለት የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስም ወዳለበት ወደ ጽዮን ተራራ ነው።

ማብራሪያ

ምዕራፍ ፲፰፥፩-፯ የእግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ያለው እንክብካቤ፤ የቤተ ክርስቲያንም መብዛት።

ይህ ምዕራፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እጅግ ግልጽ ካልሆኑት ክፍሎች አንዱ ነው፤ ይሁን እንጂ፣ በመጀመሪያ ለእነርሱ ዓላማ ተብሎ በተጻፈላቸው ሰዎች ዘንድ ከእኛ ይልቅ በደንብ የተረዳ ነበር። ፈጣን መልእክተኞች በውኃ ወደ መለኮታዊ አሳብ ወደተመላከተ፣ ተለክቶም ወደ ተረገጠ ሕዝብ ተልከዋል። የእግዚአብሔር ሕዝብ ይረገጣሉ፤ ነገር ግን እነርሱን ሊውጣቸው የሚያስብ ማንኛውም ሰው፣ እነርሱ ቢወድቁም፣ ያልተተዉና ያልጠፉ መሆናቸውን ያገኛል። በምድር ላይ ያሉ ነዋሪዎች ሁሉ የመለኮታዊ አሳብ እንቅስቃሴዎችን መመልከት፣ የመለኮታዊ ፈቃድ መመሪያዎችንም መጠበቅ አለባቸው።

እግዚአብሔር ለነቢዩ ማረጋገጫ ይሰጣል፤ በእርሱም በኩል ለሕዝቡ እንዲሰጥ ያደርጋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6