ትንቢተ ሆሴዕ 2

AMHEVGአማርኛ23 ጥቅሶች4:20 አዳምጥ
አዳምጥ 4:20 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወንድሞቻችሁን፦ “ዓሚ፥” እኅቶቻችሁንም፦ “ሩሃማ፡” በሉአቸው።

2እናታችሁ ሚስቴ አይደለችምና፥ እኔም ባልዋ አይደለሁምና ተምዋገቱ፤ ከእናታችሁ ጋር ተምዋገቱ። ግልሙትናዋን ከፊትዋ፥ ምንዝርናዋንም ከጡቶችዋ መካከል ታስወግድ፤

3ዕራቁትዋን እንዳልገፍፋት፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን እንዳላደርጋት፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር እንዳላደርጋት፥ በጥማትም እንዳልገድላት፤

4የግልሙትናዋ ልጆች ናቸውና ልጆችዋን አልምርም።

5እናታቸው አመንዝራለች፤ የፀነሰቻቸውም፦ “እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ጥጤንና የተልባ እግሬን፥ ዘይቴንና መጠጤን ከሚሰጡኝ ከውሽሞቼ በኋላ እሄዳለሁ፡” ብላ አስነወረቻቸው።

6ስለዚህ፥ እነሆ፥ መንገድሽን በእሾህ እዘጋለሁ፥ መንገድዋንም እንዳታገኝ ቅጥርን እቀጥርባታለሁ።

7ውሽሞችዋንም ትከተላለች፥ ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ ትፈልጋቸውማለች፥ ነገር ግን አታገኛቸውም፤ እርስዋም፦ “ከዛሬ ይልቅ የዚያን ጊዜ ይሻለኝ ነበርና ተመልሼ ወደ ቀደመው ባሌ እሄዳለሁ፡” ትላለች።

8እርስዋም እህልንና ወይንን ጠጅ ዘይትንም የሰጠኋት፥ ለበኣልም የተሠራውን ብርና ወርቅ ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም።

9ስለዚህ እህሌን በጊዜዋ፥ ወይን ጠጄንም በወረትዋ እወስዳለሁ፥ ዕራቁትነትዋንም እንዳትሸፍን ጥጤንና የተልባ እግሬን እገፍፋታለሁ።

10አሁንም ውሽሞችዋ እያዩ ነውርዋን እገልጣለሁ፤ ከእጄም ማንም አያድናትም።

11ደስታዋንም ሁሉ፥ በዓላቶችዋንም፥ መባቻዎችዋንም፥ ሰንበቶችዋንም፥ የተቀደሱትንም ጉባኤዎችን ሁሉ አስቀራለሁ።

12እርስዋም፦ “ውሽሞቼ የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው፡” ያለችውን ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ዱርም አደርገዋለሁ፥ የምድረ በዳም አራዊት ይበሉታል።

13እኔን ረስታ ውሽሞችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም ያጠነችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።

14ስለዚህ፥ እነሆ፥ አባብላታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳም አመጣታለሁ፥ ለልብዋም እናገራለሁ።

15ከዚያም የወይን ቦታዋን፥ የተስፋ በርም እንዲሆንላት የአኮርን ሸለቆ እሰጣታለሁ፤ በዚያም ከግብፅ ምድር እንደ ወጣችበት ቀን እንደ ሕፃንነትዋ ወራት ትዘምራለች።

16“በዚያ ቀን ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ ዳግመኛ በኣሌ ብለሽ አትጠሪኝም፥ ይላል እግዚአብሔር፤

17የበኣሊምን ስም ከአፍዋ አስወግደዋለሁና፥ በስማቸውም እንግዲህ አይታሰቡምና።

18በዚያም ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች ከመሬትም ተንቀሳቃሾች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ ቀስትንና ሰይፍን ሰልፍንም ከምድሩ እሰብራለሁ፥ ተከልለውም እንዲኖሩ አስተኛቸዋለሁ።

19ለዘላለምም ለእኔ እንድትሆኚ አጭሻለሁ፤ በጽድቅና በፍርድ በምሕረትና በርኅራኄ አጭሻለሁ።

20ለእኔም እንድትሆኚ በመታመን አጭሻለሁ፤ አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂአለሽ።

21በዚያንም ቀን እመልሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለሰማይ እመልሳለሁ፥ ሰማይም ለምድር ይመልሳል፤

22ምድርም ለእህልና ለወይን ጠጅ ለዘይትም ትመልሳለች፤ እነርሱም ለኢይዝራኤል ይመልሳሉ።

23በምድርም ላይ ለእኔ እዘራታለሁ፤ “ምሕረትም የሌላትን” እምራለሁ፥“ “ሕዝቤም” ያልሆነውን፦ “አንተ ሕዝቤ ነህ፡” እለዋለሁ፤ እርሱም፦ “አንተ አምላኬ ነህ፡” ይለኛል።

ማብራሪያ

ምዕራፍ 2፡1-5 ይህ ምዕራፍ፣ ከሆሴዕ ሚስትና ልጆች ጋር በተያያዘ፣ ለእስራኤል የተሰጠውን ምሳሌያዊ ንግግር ይቀጥላል። ጌታ ከልጆቹ መካከል የሚያስቀምጣቸውን ሁሉ እንደ ወንድሞችና እህቶች እንቀበል እንዲሁም እንውደድ፤ ምሕረትንም እንደተቀበሉ እናበረታታቸው። ነገር ግን እያንዳንዱ ክርስቲያን በምሳሌውና በኑሮው ክፋትንና በደሎችን መቃወም አለበት፤ የራሱ ከሆኑትና ክብር ከሚገባው መካከል እንኳ ቢሆን። ንስሐ የማይገቡ ኃጢአተኞች አላግባብ የሚጠቀሙባቸውን ጥቅሞች እንዲሁም ምኞቶቻቸውን ለማርካት የሚፈጁአቸውን ነገር በቅርቡ ይገፈፋሉ።

2:6-13 እግዚአብሔር በዚህ ከሃዲና ጣዖት አምላኪ ሕዝብ ላይ የሚያደርገውን ያስጠንቅቃል። እነርሱ አልተመለሱም ነበርና፣ በዚህም ምክንያት ይህ ሁሉ ደረሰባቸው፤ እኛንም ለማስጠንቀቅ ተጽፏል። አነስተኛ ችግሮች ቢታለፉ፣ እግዚአብሔር የላቁትን ያመጣል። በኃጢአት ፍላጎቶቻቸው እጅግ ቆራጥ የሆኑት፣ ብዙውን ጊዜ በእነዚያው በጣም ይገደባሉ። የእግዚአብሔርና የትእዛዝ መንገድ ብዙ ጊዜ በእሾህ የታጠረ ነው፣ ነገር ግን በእሾህ የታጠረ መንገድ የኃጢአት መንገድ እንደሆነ ለማሰብ ምክንያት አለን። በክፉ መንገድ የሚገጥሙ እንቅፋቶችና መከራዎች ታላላቅ በረከቶች ናቸው፤ እንዲሁ ተደርገው ሊቆጠሩ ይገባል። እነርሱ ከመተላለፍ ለመጠበቅ፣ የኃጢአትን መንገድ አስቸጋሪ ለማድረግ፣ እንዲሁም ከእርሱ ለመጠበቅ የእግዚአብሔር አጥሮች ናቸው። ከኃጢአት የሚጠብቀን ከሆነ፣ እግዚአብሔርን በሚገድብ ጸጋውና በሚገድቡ የአሠራሮቹ፣ አልፎ ተርፎም ለከባድ ሕመም፣ ለበሽታ ወይም ለአደጋ ልንባርከው ምክንያት አለን። ከፍጥረት እርካታን ስንፈልግ የሚገጥሙን ብስጭቶች፣ ሌላ ምንም ማድረግ ካልቻለ፣ ወደ ፈጣሪ ሊያመሩን ይገባል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6