ወደ ዕብራውያን 3

AMHNIVአማርኛ19 ጥቅሶች2:48 አዳምጥ
አዳምጥ 2:48 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ የሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፤ የእምነታችን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ።

2ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ ታማኝ እንደ ነበር፣ እርሱም ለሾመው ታማኝ ነበር።

3ቤትን የሚሠራ ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው፣ ኢየሱስም ከሙሴ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተገኝቶአል፤

4እያንዳንዱ ቤት የራሱ ሠሪ አለው፤ ነገር ግን ሁሉን የሠራ እግዚአብሔር ነው።

5ሙሴ ወደ ፊት ስለሚነገረው ነገር እየመሰከረ፣ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ እንደ አንድ ታማኝ አገልጋይ ነበር፤

6ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ታማኝ ልጅ ነው። እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።

7ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፣ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣

8በምድረ በዳ በፈተና ቀን፣ በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።

9አባቶቻችሁ በዚያ ተፈታተኑኝ፤ መረመሩኝ፤ ያደረግሁትንም ሁሉ ለአርባ ዓመት አዩ።

10በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤ እንዲህም አልሁ፤ ‘ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል፤ መንገዴንም አላወቁም፤’

11ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤ “ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም።”

12ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።

13ነገር ግን ከመካከላችሁ ማንም በኀጢአት ተታሎ ልቡ እንዳይደነድን፣ “ዛሬ” እየተባለ ሳለ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።

14በመጀመሪያ የነበረንን እምነት እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንይዝ ከክርስቶስ ጋር ተካፋዮች እንሆናለን፤

15ይኸውም፣ “ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ፣ በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ አሁንም ልባችሁን አታደንድኑ” እንደ ተባለው ነው።

16ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ ከግብፅ መርቶ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን?

17አርባ ዓመት የተቈጣውስ እነማንን ነበር? ኀጢአት ሠርተው ሬሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረውን አይደለምን?

18ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ?

19እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ካለማመናቸው የተነሣ እንደሆነ እንረዳለን።

ማብራሪያ

3:1-6 ክርስቶስ የምንመሰክረው የእምነታችን ሐዋርያ፣ በእግዚአብሔር ወደ ሰዎች የተላከ መልእክተኛ፣ የምንይዘው ብለን የምንመሰክረው የእምነትና የምንመሰክረው የተስፋ ታላቅ ገላጭ ሆኖ ሊታይ ይገባል። እንደ ክርስቶስ፣ መሲህ፣ ለሐዋርያነትም ለሊቀ ካህንነትም ለሥራው የተቀባ፤ እንደ ኢየሱስም፣ አዳኛችን፣ ፈዋሻችን፣ የነፍሳት ታላቅ ሐኪም ነው። እርሱን እንዲህ እንመልከተው። እርሱ በራሱ ምን እንደሆነ፣ ለእኛም ምን እንደሆነ፣ ከዚህ በኋላም ለዘላለም ለእኛ ምን እንደሚሆን እንመልከት። ክርስቶስን በጥልቀትና በቁም ነገር ማሰላሰል ስለ እርሱ ይበልጥ እንድናውቅ ያደርገናል።

አይሁድ የሙሴን ታማኝነት ከፍ አድርገው ያዩት ነበር፤ ሆኖም የእርሱ ታማኝነት የክርስቶስ ታማኝነት ምሳሌ ብቻ ነበር። ክርስቶስ የዚህ ቤት፣ የቤተ ክርስቲያኑ፣ የሕዝቡ ጌታ እንዲሁም ፈጣሪያቸው ነበር። ሙሴ ታማኝ አገልጋይ ነበር፤ ክርስቶስ ግን፣ እንደ እግዚአብሔር የዘላለም ልጅ፣ የቤተ ክርስቲያን ህጋዊ ባለቤትና ሉዓላዊ ገዥ ነው። በክርስቶስ መንገዶች ላይ በሚገባ መጀመር ብቻ ሳይሆን፣ እስከ መጨረሻው ድረስ ጽናትና ጸንቶ መቆየትም ሊኖር ይገባል። ስለ እርሱ ማንነትና ስለ ድነቱ እያንዳንዱ ማሰላሰል የበለጠ ጥበብን፣ ለመውደድ፣ ለመታመንና ለመታዘዝ አዳዲስ መነሳሳቶችን ያመጣል።

3:7-13 የፈተና ቀናት ብዙ ጊዜ የመቀስቀሻ ቀናት ናቸው። ነገር ግን እኛ ሙሉ በሙሉ በእርሱ እንደምንደገፍና በእርሱ እንደምንኖር ሲያሳየን እግዚአብሔርን ማስቆጣት በእርግጥም ትልቅ ቁጣን የሚያስነሳ ነው። የልብ መደንደን ለሌሎች ኃጢአቶች ሁሉ ምንጭ ነው። የሌሎች ኃጢአቶች፣ በተለይም የዘመዶቻችን፣ ለእኛ ማስጠንቀቂያ ሊሆኑን ይገባል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤ አማርኛ ENGNIV Therefore, holy brothers, who share in the heavenly calling, fix your thoughts on Jesus, the apostle and high priest wh… English BCV እምበኣር ኣቱም ካብቲ ሰማያዊ መፀዋዕታ፥ ተኻፈልቲ ዝኾንኩም ቅዱሳን ኣሕዋትና፥ ናይ እምነትና ሃዋርያን ሊቀ ካህናትን ንዝኾነ ኢየሱስ ተመልከትዎ። ትግርኛ GAZBIB Kanaafis yaa obboloota Waaqayyoof qulqullooftanii, waamicha isa waaqa irraa keessaa hirmaattanii! Yesusin ergamaa fi an… Afaan Oromoo BCV GIZ ወይእዜኒ አኀዊነ ቅዱሳን ወጽዉዓን እምሰማይ በጽዋዔ ከማነ ርእይዎ ለዝንቱ ሐዋርያክሙ ሊቀ ካህናት ዘኪያሁ ትትአመኑ ኢየሱስ ክርስቶስ። giz GAZGAZ Kanaafis yaa obboloota Waaqayyoof qulqullooftanii, waamicha isa waaqa irraa keessaa hirmaattanii! Yesusin ergamaa fi an… Afaan Oromoo BCV aksum እምበኣር ኣቱም ካብቲ ሰማያዊ መፀዋዕታ፥ ተኻፈልቲ ዝኾንኩም ቅዱሳን ኣሕዋትና፥ ናይ እምነትና ሃዋርያን ሊቀ ካህናትን ንዝኾነ ኢየሱስ ተመልከትዎ። ትግርኛ SWAHSUV Kwa hiyo, ndugu watakatifu, wenye kuushiriki mwito wa mbinguni, mtafakarini sana Mtume na Kuhani Mkuu wa maungamo yetu,… Kiswahili