ትንቢተ ሕዝቅኤል 8

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች4:03 አዳምጥ
አዳምጥ 4:03 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በስድስተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፣ በዚያ የጌታ እግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣች።

2እኔም አየሁ፤ እነሆ፤ የሰውን ልጅ የሚመስል ነበረ፤ ወገቡ ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ታች እንደ እሳት ያለ ነበር፤ ወገቡንም ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ላይ እንደ ጋለ ብረት ያበራ ነበር።

3እርሱም እጅ መሳይ ዘርግቶ የራስ ጠጕሬን ያዘ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፤ እርሱም ቅናት የሚያነሣው ጣዖት ወደ ቆመበት፣ ወደ ውስጠኛው አደባባይ መግቢያ ወደ ሰሜን በር ወደ ኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ራእይ ወሰደኝ።

4እነሆ፤ በረባዳው ስፍራ በራእይ ያየሁት የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበረ።

5እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ወደ ሰሜን ተመልከት” አለኝ። እኔም ተመለከትሁ፤ እነሆ ከመሠዊያው በር በሰሜን በኩል መግቢያው ላይ ይህ የቅናት ጣዖት ነበረ።

6ደግሞም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ከመቅደሴ ያርቀኝ ዘንድ በዚህ የሚያደርገውን እጅግ አስጸያፊ ነገር ታያለህን? ከዚህም የባሰ አስጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ።

7ከዚያም በኋላ ወደ አደባባዩ መግቢያ አመጣኝ፤ እኔም ግንቡን ተመለከትሁ፤ ቀዳዳም ነበረበት።

8እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ግንቡን ንደለው” አለኝ፤ እኔም ግንቡን ነደልሁት፤ አንድ በርም አገኘሁ።

9እርሱም፣ “ግባና በዚህ የሚፈጽሙትን እጅግ የከፋ ርኵሰት ተመልከት አለኝ።

10እኔም ገብቼ አየሁ፤ እነሆ በደረታቸው የሚሳቡ ፍጡራንና የርኵሳን አራዊት ዐይነት ሁሉ፣ የእስራኤልም ቤት ጣዖታት ሁሉ ዙሪያውን በግንቡ ላይ ተቀርጸው ነበር።

11በእነዚህም ፊት ከእስራኤል ቤት ሰባ ሽማግሌዎች ቆመው ነበር፤ በመካከላቸውም የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆሞ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በእጃቸው ጥና ይዘዋል፤ መልካም መዐዛ ያለው የዕጣን ጢስም እየተትጐለጐለ ይወጣ ነበር።

12እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዳቸው በጣዖታቸው ምስል ጓዳ ውስጥ በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ፣ ‘እግዚአብሔር አያየንም፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአል” ይላሉ” አለኝ።

13ደግሞም፣ “ከእነዚህ የባሰ አስጸያፊ ነገር ሲሠሩ ታያለህ” አለኝ።

14ከዚህም በኋላ በሰሜን በኩል ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ በዚያም ሴቶች ተቀምጠው ተሙዝ ለተባለው ጣዖት ሲያለቅሱ አየሁ።

15እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን አይተሃልን? ከዚህም የባሰ አስጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ።

16ደግሞም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በመተላለፊያውና በመሠዊያው መካከል በቤተ መቅደሱ መግቢያ ላይ ሃያ አምስት ሰዎች ያህል ነበሩ፤ ጀርባቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፣ ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አድርገው ለምትወጣዋ ፀሓይ ይሰግዱ ነበር።

17እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህን አይተሃልን? የይሁዳ ቤት በዚህ ቦታ የሚፈጽሙት ጸያፍ ተግባር ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱንስ በዐመፅ በመሙላት ዘወትር ያስቈጡኝ ዘንድ ይገባልን? እነሆ፤ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫቸው አቅርበዋል!

18ስለዚህ በቍጣ እመጣባቸዋለሁ፤ በርኅራኄ ዐይን አላያቸውም፤ ከሚመጣባቸው ነገር አላድናቸውም፤ ወደ ጆሮዬም ቢጮኹ አልሰማቸውም።”

ማብራሪያ

፰:፩-፮ ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ክቡር አካል የያዘው ይመስል ነበር፤ እርሱም በመንፈስ ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ። በዚያም፣ በቤተ መቅደሱ የውስጥ ግቢ ውስጥ፣ ለአንዳንድ ወራዳ ጣዖት የሚሆን ስፍራ ተዘጋጅቶ ነበር። ይህ ሁሉ ለነቢዩ በራእይ ተገለጠለት። እግዚአብሔር ፈቃዱ ቢሆንና ማንኛውም ሰው የእርሱን ክብርና ግርማ ሞገስ፣ እንዲሁም በማንኛውም ከተማ የሚፈጸሙትን ርኩሰቶች ሁሉ በግልጽ እንዲያይ ቢያደርገው፣ ያኔ እግዚአብሔር በእርሷ ላይ ሊያደርጋቸው የሚገቡትን የከፋ ቅጣቶች ፍትሐዊነት ይረዳ ነበር።

፰:፯-፲፪ ሚስጥራዊ ስፍራ እንደተከፈተ ያህል ነበር፤ ነቢዩም በግድግዳዎች ላይ የተቀረጹ ፍጥረታትን፣ የእስራኤልም ሽማግሌዎች ቁጥር በፊታቸው ሲሰግዱ አየ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በስድስተኛውም ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ወደቀች። አማርኛ ENGNIV In the sixth year, in the sixth month on the fifth day, while I was sitting in my house and the elders of Judah were si… English BCV ኮነ ድማ፥ ኣብ ሻድሸይቲ ዓመት፥ ኣብታ ሻድሸይቲ ወርሒ፥ ካብታ ወርሒውን ኣብ ሓምሸይቲ መዓልቲ፥ ኣብ ቤተይ ተቐሚጠ እንተለኹ፥ እቶም ዓበይቲ ይሁዳውን ኣብ ቅድመይ ተቐሚጦም እንተለዉ፥ ኣብኡ… ትግርኛ GAZBIB Waggaa ja'affaatti, waggicha keessaas ji'a ja'affaatti, ji'icha keessaa immoo guyyaa shanaffaatti, ani mana koo keessa … Afaan Oromoo BCV GIZ ወኮነ በሳድስ ዓመት በሳድስ ወርኅ በኅሙስ ሠርቅ፡ እንዘ ሀሎኩ እነብር ውስተ ቤትየ ወረበናተ አይሁድ ይነብሩ ቅድሜየ፤ ወመጽአ እደ እግዚአብሔር አዶናይ ኅቤየ። giz GAZGAZ Waggaa ja'affaatti, waggicha keessaas ji'a ja'affaatti, ji'icha keessaa immoo guyyaa shanaffaatti, ani mana koo keessa … Afaan Oromoo BCV aksum ኮነ ድማ፥ ኣብ ሻድሸይቲ ዓመት፥ ኣብታ ሻድሸይቲ ወርሒ፥ ካብታ ወርሒውን ኣብ ሓምሸይቲ መዓልቲ፥ ኣብ ቤተይ ተቐሚጠ እንተለኹ፥ እቶም ዓበይቲ ይሁዳውን ኣብ ቅድመይ ተቐሚጦም እንተለዉ፥ ኣብኡ… ትግርኛ SWAHSUV Ikawa katika mwaka wa sita, mwezi wa sita, siku ya tano ya mwezi, nilipokuwa nikikaa nyumbani mwangu, wazee wa Yuda nao… Kiswahili