ትንቢተ ሕዝቅኤል 8

AMHEVGአማርኛ18 ጥቅሶች3:54 አዳምጥ
አዳምጥ 3:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በስድስተኛውም ዓመት በስድስተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ወደቀች።

2እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ እንደ እሳት የሚመስል አምሳያ ነበረ፤ ከወገቡም ምሳሌ ወደ ታች እሳት ነበረ፥ ከወገቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እንደሚብለጨለጭም የወርቅ ምሳሌ ነበረ።

3እጅ መሳይንም ዘረጋ በራስ ጠጕሬም ያዘኝ፤ መንፈስም በምድርና በሰማይ መካከል አነሣኝ፥ በእግዚአብሔርም ራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ሰሜን ወደሚመለከተው ወደ ውስጠኛው አደባባይ በር መግቢያ አመጣኝ፤ በዚያም ቅንዓት የሚያነሣሣ የቅንዓት ጣዖት ተተክሎ ነበር።

4እነሆም፥ በቈላው እንዳየሁት ራእይ የእስራኤል አምላክ ክብር በዚያ ነበረ።

5እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ዓይንህን ወደ ሰሜን መንገድ አንሣ፡ አለኝ። ዓይኔንም ወደ ሰሜን መንገድ አነሣሁ፤ እነሆም፥ በመሠዊያው በር በሰሜን በኩል በመግቢያው ይህ የቅንዓት ጣዖት ነበረ።

6እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የሚያደርጉትን፥ ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉትን ታላቁን ርኵሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኵሰት ታያለህ፡ አለኝ።

7ወደ አደባባዩም መግቢያ አመጣኝ፤ ባየሁም ጊዜ፥ እነሆ፥ በግንቡ ውስጥ ፉካ ነበረ።

8እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ግንቡን ንደለው፡ አለኝ፤ ግንቡንም በነደልሁት ጊዜ መዝጊያ አገኘሁ።

9እርሱም፦ ግባ፥ በዚህም የሚያደርጉትን ክፉውን ርኵሰት እይ፡ አለኝ።

10እኔም ገባሁና እነሆ፥ በግንቡ ዙሪያ ላይ የተንቀሳቃሾችና የርኩሳን አራዊት ምሳሌ የእስራኤልንም ቤት ጣዖታት ሁሉ ተስለው አየሁ።

11በፊታቸውም ከእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች ሰባ ሰዎች ቆመው ነበር፥ በመካከላቸውም የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆሞ ነበር፥ ሰውም ሁሉ እያንዳንዱ በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ የዕጣኑም ጢስ ሽቱ ይወጣ ነበር።

12እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በጨለማ እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ፦ እግዚአብሔር አያየንም፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል፡ ይላሉና፡ አለኝ።

13እርሱም፦ ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠውን የሚያደርጉትን ታላቅ ርኵሰት ታያለህ፡ አለኝ።

14ወደ ሰሜንም ወደሚመለከተው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ፤ እነሆም፥ ሴቶች ለተሙዝ እያለቀሱ በዚያ ተቀምጠው ነበር።

15እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? ደግሞ ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ርኵሰት ታያለህ፡ አለኝ።

16ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፥ እነሆም፥ በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሀያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።

17እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሚያደርጉትን ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ ለይሁዳ ቤት ጥቂት ነገር ነውን? ምድሪቱን በግፍ ሞልተዋታል ያስቈጡኝም ዘንድ ተመልሰዋል፤ እነሆም፥ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫው አቅርበዋል።

18ስለዚህ እኔ ደግሞ በመዓት እሠራለሁ፤ ዓይኔ አይራራም እኔም አላዝንም፤ ወደ ጆሮዬም በታላቅ ድምፅ ቢጮኹ አልሰማቸውም፡ አለኝ።

ማብራሪያ

፰:፩-፮ ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ክቡር አካል የያዘው ይመስል ነበር፤ እርሱም በመንፈስ ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ። በዚያም፣ በቤተ መቅደሱ የውስጥ ግቢ ውስጥ፣ ለአንዳንድ ወራዳ ጣዖት የሚሆን ስፍራ ተዘጋጅቶ ነበር። ይህ ሁሉ ለነቢዩ በራእይ ተገለጠለት። እግዚአብሔር ፈቃዱ ቢሆንና ማንኛውም ሰው የእርሱን ክብርና ግርማ ሞገስ፣ እንዲሁም በማንኛውም ከተማ የሚፈጸሙትን ርኩሰቶች ሁሉ በግልጽ እንዲያይ ቢያደርገው፣ ያኔ እግዚአብሔር በእርሷ ላይ ሊያደርጋቸው የሚገቡትን የከፋ ቅጣቶች ፍትሐዊነት ይረዳ ነበር።

፰:፯-፲፪ ሚስጥራዊ ስፍራ እንደተከፈተ ያህል ነበር፤ ነቢዩም በግድግዳዎች ላይ የተቀረጹ ፍጥረታትን፣ የእስራኤልም ሽማግሌዎች ቁጥር በፊታቸው ሲሰግዱ አየ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV In the sixth year, in the sixth month on the fifth day, while I was sitting in my house and the elders of Judah were si… English BCV ኮነ ድማ፥ ኣብ ሻድሸይቲ ዓመት፥ ኣብታ ሻድሸይቲ ወርሒ፥ ካብታ ወርሒውን ኣብ ሓምሸይቲ መዓልቲ፥ ኣብ ቤተይ ተቐሚጠ እንተለኹ፥ እቶም ዓበይቲ ይሁዳውን ኣብ ቅድመይ ተቐሚጦም እንተለዉ፥ ኣብኡ… ትግርኛ GAZBIB Waggaa ja'affaatti, waggicha keessaas ji'a ja'affaatti, ji'icha keessaa immoo guyyaa shanaffaatti, ani mana koo keessa … Afaan Oromoo BCV GIZ ወኮነ በሳድስ ዓመት በሳድስ ወርኅ በኅሙስ ሠርቅ፡ እንዘ ሀሎኩ እነብር ውስተ ቤትየ ወረበናተ አይሁድ ይነብሩ ቅድሜየ፤ ወመጽአ እደ እግዚአብሔር አዶናይ ኅቤየ። giz GAZGAZ Waggaa ja'affaatti, waggicha keessaas ji'a ja'affaatti, ji'icha keessaa immoo guyyaa shanaffaatti, ani mana koo keessa … Afaan Oromoo BCV aksum ኮነ ድማ፥ ኣብ ሻድሸይቲ ዓመት፥ ኣብታ ሻድሸይቲ ወርሒ፥ ካብታ ወርሒውን ኣብ ሓምሸይቲ መዓልቲ፥ ኣብ ቤተይ ተቐሚጠ እንተለኹ፥ እቶም ዓበይቲ ይሁዳውን ኣብ ቅድመይ ተቐሚጦም እንተለዉ፥ ኣብኡ… ትግርኛ AMHNIV በስድስተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በአምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፣ በዚያ የጌታ እግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣች። አማርኛ SWAHSUV Ikawa katika mwaka wa sita, mwezi wa sita, siku ya tano ya mwezi, nilipokuwa nikikaa nyumbani mwangu, wazee wa Yuda nao… Kiswahili