ትንቢተ ሕዝቅኤል 39

AMHNIVአማርኛ29 ጥቅሶች5:49 አዳምጥ
አዳምጥ 5:49 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“አንተ የሰው ልጅ ሆይ፤ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሞሳሕና የቶቤል ዋና አለቃ ጎግ ሆይ፤ ተነሥቼብሃለሁ፤

2ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፤ እንዲሁም እጐትትሃለሁ፤ ከሩቅ ሰሜን አምጥቼ በእስራኤል ተራሮች ላይ እሰድሃለሁ።

3በግራ እጅህ ያለውን ቀስትህን እመታለሁ፤ በቀኝ እጅህ የያዝሃቸውንም ፍላጾች አስረግፍሃለሁ።

4አንተና ወታደሮችህ ሁሉ፣ ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝቦች በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ። ነጣቂ አሞሮችና የዱር አራዊት ይበሏችሁ ዘንድ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።

5አውላላ ሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

6በማጎግና ያለ ሥጋት በባሕር ዳርቻ በሚኖሩት ላይ እሳት እሰዳለሁ፤ እነርሱም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።

7“ ‘ቅዱሱ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል ዘንድ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅዱስ ስሜ እንዲናቅ፣ እንዲቃለል አልፈልግም፤ አሕዛብም እኔ እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ እንደሆንሁ ያውቃሉ።

8እነሆ ይመጣል፤ በእርግጥም ይሆናል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ያ ያልሁት ቀን ይህ ነው።

9“ ‘ከዚያም በእስራኤል ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ወጥተው የጦር መሣሪያውን፣ ትልልቁንና ትንንሹን ጋሻ፣ ቀስቱን፣ ፍላጻውን፣ የጦር ዱላውንና ጦሩን ሰብስበው ማገዶ በማድረግ ያነዱታል፤ ሰባት ዓመት ይማግዱታል።

10ከሜዳ ላይ ዕንጨት መልቀም፣ ከዱርም ዛፍ መቍረጥ አያስፈልጋቸውም፤ የጦር መሣሪያቸውን በመማገድ ይጠቀማሉና። የዘረፏቸውን ይዘርፋሉ፤ የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

11“ ‘በዚያ ቀን ሰዎች በምሥራቅ በኩል ወደ ባሕሩ በሚጓዙበት ሸለቆ፣ ለጎግ የመቃብር ስፍራ በእስራኤል እሰጠዋለሁ። ጎግና ሰራዊቱ ሁሉ በዚያ ስለሚቀበሩ፣ የተጓዦችን መንገድ ይዘጋሉ፤ ስለዚህም የሐሞን ጎግ ሸለቆ ይባላል።

12“ ‘ምድሪቱን ለማጽዳት፣ የእስራኤል ቤት ሰዎች ሰባት ወር ሙሉ ይቀብሯቸዋል።

13የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ይቀብሯቸዋል፤ እኔ የምከብርበትም ዕለት የመታሰቢያ ቀን ይሆናቸዋል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

14“ ‘ሰዎች ምድሪቱን ለማጽዳት በየጊዜው ይቀጠራሉ። አንዳንዶቹ ምድሪቱን ያስሳሉ፤ ከእነርሱም በተጨማሪ ሌሎች ሳይቀበሩ የቀሩትን ይቀብራሉ። ከሰባት ወር በኋላም ፍለጋ ይጀምራሉ።

15እነርሱም በምድሪቱ መካከል ሲሄዱ፣ ከእነርሱ አንዱ የሰው ዐፅም ባየ ቍጥር ምልክት ያደርግበታል፤ ይህም መቃብር ቈፋሪዎች በሐሞን ጎግ ሸለቆ እስኪቀብሩት ድረስ ነው።

16በዚያም ሐሞና የምትባል ከተማ አለች፤ ስለዚህ ምድሯን ያጸዳሉ።’

17“ ‘የሰው ልጅ ሆይ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ማንኛውንም ዐይነት ወፍና የዱር አራዊት ሁሉ ጥራ፤ እንዲህም በላቸው፤ “ከየአቅጣጫው ተሰብስባችሁ እኔ ወደማዘጋጅላችሁ መሥዋዕት ኑ፤ ይህም በእስራኤል ተራሮች ላይ የሚሆን ታላቁ መሥዋዕት ነው። በዚያ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ደምም ትጠጣላችሁ።

18እንደ አውራ በግና እንደ ጠቦት፤ እንደ ፍየልና እንደ ወይፈን፣ የኀያላን ሰዎችን ሥጋ ትበላላችሁ፤ የምድርንም መሳፍንት ደም ትጠጣላችሁ፤ እነዚህ ሁሉ የሰቡ የባሳን ከብቶች ናቸው።

19እኔ በማዘጋጅላችሁም መሥዋዕት እስክትጠግቡ ስብ ትበላላችሁ፤ እስክትሰክሩም ደም ትጠጣላችሁ።

20በገበታዬም ፈረሶችንና ፈረሰኞችን፣ ኀያላን ሰዎችንና ከየወገኑ የሆኑትን ወታደሮች እስክትጠግቡ ትበላላችሁ፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

21“ክብሬን በአሕዛብ መካከል እገልጣለሁ፤ አሕዛብም ሁሉ በእነርሱ ላይ ያመጣሁትን ቅጣትና በላያቸው ላይ የጫንሁትን እጅ ያያሉ።

22ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የእስራኤል ቤት እኔ እግዚአብሔር፣ አምላካቸው እንደሆንሁ ያውቃሉ።

23አሕዛብም የእስራኤል ሕዝብ ለእኔ ታማኞች ባለመሆን ከሠሩት ኀጢአት የተነሣ እንደ ተሰደዱ ያውቃሉ፤ ስለዚህ ፊቴን ከእነርሱ ሰወርሁ፤ ለጠላቶቻቸው አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወደቁ።

24እንደ ርኵሰታቸውና እንደ በደላቸው መጠን ፈረድሁባቸው፤ ፊቴንም ከእነርሱ ሰወርሁ።

25“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ያዕቆብን አሁን ከስደት እመልሰዋለሁ፤ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እራራለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ።

26የሚያስፈራቸው ማንም ሳይኖር በምድራቸው በሰላም በሚኖሩበት ጊዜ፣ ውርደታቸውንና ለእኔ ታማኝ ሆነው ያልኖሩበትን ዘመን ይረሳሉ።

27ከአሕዛብ ምድር መልሼ ሳመጣቸው፣ ከጠላቶቻቸው አገር ስሰበስባቸው የራሴን ቅድስና በእነርሱ በኩል በብዙ ሕዝቦች ፊት አሳያለሁ።

28በአሕዛብ መካከል እንዲሰደዱ ባደርግም፣ አንድም ሳላስቀር ወደ ገዛ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደሆንሁ ያውቃሉ።

29ከእንግዲህ ፊቴን ከእነርሱ አልሰውርም፤ መንፈሴን በእስራኤል ቤት ላይ አፈሳለሁና፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

ማብራሪያ

39:1-10 እግዚአብሔር እጅግ ግድየለሾችና ደንዳና ኃጢአተኞችን ቅዱስ ስሙን ወይ በጽድቅ ቁጣው ወይ በምህረቱና በጸጋው ባለጠግነት ያስያውቃል። በጽዮን ላይ የተነሱ የጦር መሳሪያዎች አይሳካላቸውም። ይህ ትንቢት በመጨረሻዎቹ ዘመናት የሚፈጸም ቢሆንም፣ እርግጥ ነው። ጥቅም ላይ ከዋለው አነጋገር በመነሳት፣ የጎግ ሠራዊት በተአምር የሚጠፋ ይመስላል።

39:11-22

እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ለመጠበቅ ያጠፋቸው ጠላቶች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው! ታላቅ ድነት የተደረገባቸው ጊዜያት የመታደስ ጊዜያት መሆን አለባቸው። እያንዳንዱ ሰው ምድሪቱን ከነውር ለማንጻት በሚቻለው መጠን ሁሉ ሊረዳ ይገባል። ኃጢአት እያንዳንዱ ሰው ሊታገለው የሚገባ ጠላት ነው። በሕዝብ ሥራ ላይ የተሰማሩት፣ በተለይም ምድሪቱን የማንጻትና የማደስ ሥራ ላይ ያሉት፣ የጀመሩትን እስከመጨረሻው የሚያከናውኑና ሁልጊዜም በትጋት የሚሠሩ ሰዎች መሆን አለባቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሳሕና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ አማርኛ ENGNIV “Son of man, prophesy against Gog and say: ‘This is what the Sovereign Lord says: I am against you, O Gog, chief prince… English BCV “ኣታ ወዲ ሰብ፥ ንጎግ ተነበየሉ፤ እግዚኣብሄር ኣምላኽ ከምዙይ ይብል ኣሎ ኢልካውን ንገሮ፥ ኣታ ጎግ ሓለቓ ሞሳሕን ቶቤልን እኒሀኹ፥ ኣነ ኣብ ልዕሌኻ እየ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo gooftaan,“Yaa mucaa namaa! Ati Goog irratti raajii dubbadhu!“Yaa Goog angafa Rosh, angafa Meshek, angafa Tubaa… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአንተ ወልደ ዕጓለ እመሕያው፡ ተነበይ ላዕላ ጎግ ወበል፦ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር እግዚእ፦ ናሁ አነ ላዕሌከ ጎግ መልአከ ወርእሰ ሞሳሕ ወቶቤል፤ giz GAZGAZ Waaqayyo gooftaan,“Yaa mucaa namaa! Ati Goog irratti raajii dubbadhu!“Yaa Goog angafa Rosh, angafa Meshek, angafa Tubaa… Afaan Oromoo BCV aksum “ኣታ ወዲ ሰብ፥ ንጎግ ተነበየሉ፤ እግዚኣብሄር ኣምላኽ ከምዙይ ይብል ኣሎ ኢልካውን ንገሮ፥ ኣታ ጎግ ሓለቓ ሞሳሕን ቶቤልን እኒሀኹ፥ ኣነ ኣብ ልዕሌኻ እየ። ትግርኛ SWAHSUV Na wewe, mwanadamu, tabiri juu ya Gogu, useme, Bwana MUNGU asema hivi, Tazama, mimi ni juu yako, Ewe Gogu, mkuu wa Rosh… Kiswahili