ትንቢተ ሕዝቅኤል 39

AMHEVGአማርኛ28 ጥቅሶች5:19 አዳምጥ
አዳምጥ 5:19 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ በጎግ ላይ ትንቢትን ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሞሳሕና የቶቤል ዋነኛ አለቃ ጎግ ሆይ፥ እነሆ፥ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤

2እመልስሃለሁ፥ እነዳህማለሁ፥ ከሰሜንም ዳርቻ እጐትትሃለሁ፥ ወደ እስራኤልም ተራሮች አመጣሃለሁ።

3ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፥ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ።

4አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፤ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።

5አንተ በምድር ፊት ላይ ትወድቃለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

6በማጎግም ላይ ሳይፈሩም በደሴቶች በሚቀመጡ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

7ቅዱሱም ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ይታወቅ ዘንድ አደርጋለሁ፥ ቅዱሱንም ስሜን ከእንግዲህ ወዲህ አላስረክስም፤ አሕዛብም እግዚአብሔር፥ የእስራኤል ቅዱስ፥ እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

8እነሆ፥ ይመጣል ይሆንማል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ያልሁት ቀን ይህ ነው።

9በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ይወጣሉ፥ የጦር መሣሪያዎችንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ አላባሽ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትንና ፍላጻዎችን፥ ጎመድንና ጦርንም ያቃጥላሉ፤ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል።

10በጦር መሣሪያው እሳትን ያነድዳሉ እንጂ እንጨትን ከምድረ በዳ አይወስዱም ከዱርም አይቈርጡም፤ የገፈፉአቸውንም ይገፍፋሉ የበዘበዙአቸውንም ይበዘብዛሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

11በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፥ የሚያልፉትንም ይከለክላል፤ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ይቀብራሉ፤ የሸለቆውንም ስም፡ ሐሞንጎግ፡ ብለው ይጠሩታል።

12ምድሩንም ያጸዱ ዘንድ የእስራኤል ቤት ሰዎች ሰባት ወር ይቀብሩአቸዋል፥

13የምድርም ሕዝብ ሁሉ ይቀብሩአቸዋል፥ በተመሰገንሁበትም ቀን ለክብር ይሆንላችኋል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

14ምድርንም ለማጽዳት በምድሩ ላይ ወድቀው የቀሩትን የሚቀብሩ፥ ዘወትር በምድሩ ላይ የሚዞሩትን ሰዎች ይቀጥራሉ፤ ከሰባት ወርም በኋላ ይመረምራሉ።

15በምድርም የሚዞሩት ያልፋሉ፤ የሰውንም አጥንት ቢያዩ፥ ቀባሪዎች በሐሞን ጎግ ሸለቆ እስኪቀብሩት ድረስ ምልክት ያኖሩበታል።

16ደግሞም የከተማይቱ ስም ሐሞና ይባላል። እንዲሁ ምድሪቱን ያጸዳሉ።

17አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለወፎች ሁሉና ለምድር አራዊት ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ ኑ፥ ተከማቹ፥ ሥጋንም ትበሉ ዘንድ ደምንም ትጠጡ ዘንድ በእስራኤል ተራሮች ላይ ወደማርድላችሁ መሥዋዕት፥ እርሱም ታላቅ መሥዋዕት፥ ከየስፍራው ሁሉ ተሰብሰቡ።

18የኃያላኑን ሥጋ ትበላላችሁ የምድርንም አለቆች፥ የአውራ በጎችንና የጠቦቶችን፥ የፍየሎችንና የወይፈኖችን፥ የባሳንን ፍሪዳዎች ሁሉ፥ ደም ትጠጣላችሁ።

19እኔም ከማርድላችሁ መሥዋዕት እስክትጠግቡ ድረስ ጮማ ትበላላችሁ እስክትሰክሩም ድረስ ደም ትጠጣላችሁ።

20በሰደቃዬም ከፈረሶችና ከፈረሰኞች፥ ከኃያላንና ከሰልፈኞች ሁሉ ትጠግባላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

21ክብሬንም በአሕዛብ መካከል አኖራለሁ አሕዛብም ሁሉ ያደርግሁትን ፍርዴን፥ በላያቸውም ያኖርኋትን እጄን ያያሉ።

22ከእንግዲህም ወዲያ የእስራኤል ቤት እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።

23አሕዛብም የእስራኤል ቤት በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ተማረኩ ያውቃሉ፤ ስለ በደሉኝ እኔም ፊቴን ከእነርሱ ስለ ሸሸግሁ፥ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ ሰጠኋቸው፥ እነርሱም ሁሉ በሰይፍ ወደቁ።

24እንደ ርኵሰታቸውም እንደ መተላለፋቸውም መጠን አደረግሁባቸው ፊቴንም ከእነርሱ ሸሸግሁ።

25ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁን የያዕቆብን ምርኮ እመልሳለሁ፥ ለእስራኤልም ቤት ሁሉ እራራለሁ፥ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀናለሁ።

26ማንም ሳያስፈራቸው በምድራቸው ተዘልለው በተቀመጡ ጊዜ ከአሕዛብም ዘንድ በመለስኋቸው ጊዜ ከጠላቶቻቸውም ምድር በሰበሰብኋቸው ጊዜ በብዙ አሕዛብም ፊት በተቀደስሁባቸው ጊዜ፥ እፍረታቸውንና የበደሉኝን በደላቸውን ሁሉ ይሸከማሉ።

28እኔም ወደ አሕዛብ አስማርኬአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ በዚያም ከእነርሱ አንድ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ አልተውም፥

29ፊቴንም ከእነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አልሸሽግም፤ መንፈሴን በእስራኤል ቤት ላይ አፍስሻለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

ማብራሪያ

39:1-10 እግዚአብሔር እጅግ ግድየለሾችና ደንዳና ኃጢአተኞችን ቅዱስ ስሙን ወይ በጽድቅ ቁጣው ወይ በምህረቱና በጸጋው ባለጠግነት ያስያውቃል። በጽዮን ላይ የተነሱ የጦር መሳሪያዎች አይሳካላቸውም። ይህ ትንቢት በመጨረሻዎቹ ዘመናት የሚፈጸም ቢሆንም፣ እርግጥ ነው። ጥቅም ላይ ከዋለው አነጋገር በመነሳት፣ የጎግ ሠራዊት በተአምር የሚጠፋ ይመስላል።

39:11-22

እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን ለመጠበቅ ያጠፋቸው ጠላቶች ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ነው! ታላቅ ድነት የተደረገባቸው ጊዜያት የመታደስ ጊዜያት መሆን አለባቸው። እያንዳንዱ ሰው ምድሪቱን ከነውር ለማንጻት በሚቻለው መጠን ሁሉ ሊረዳ ይገባል። ኃጢአት እያንዳንዱ ሰው ሊታገለው የሚገባ ጠላት ነው። በሕዝብ ሥራ ላይ የተሰማሩት፣ በተለይም ምድሪቱን የማንጻትና የማደስ ሥራ ላይ ያሉት፣ የጀመሩትን እስከመጨረሻው የሚያከናውኑና ሁልጊዜም በትጋት የሚሠሩ ሰዎች መሆን አለባቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV “Son of man, prophesy against Gog and say: ‘This is what the Sovereign Lord says: I am against you, O Gog, chief prince… English BCV “ኣታ ወዲ ሰብ፥ ንጎግ ተነበየሉ፤ እግዚኣብሄር ኣምላኽ ከምዙይ ይብል ኣሎ ኢልካውን ንገሮ፥ ኣታ ጎግ ሓለቓ ሞሳሕን ቶቤልን እኒሀኹ፥ ኣነ ኣብ ልዕሌኻ እየ። ትግርኛ GAZBIB Waaqayyo gooftaan,“Yaa mucaa namaa! Ati Goog irratti raajii dubbadhu!“Yaa Goog angafa Rosh, angafa Meshek, angafa Tubaa… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአንተ ወልደ ዕጓለ እመሕያው፡ ተነበይ ላዕላ ጎግ ወበል፦ ከመዝ ይቤ እግዚአብሔር እግዚእ፦ ናሁ አነ ላዕሌከ ጎግ መልአከ ወርእሰ ሞሳሕ ወቶቤል፤ giz GAZGAZ Waaqayyo gooftaan,“Yaa mucaa namaa! Ati Goog irratti raajii dubbadhu!“Yaa Goog angafa Rosh, angafa Meshek, angafa Tubaa… Afaan Oromoo BCV aksum “ኣታ ወዲ ሰብ፥ ንጎግ ተነበየሉ፤ እግዚኣብሄር ኣምላኽ ከምዙይ ይብል ኣሎ ኢልካውን ንገሮ፥ ኣታ ጎግ ሓለቓ ሞሳሕን ቶቤልን እኒሀኹ፥ ኣነ ኣብ ልዕሌኻ እየ። ትግርኛ AMHNIV “አንተ የሰው ልጅ ሆይ፤ በጎግ ላይ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የሞሳሕና የቶቤል ዋና አለቃ ጎግ ሆይ፤ ተነሥቼብሃለሁ፤ አማርኛ SWAHSUV Na wewe, mwanadamu, tabiri juu ya Gogu, useme, Bwana MUNGU asema hivi, Tazama, mimi ni juu yako, Ewe Gogu, mkuu wa Rosh… Kiswahili