ትንቢተ ሕዝቅኤል 37

AMHEVGአማርኛ28 ጥቅሶች5:20 አዳምጥ
አዳምጥ 5:20 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ አጥንቶችም በሞሉባት ሸለቆ መካከል አኖረኝ።

2በእነርሱም አንጻር በዙሪያቸው አሳለፈኝ፤ እነሆም፥ በሸለቆው ፊት እጅግ ብዙ ነበሩ፥ እነሆም፥ እጅግ ደርቀው ነበር።

3እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች በሕይወት ይኖራሉን? አለኝ። እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ፡ አልሁ።

4እርሱም እንዲህ አለኝ፦ በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር፡ እንዲህም በላቸው፦ እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ።

5ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ትንፋሽን አገባባችኋለሁ፥ በሕይወትም ትኖራላችሁ።

6ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

7እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፤ ስናገርም ድምፅ ሆነ፥ እነሆም፥ መናወጥ ሆነ፥ አጥንቶችም አጥንት ከአጥንት ጋር ተቀራረቡ።

8እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ ጅማት ነበረባቸው ሥጋም ወጣ ቁርበትም በላያቸው ተዘረጋ፥ ትንፋሽ ግን አልነበረባቸውም።

9እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስ ትንቢት ተናገር፥ ለነፋስም፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ፥ ከአራቱ ነፋሳት ዘንድ ና፥ እነዚህም የተገደሉት በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በልባቸው፡ በል፡ አለኝ።

10እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፥ ትንፋሽም ገባባቸው ሕያዋንም ሆኑ፥ እጅግም ታላቅ ሠራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።

11እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ፦ አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል ፈጽመንም ተቈርጠናል፡ ብለዋል።

12ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ እነሆ፥ መቃብራችሁን እከፍታለሁ፥ ከመቃብራችሁም አወጣችኋለሁ፥ ወደ እስራኤልም ምድር አገባችኋለሁ።

13ሕዝቤ ሆይ፥ መቃብራችሁን በከፈትሁ ጊዜ ከመቃብራችሁም ባወጣኋችሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

14መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁም አኖራችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ እንዳደረግሁም ታውቃላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

15የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

16አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ አንድ በትር ውሰድና፦ ለይሁዳና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ልጆች፡ ብለህ በላዩ ጻፍ፤ ሌላም በትር ውሰድና፦ የኤፍሬም በትር ለዮሴፍና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ቤት ሁሉ፡ ብለህ በላዩ ጻፍ።

17አንድ በትርም እንዲሆኑ አንዱን ከሁለተኛው ጋር ለአንተ አጋጥም፥ በእጅህም ውስጥ አንድ ይሁኑ።

18የሕዝብህም ልጆች፦ ይህ የምታደርገው ነገር ምን ማለት እንደሆነ አትነግረንምን? ብለው በተናገሩህ ጊዜ፥

19አንተ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን በትር ባልንጀሮቹንም የእስራኤልን ነገዶች እወስዳለሁ፥ ከእርሱም ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥማቸዋለሁ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም ውስጥ አንድ ይሆናሉ፡ በላቸው።

20የምትጽፍባቸውም በትሮች በዓይናቸው ፊት በእጅህ ውስጥ ይሆናሉ።

21አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የእስራኤልን ልጆች ከሄዱባቸው ከአሕዛብ መካከል እወስዳለሁ፥ ከስፍራም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም አመጣቸዋለሁ፤

22በምድርም ላይ በእስራኤል ተራሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደርጋቸዋለሁ፥ አንድ ንጉሥም በሁላቸው ላይ ይነግሣል፤ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፥ ከዚያ ወዲያም ሁለት መንግሥቶች ሆነው አይለዩም።

23ከዚያ ወዲያም በጣዖቶቻቸውና በርኵሰታቸው በመተላለፋቸውም ሁሉ አይረክሱም፥ ኃጢአትም ከሠሩባት ዓመፅ ሁሉ አድናቸዋለሁ አነጻቸውማለሁ፤ ሕዝብም ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።

24ባሪያዬም ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፤ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል፤ በፍርዴም ይሄዳሉ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል።

25አባቶቻችሁም በኖሩበት ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠኋት ምድር ይኖራሉ፤ እነርሱና ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸውም ለዘላለም ይኖሩባታል፤ ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል።

26የሰላምም ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደርጋለሁ፥ የዘላለምም ቃል ኪዳን ይሆንላቸዋል፤ እኔም እባርካቸዋለሁ አበዛቸውማለሁ መቅደሴንም ለዘላለም በመካከላቸው አኖራለሁ።

27ማደሪያዬም በላያቸው ላይ ይሆናል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።

28መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስራኤልን የምቀድሰው እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ አሕዛብ ያውቃሉ።

ማብራሪያ

37:1-14 የትኛውም የተፈጠረ ኃይል የሰውን አጥንት ወደ ሕይወት መመለስ አይችልም። ሕያው ሊያደርጋቸው የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ቆዳና ሥጋ አለበሳቸው፣ ከዚያም ንፋስ በእነዚህ አካላት ላይ እንዲነፍስ ታዘዘ፤ እነርሱም ወደ ሕይወት ተመለሱ። ንፋሱም የእግዚአብሔር መንፈስ ምሳሌ ሲሆን፣ ሕይወትን የሚሰጡ ኃይላቱን ይወክላል። ራእዩ ተስፋ የቆረጡ አይሁዶችን ለማበረታታት፣ ከምርኮ በኋላ ስለሚሆነው መመለሳቸውና አሁን ካለባቸው ረጅም ዘመን የዘለቀው መበተን ስለሚነሱበት ሁኔታ ለመተንበይ ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV The hand of the Lord was upon me, and he brought me out by the Spirit of the Lord and set me in the middle of a valley;… English BCV ኢድ እግዚኣብሄር ኣብ ልዕለይ ነበረት፤ እግዚኣብሄር ከዓ ብመንፈስ ኣውፅአኒ፤ ኣብ ማእኸል እታ ለሰ ድማ ኣንበረኒ፤ ንሳውን ኣዕፅምቲ መሊእዋ ነበረ። ትግርኛ GAZBIB Harki Waaqayyoo ana irra ture, innis hafuura Waaqayyootiin na fuudhee dachaa lafeen keessa guute tokko keessa na dhaabe. Afaan Oromoo BCV GIZ ወኮነት ላዕሌየ እደ እግዚአብሔር፡ ወአወጸአኒ መንፈስ እግዚአብሔር፡ ወአንበረኒ ማእክለ ገዳም፡ ወምሉእ ህየ አዕፅምተ ሰብእ። giz GAZGAZ Harki Waaqayyoo ana irra ture, innis hafuura Waaqayyootiin na fuudhee dachaa lafeen keessa guute tokko keessa na dhaabe. Afaan Oromoo BCV aksum ኢድ እግዚኣብሄር ኣብ ልዕለይ ነበረት፤ እግዚኣብሄር ከዓ ብመንፈስ ኣውፅአኒ፤ ኣብ ማእኸል እታ ለሰ ድማ ኣንበረኒ፤ ንሳውን ኣዕፅምቲ መሊእዋ ነበረ። ትግርኛ AMHNIV የእግዚአብሔር እጅ በላዬ ነበረ፤ እርሱም በእግዚአብሔር መንፈስ አወጣኝ፤ በሸለቆ መካከልም አኖረኝ፤ ሸለቆውም በዐጥንቶች ተሞልቶ ነበር። አማርኛ SWAHSUV Mkono wa Bwana ulikuwa juu yangu, naye akanichukua nje katika roho ya Bwana, akaniweka chini, katikati ya bonde; nalo l… Kiswahili