ኦሪት ዘጸአት 38

AMHNIVአማርኛ31 ጥቅሶች6:22 አዳምጥ
አዳምጥ 6:22 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከፍታው ሦስት ክንድ የሆነ የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠሩ፤ ርዝመቱ አምስት ክንድ፣ ወርዱ አምስት ክንድ የሆነ ባለ ዐራት ማእዘን ነበረ።

2ቀንዶቹና መሠዊያው አንድ ወጥ ይሆኑ ዘንድ በአራቱም ማእዘኖች ላይ አራት ቀንድ ሠሩ፣ መሠዊያውንም በናስ ለበጡት።

3ዕቃዎቹንም ሁሉ ይኸውም ምንቸቶቹን፣ መጫሪያዎቹን፣ መርጫ ጐድጓዳ ሳህኖቹን፣ ሜንጦዎቹንና የእሳት መያዣዎቹን ከናስ ሠሯቸው።

4ለመሠዊያውም ከጠርዝ በታች ሆኖ ከመሠዊያው ግማሽ ቁመት ላይ የሚሆን የናስ ፍርግርግ ማንደጃ ሠሩ።

5ለናሱ ፍርፍርግ ማንደጃ አራት ማእዘኖች መሎጊያዎቹን እንዲይዙ የናስ ቀለበቶችን ሠሩ።

6መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርተው በናስ ለበጧቸው።

7መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጐኖች ይሆኑ ዘንድ መሎጊያዎቹን በቀለበቶቹ ውስጥ አስገቧቸው፤ ውስጡንም ክፍት በማድረግ ከሳንቃዎች ሠሩት።

8የናስ መታጠቢያ ሳሕንና የናስ መቆሚያውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ከሚያገለግሉት ሴቶች መስተዋት ሠሩት።

9ቀጥሎም አደባባዩን ሠሩ፤ የደቡቡ ክፍል ርዝመት አንድ መቶ ክንድ ሲሆን፣ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ነበሩት፤

10ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ የናስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹ ላይ ዘንጎች ነበሩት።

11የሰሜኑም ክፍል ቁመቱ አንድ መቶ ክንድ ነበር፤ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ የናስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ነበሩት።

12የምዕራቡ ጫፍ ወርዱ አምሳ ክንድ ነበር፤ ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎች እንዲሁም የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ያሉት መጋረጃዎች ነበሩት።

13በፀሓይ መውጫ በኩል ያለው የምሥራቁም ጫፍ ወርዱ አምሳ ክንድ ነበር።

14ከሦስት ምሰሶዎችና ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆኑ መጋረጃዎች በአንድ በኩል ባለው መግቢያ ላይ ነበሩ፤

15ከሦስት ምሰሶዎችና ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ርዝመታቸው ዐሥራ አምስት ክንድ የሆኑ መጋረጃዎች በአደባባዩ መግቢያ በሌላው በኩል ነበሩ።

16በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች በሙሉ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ ነበሩ።

17የምሰሶዎቹ መቆሚያዎች ናስ ነበሩ፤ ኵላቦቹና በምሰሶዎቹ ላይ ያሉት ዘንጎች ከብር የተሠሩ ነበሩ፤ ጫፎቻቸውም በብር ተለብጠው ነበር፤ ስለዚህ የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎች ነበሯቸው።

18በአደባባዩ መግቢያ ላይ ያለው መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና የጥልፍ ባለሙያ ከጠለፈው፣ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበር፤ ቁመቱ ሃያ ክንድ፣ እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ከፍታው አምስት ክንድ ነበረ፤

19አራት ምሰሶዎችና አራት መቆሚያዎች ነበሩት፤ ኵላቦቻቸውና ዘንጎቻቸው የብር ሲሆኑ፣ ጫፎቻቸው በብር ተለብጠው ነበር።

20የማደሪያው ድንኳንና የአደባባዩ ዙሪያ ካስማዎች ሁሉ ከናስ የተሠሩ ነበሩ።

21ለማደሪያው ድንኳን፣ ይኸውም ለምስክሩ ድንኳን ሙሴ ባዘዘው፣ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት ሌዋውያኑ በጻፉት መሠረት የዕቃዎቹ ቍጥር ይህ ነው።

22ከይሁዳ ነገድ የሆር የልጅ ልጅ፣ የኡሪ ልጅ የሆነው ባስልኤል፣ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።

23ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ፣ ዕቅድ አውጭና የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በቀጭን በፍታ ጥልፍ ጠላፊ ነበር።

24ለመቅደሱ ሥራ ሁሉ ከመወዝወዙ ስጦታ በመቅደሱ ሰቅል መሠረት የዋለው ጠቅላላ ወርቅ ሃያ ዘጠኝ መክሊትና ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ።

25በቈጠራው ወቅት ተቈጥረው ከነበሩት ማኅበረሰብ የተገኘው ብር ለመቅደሱ ሰቅል አንድ መቶ መክሊትና አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሰቅሎች ነበሩ፤

26ከተቈጠሩት ጋር አብረው ከሆኑት ሃያና ከሃያ ዓመት በላይ የሆናቸው ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች የሰጡት እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በአንድ ሰው አንድ ቤካ ይኸውም ግማሽ ሰቅል ነበረ።

27አንድ መቶ የብር መክሊቶች የመቅደሱንና የመጋረጃዎቹን መቆሚያዎች ለመሥራት አገልግሎት ላይ ውለው ነበር፤ ይኸውም ከአንድ መቶ መክሊቶች አንድ መቶ መቆሚያዎች ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ መቆሚያ አንድ መክሊት ማለት ነው።

28አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ አምስት ሰቅሎችን ለምሰሶዎቹ ኵላቦች፣ የምሰሶዎቹን አናት ለመለበጥና ዘንጎቻቸውንም ለመሥራት አገልግሎት ላይ ውለው ነበር።

29ከመወዝወዙ ስጦታ የሆነው ናስ ሰባ መክሊትና ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።

30ለመገናኛው ድንኳን መግቢያ ለናስ መሠዊያው ከናስ መጫሪያው፣ ለዕቃዎቹም ሁሉ መቆሚያዎቹን ለመሥራት አገልግሎት ላይ አውለውት ነበር፤

31ለአደባባዩ ዙሪያ፣ ለመግቢያው እንዲሁም ለማደሪያው ድንኳን ካስማዎች ሁሉና ለአደባባዩ ዙሪያ ሁሉ እንዲሁ አገልግሎት ላይ አውለውት ነበር።

ማብራሪያ

38:1-8 በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ዘመናት ሁሉ፣ ከሌሎች ይልቅ ለእግዚአብሔር የበለጠ የተሰጡ፣ የእርሱን ሥርዓታት በመጠበቅ ይበልጥ ጸንተው የቆሙ፣ እና በእርሱ ምክንያት ሕጋዊ የሆኑ ነገሮችን እንኳ ለመተው ይበልጥ ፈቃደኞች የሆኑ ሰዎች ነበሩ። አንዳንድ ለእግዚአብሔር የተሰጡና ለማደሪያ ድንኳን አምልኮ ቀናተኞች የሆኑ ሴቶች፣ ቅንአታቸውን የገለጹት መስተዋቶቻቸውን በመለገስ ነበር፤ እነዚህም የተወለወሉ የናስ ሳህኖች ነበሩ። የመስታወት መስተዋቶች ከመሠራታቸው በፊት፣ እነዚህ ተመሳሳይ ዓላማዎችን ያገለግሉ ነበር።

ምዕራፍ 38። እዚህ ላይ የሚከተሉት ነገሮች ተዘግበዋል፦ I. የናስ መሠዊያ መሠራቱ (ቁ. 1-7) እና የመታጠቢያ ገንዳው (ቁ. 8)። II. የማደሪያው ድንኳን የሚቆምበትን አደባባይ ለመከለል መጋረጃዎች መዘጋጀታቸው (ቁ. 9-20)። III. ለማደሪያው ድንኳን ዝግጅት የተሰበሰበውና ጥቅም ላይ የዋለው ወርቅ፣ ብርና ናስ ማጠቃለያ (ቁ. 21፣ ወዘተ)።

ቁጥር 1-8። ቤዛሌል በአብዛኛው ከዓይን የተሰወረውንና እጅግ ውድ የሆነውን የወርቅ ሥራ በድንኳኑ ውስጥ ከጨረሰ በኋላ፣ አሁን ደግሞ ለሁሉም ክፍት የሆነውን አደባባይ ማዘጋጀት ቀጠለ። አደባባዩ በሁለት ነገሮች የተሟላ ነበር፤ ሁለቱም ከናስ የተሠሩ ነበሩ፦

I. የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ፣ ቁ. 1-7። በዚህ ላይ ሁሉም መሥዋዕቶቻቸው ይቀርቡ ነበር፤ ይህ መሠዊያም በመለኮታዊ ትእዛዝ ለዚህ ዓላማ የተቀደሰ በመሆኑ፣ በእርሱ ላይ በእምነት የሚቀርበውን ስጦታ ይቀድስ ነበር። ክርስቶስ ራሱ ለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕቱ መሠዊያ ነበር፤ ለምስጋና መሥዋዕቶቻችንም ሁሉ እርሱ መሠዊያ ነው። እኛ መሥዋዕቶቻችንን ስናቀርብ እርሱን ማየት አለብን፣ እግዚአብሔርም ሲቀበላቸው እርሱን እንደሚያይ ሁሉ።

II. ካህናት ለማገልገል ሲገቡ የሚታጠቡበትን ውኃ የሚይዝ መታጠቢያ ገንዳ፣ ቁ. 8። ይህም በክርስቶስ ወንጌል ውስጥ ነፍሳችንን ከኃጢአት ሥነ ምግባራዊ ብክለት በክርስቶስ የደም ዋጋና ጸጋ ለማንጻት የተደረገውን ዝግጅት ያመለክታል። ይህም ቅዱስ እግዚአብሔርን በቅዱስ አገልግሎት ለማገልገል እንድንችል ነው። ይህ መታጠቢያ ገንዳ የተሠራው በማደሪያው ድንኳን በር ላይ ይሰበሰቡ ከነበሩት ሴቶች መስተዋቶች (ወይም መስታወቶች) እንደሆነ እዚህ ላይ ተገልጿል።

1. እነዚህ ሴቶች በአምልኮታቸው የላቁና ምሳሌ የሚሆኑ ይመስላል፤ ከሌሎች ይልቅ በአደባባይ የአምልኮ ስፍራ በተደጋጋሚና በቁም ነገር ይገኙ ነበር፤ ይህ ደግሞ ለክብራቸው እዚህ ላይ ተጠቅሷል። ከብዙ ጊዜ በኋላ ሐና እንዲህ ያለች ነበረች፤ እርሷም ከመቅደስ አትለይም ነበር፣ ነገር ግን በቀንና በሌሊት በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን ታገለግል ነበር፣ ሉቃስ 2:37። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በእያንዳንዱ ዘመን በቁም ነገር ባለው ቀናተኛ እግዚአብሔርን በመፍራት ራሳቸውን የለዩ ሰዎች የነበሩ ይመስላል፤ በዚህም ራሳቸውን ለይተዋል፤ ምክንያቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሴቶች በእርግጥ የተከበሩ ሴቶች ናቸው (የሐዋርያት ሥራ 13:50)፣ በኋለኛው ዘመን በሚሳለቁ ሰዎች ሞኞች ተብለው ቢጠሩም ክብራቸው አይቀንስም። ምናልባት እነዚህ ሴቶች በዚህ አጋጣሚ ለማደሪያው ድንኳን አገልግሎት እየተካሄደ ባለው ሥራ በመርዳት ቅንዓታቸውን ያሳዩ ነበሩ። በቡድን ይሰበሰቡ ነበር፤ ቃሉ እንዲህ ይላል፤ በዚህ መልካም ሥራ ብዙዎችን፣ እነርሱንም በጣም ቀናተኞችና አንድ ልብ የሆኑትን ማየት የተባረከ እይታ ነው።

2. እነዚህ ሴቶች መስተዋቶቻቸውን (ለዚሁ ዓላማ የተወለወለ እጅግ በጣም ጥሩ ናስ የነበሩትን) ለማደሪያው ድንኳን አገልግሎት ሰጡ። የራሳቸውን ውበት የሚያደንቁ፣ የራሳቸውን ጥላ የሚወዱ፣ እና ልብስ መልበስን ዋነኛ ጌጣቸው አድርገው ራሳቸውን የሚገመግሙና የሚያስተዋውቁ ሴቶች መስተዋቶቻቸውን ለመተው ይቸገራሉ፤ ሆኖም እነዚህ ሴቶች መስተዋቶቻቸውን ለእግዚአብሔር አቀረቡ፣ ወይ (1.

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆን መሠዊያን ከግራር እንጨት አደረገ፤ አራት ማዕዘንም ነበረ፤ ከፍታው ሦስት ክንድ ነበረ። አማርኛ ENGNIV They built the altar of burnt offering of acacia wood, three cubits high; it was square, five cubits long and five cubi… English BCV ብዕንፀይቲ ሰራው ገይሩ፥ ሓሙሽተ እመት ዝምንዋሑ፥ ሓሙሽተ እመት ዝምግፋሑ፥ መስዋእቲ ዝቃፀለሉ መሰውኢ ገበረ። እቲ መሰውኢ ኣርባዕተ መኣዝን ነበረ፤ ምብራኹ ድማ ሰለስተ እመት ነበረ። ትግርኛ GAZBIB Bazaali'el itti fufee muka laaftoo irraa iddoo aarsaa dheerinni isaa dhundhuma shan, bal'inni isaa dhundhuma shan, irra… Afaan Oromoo BCV GIZ ወገብረ ምሥዋዐ ለመሥዋዕት እምዕፅ ዘኢይነቅዝ ዘኅምስቱ በእመት ኑኁ፡ ወኅምስቱ ራኅቡ፡ ርቡዐ ኮነ፡ ወሥልሰ በእመት ቆመ። giz GAZGAZ Bazaali'el itti fufee muka laaftoo irraa iddoo aarsaa dheerinni isaa dhundhuma shan, bal'inni isaa dhundhuma shan, irra… Afaan Oromoo BCV aksum ብዕንፀይቲ ሰራው ገይሩ፥ ሓሙሽተ እመት ዝምንዋሑ፥ ሓሙሽተ እመት ዝምግፋሑ፥ መስዋእቲ ዝቃፀለሉ መሰውኢ ገበረ። እቲ መሰውኢ ኣርባዕተ መኣዝን ነበረ፤ ምብራኹ ድማ ሰለስተ እመት ነበረ። ትግርኛ SWAHSUV Kisha akafanya hiyo madhabahu ya sadaka ya kuteketezwa, ya mti wa mshita urefu wake ulikuwa dhiraa tano, na upana wake … Kiswahili