ወደ ኤፌሶን 3

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች3:08 አዳምጥ
አዳምጥ 3:08 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በዚህም ምክንያት እኔ ጳውሎስ ለእናንተ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ሆኛለሁ።

2ለእናንተ ጥቅም ሲባል ስለ ተሰጠኝ የእግዚአብሔር ጸጋ መጋቢነት በርግጥ ሰምታችኋል፤

3ቀደም ሲል በአጭሩ እንደ ጻፍሁት፣ በመገለጥ እንዳውቀው የተደረገው ምስጢር ይህ ነው።

4እንግዲህ ይህን ስታነቡ፣ የክርስቶስን ምስጢር እንዴት እንደ ማስተውል ለመረዳት ትችላላችሁ።

5ይህም ምስጢር አሁን ለቅዱሳኑ ሐዋርያትና ነቢያት የተገለጠውን ያህል ባለፉት ዘመናት ለነበሩ ሰዎች አልተገለጠም ነበር።

6ይህም ምስጢር አሕዛብ በወንጌል አማካይነት ከእስራኤል ጋር አብረው ወራሾች፣ አብረው የአንዱ አካል ብልቶች እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነው ተስፋ አብረው ተካፋይ መሆናቸው ነው።

7እኔም በኀይሉ አሠራር በተሰጠኝ በእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ የዚህ ወንጌል አገልጋይ ሆኛለሁ።

8ምንም እንኳ ከቅዱሳን ሁሉ ያነስሁ ብሆንም፣ የማይመረመረውን የክርስቶስን ባለጠግነት ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ ይህ ጸጋ ለእኔ ተሰጠኝ።

9እንዲሁም ሁሉን በፈጠረ በእግዚአብሔር ላለፉት ዘመናት የተሰወረውን የዚህን ምስጢር አሠራር ለሁሉም እገልጥ ዘንድ ተሰጠኝ።

10አሳቡም በአሁኑ ዘመን በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ብዙ ገጽታ ያለው የእግዚአብሔር ጥበብ በሰማያዊ ስፍራ ላሉት አለቆችና ባለ ሥልጣናት ይታወቅ ዘንድ ነው፤

11ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን በፈጸመው ዘላለማዊ ዕቅዱ መሠረት ነው።

12በእርሱና በእርሱ ላይ ባለን እምነት አማካይነት፣ በነጻነትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን።

13ስለዚህ ክብራችሁ በሆነው ስለ እናንተ በደረሰብኝ መከራ ተስፋ እንዳትቈርጡ ዐደራ እላችኋለሁ።

14በዚህም ምክንያት በአብ ፊት እንበረከካለሁ፤

15ከእርሱም በሰማይና በምድር ያለ ቤተ ሰብ ሁሉ ስያሜ ያገኛል።

16በውስጥ ሰውነታችሁ እንድትጠነክሩ፣ ከክብሩ ባለጠግነት በመንፈሱ በኩል ኀይል እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤

17ይኸውም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲያድር ነው። ደግሞም ሥር ሰዳችሁ፣ በፍቅር ታንጻችሁ፣

18የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር የመገንዘብ ኀይልን እንድታገኙ ነው።

19እስከ እግዚአብሔር ሙላት ሁሉ ልክ ደርሳችሁ እንድትሞሉ፣ ከመታወቅ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር ታውቁም ዘንድ ነው።

20እንግዲህ በእኛ ውስጥ እንደሚሠራው እንደ ኀይሉ መጠን፣ ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው፣

21በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በዘመናት ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን፤ አሜን።

ማብራሪያ

3:1-7 የእውነትን ትምህርት ስለሰበከ ሐዋርያው እስረኛ ነበርና፤ ነገር ግን እርሱ የኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ ነበር። ስለ እርሱ በዚህ መንገድ ሲሰቃይ ሳለ፣ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ የተደረገለት ነበር። የወንጌል ጸጋ የተሞሉ ጥሪዎች ሁሉ እንዲሁም የሚይዘው የምስራች ሁሉ የሚመነጩት ከእግዚአብሔር ባለጠጋ ጸጋ ነው። ይህ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ነፍሳት ውስጥ ጸጋን የሚያደርግበት ዋነኛው መንገድ ነው። ምስጢሩም በክርስቶስ በኩል የሚገኘው የመዳን ስውርና የተደበቀ ዓላማ ነው። ይህ ከአዲስ ኪዳን ነቢያት እንደተገለጠው ያህል፣ ከክርስቶስ በፊት በነበሩት ዘመናት በሙሉና በግልጽ አልተገለጸም ነበር። ይህ ሐዋርያው የተገለጠለት ታላቅ እውነት ነበር፤ እግዚአብሔር አሕዛብን በክርስቶስ በማመን ወደ መዳን እንደሚጠራቸው። መለኮታዊ ኃይል ሙሉ በሙሉ የሚሰራው ስራ ከመለኮታዊ ጸጋ ስጦታዎች ጋር አብሮ ይመጣል። እግዚአብሔር ጳውሎስን ለዚህ አገልግሎት እንደሾመው ሁሉ፣ ለእርሱም አበቃው።

3:8-12 እግዚአብሔር ለክብር አገልግሎት የሚያስገባቸውን በራሳቸው ዓይን ትሑት ያደርጋቸዋል። እግዚአብሔር ትሑት ለመሆን ጸጋ በሚሰጥበትም ስፍራ የሚያስፈልገውን ሌላ ጸጋ ሁሉ ይሰጣል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6