ወደ ቆላስይስ 2

AMHNIVአማርኛ23 ጥቅሶች3:54 አዳምጥ
አዳምጥ 3:54 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት እንዲሁም በአካል አይተውኝ ስለማያውቁ ሁሉ ምን ያህል እየተጋደልሁ እንደሆነ እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤

2ደግሞም ልባቸው እንዲጽናናና በፍቅር እንዲተሳሰሩ፣ ፍጹም የሆነውን የመረዳት ብልጥግና አግኝተው የእግዚአብሔር ምስጢር የሆነውን ክርስቶስን እንዲያውቁ እተጋለሁ፤

3የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የሚገኘው በእርሱ ዘንድ ነውና።

4ማንም ንግግር በማሳመር እንዳያታልላችሁ ይህን እነግራችኋለሁ።

5ምንም በሥጋ ከእናንተ ርቄ ብገኝ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና በሥርዐት መኖራችሁንና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል።

6እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት እንዲሁ በእርሱ ኑሩ፤

7በእርሱ ተተክላችሁና ታንጻችሁ፣ እንደ ተማራችሁት በእምነት ጸንታችሁ፣ የተትረፈረፈ ምስጋና እያቀረባችሁ ኑሩ።

8በክርስቶስ ላይ ሳይሆን፣ በሰዎች ልማድና በዚህ ዓለም መሠረታዊ ሕግጋት ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማግባቢያ ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።

9የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና፤

10እናንተም የገዥነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሙሉ ሆናችኋል።

11በእርሱ ሆናችሁ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ ተገረዛችሁ፤ በክርስቶስም መገረዝ የሥጋን ኀጢአታዊ ባሕርይ አስወገዳችሁ፤

12በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፣ እርሱን ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር ኀይል በማመን ከእርሱ ጋር ደግሞ ተነሣችሁ።

13እናንተም በበደላችሁና የሥጋችሁን ኀጢአታዊ ባሕርይ ባለመገረዝ ሙታን ሳላችሁ፣ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አደረጋችሁ፤ ኀጢአታችንንም ሁሉ ይቅር አለን፤

14ሲቃወመንና ሲጻረረን የነበረውን የዕዳ ጽሕፈት ከነሕግጋቱ በመደምሰስ፣ በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው።

15የአለቆችንና የባለሥልጣናትንም ማዕረግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ።

16እንግዲህ በምትበሉትም ሆነ በምትጠጡት ወይም በዓልን፣ ወር መባቻንና ሰንበትን በማክበር ነገር ማንም አይፍረድባችሁ፤

17እነዚህ ሊመጡ ላሉ ነገሮች ጥላ ናቸውና፤ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።

18ዐጒል ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ የሚወድ ማንም ሰው እንዳያደናቅፋችሁ ተጠንቀቁ። እንደዚህ ያለ ሰው ስላየው ራእይ ከመጠን በላይ ራሱን እየካበ በሥጋዊ አእምሮው ከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይታበያል፤

19ይህ ሰው፣ አካል ሁሉ በጅማትና በማሰሪያ እየተጋጠመ ምግብንም እየተቀበለ እግዚአብሔር በሚሰጠው ማደግ ከሚያድግበት ራስ ከሆነው ጋር ግንኙነት የለውም።

20ለዚህ ዓለም መርሕ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ ታዲያ ለምን እንደዚህ ዓለም ሰው ለሕጎቹ ተገዥ ትሆናላችሁ?

21“አትያዝ! አትቅመስ! አትንካ!” እንደሚሉት ዐይነት፣

22እነዚህ ሁሉ በሰው ትእዛዝና ትምህርት ላይ የተመሠረቱ ስለሆኑ በተግባር ላይ ሲውሉ ጠፊ ናቸው።

23እነዚህ ነገሮች በገዛ ራስ ላይ ከሚፈጥሩት የአምልኮ ስሜት፣ ከዐጒል ትሕትናና ሰውነትን ከመጨቈን አንፃር በርግጥ ጥበብ ያለባቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሥጋን ልቅነት ለመቈጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም።

ማብራሪያ

፪፥፩-፯ ነፍስ የምትበለጽገው በኢየሱስ እንዳለችው የእውነት ግልጽ እውቀት ሲኖረን ነው። በልብ ከማመን ባሻገር፣ ስንጠራ በአፍ ለመመስከር ዝግጁ ስንሆን ጭምር ነው። እውቀትና እምነት ነፍስን ያበለጽጋሉ። እምነታችን በጠነከረ ቁጥር፣ ፍቅራችንም በሞቀ መጠን፣ መጽናናታችንም ይበልጥ ይጨምራል። የጥበብ ውድ ሀብቶች ከእኛ ሳይሆን፣ ለእኛ በክርስቶስ ተደብቀዋል። እነዚህ በትዕቢተኞች ከማያምኑ ሰዎች ተደብቀው የነበሩ ሲሆን፣ በክርስቶስ ማንነትና ቤዛነት ግን ተገልጠዋል። አሳሳች ቃላት የሚያስከትሉትን አደጋ ተመልከቱ፤ ስንቶች በተሳሳተ ማድበስበስ እና በክፉ መርሆችና በኃጢአተኛ ምግባሮች ውብ መልክ ይበላሻሉ! ወደ የትኛውም ክፉ ነገር ሊያሳስቱ ከሚሹ ሰዎች ተጠንቀቁና ፍሩ፤ ምክንያቱም እነርሱ ሊያበላሹአችሁ ነውና። ሁሉም ክርስቲያኖች፣ ቢያንስ በቃል ደረጃ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ተቀብለዋል፣ ተስማምተውበታል እንዲሁም የራሳቸው አድርገው ወስደውታል። በክርስቶስ ልንታነጽ ወይም በእርሱ ልናድግ አንችልም፣ በመጀመሪያ በእርሱ ሥር ካልሰደድን ወይም በእርሱ ላይ ካልተመሠረትን በቀር። በእምነት ጸንተን፣ በእርሱ መትረፍ እና ይበልጥ እያደግን መሄድ አለብን። ይህን በረከት በምስጋና ከማይቀበሉት፣ እግዚአብሔር በጽድቅ ይነጥቃል፤ ስለ ምሕረቶቹም ምስጋና በእግዚአብሔር ዘንድ በጽድቅ የሚፈለግ ነው።

ቍጥር ፪፥፰-፲፯

የማመዛዘን ችሎታችንን በአግባቡ የምታንቀሳቅስ ፍልስፍና አለች፤ ይህም የእግዚአብሔርን ሥራዎች ማጥናት ሲሆን ወደ እግዚአብሔር እውቀት የምትመራንና በእርሱም ያለንን እምነት የምታጸናልን ናት። ነገር ግን ከንቱና አታላይ የሆነ ፍልስፍናም አለ፤ ይህ ፍልስፍና የሰዎችን ምናብ የሚያስደስት ቢሆንም፣ እምነታቸውን ግን ያደናቅፋል፦ ለምሳሌ ከእኛ በላይ ስላሉ ነገሮች ወይም ምንም በማይመለከቱን ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ የማወቅ ጉጉት የተሞሉ ግምቶች ናቸው። በዓለም መንገድ የሚሄዱ ሰዎች ክርስቶስን ከመከተል ይርቃሉ።

በእርሱ የሥርዓት ሕጉ ጥላዎች ሁሉ ፍሬ ነገር አለን። የሕጉ ጉድለቶች ሁሉ በክርስቶስ ወንጌል፣ በኃጢአት ምክንያት ባደረገው ፍጹም መስዋዕትነትና በእግዚአብሔር ፈቃድ መገለጥ ሙሉ በሙሉ ተሟልተዋል። ፍጹም መሆን ማለት ለመዳን አስፈላጊ በሆኑ ነገሮች ሁሉ መሟላት ማለት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ፊቴንም በሥጋ ስላላዩት ሁሉ እንዴት ያለ ትልቅ መጋደል እንዳለኝ ልታውቁ እወዳለሁና። አማርኛ ENGNIV I want you to know how much I am struggling for you and for those at Laodicea, and for all who have not met me personal… English BCV ምእንታኻትኩምን ምእንቲ እቶም ኣብ ሎዶቅያ ዘለዉን፥ ምእንቲ እቶም ገፀይ ብስጋ ሪኦም ዘይፈልጡን፥ ከመይ ዝበለ ዓብዪ ገድሊ ኸም ዘለኒ፥ ክትፈልጡ እደሊ ኣለኹ። ትግርኛ GAZBIB Ani isinii fi warra Laa'odiiqeyaatiif akkasumas warra fuula koo hin argin hundumaaf attam guddisee akkan dhama'aa ture … Afaan Oromoo BCV GIZ ወእፈቅድ ታእምሩ መጠነ እትጋደል በእንቲኣክሙ ወበእንተ እለ በሎዶቅያ ወበእንተ ኵሎሙ እለ ኢርእዩኒ ገጽየ በሥጋየ። giz GAZGAZ Ani isinii fi warra Laa'odiiqeyaatiif akkasumas warra fuula koo hin argin hundumaaf attam guddisee akkan dhama'aa ture … Afaan Oromoo BCV aksum ምእንታኻትኩምን ምእንቲ እቶም ኣብ ሎዶቅያ ዘለዉን፥ ምእንቲ እቶም ገፀይ ብስጋ ሪኦም ዘይፈልጡን፥ ከመይ ዝበለ ዓብዪ ገድሊ ኸም ዘለኒ፥ ክትፈልጡ እደሊ ኣለኹ። ትግርኛ SWAHSUV Maana nataka ninyi mjue jinsi ilivyo kuu juhudi yangu niliyo nayo kwa ajili yenu, na kwa ajili ya wale wa Laodikia, na … Kiswahili