የሐዋርያት ሥራ 20

AMHNIVአማርኛ38 ጥቅሶች6:37 አዳምጥ
አዳምጥ 6:37 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ሁከቱም እንደ በረደ፣ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርትን አስጠርቶ መከራቸው፤ ተሰናበቶአቸውም ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣ።

2ባለፈባቸውም ስፍራዎች ሕዝቡን በብዙ ቃል እየመከረ ግሪክ አገር ደረሰ፤

3በዚያም ሦስት ወር ተቀመጠ። ወደ ሶርያ በመርከብ ለመሄድ ሲዘጋጅም አይሁድ አሢረውበት ስለ ነበር፣ በመቄዶንያ በኩል አድርጎ ለመመለስ ወሰነ።

4የጳይሮስ ልጅ የቤርያው ሱሲጳጥሮስ፣ የተሰሎንቄዎቹ አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ከእስያ አውራጃ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ፣ እንዲሁም ጢሞቴዎስ አብረውት ሄዱ።

5እነዚህም ሰዎች ወደ ፊት ቀድመውን በጢሮአዳ ጠበቁን።

6እኛ ግን፣ የቂጣ በዓል ካለፈ በኋላ፣ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሣን፤ ከአምስት ቀንም በኋላ ከሌሎቹ ጋር በጢሮአዳ ተገናኘን፤ በዚያም ሰባት ቀን ተቀመጥን።

7በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቊረስ ተሰብስበን ሳለን፣ ጳውሎስ በማግስቱ ለመሄድ ስላሰበ፣ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር፤ ንግግሩንም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አራዘመ።

8በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራት ነበር።

9አውጤኪስ የተባለ አንድ ጐበዝም በመስኮት ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ፣ እንቅልፍ እንቅልፍ አለውና ጭልጥ ብሎ ተኛ፤ ከሦስተኛውም ፎቅ ቊልቊል ወደቀ፤ ሞቶም አነሡት።

10ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ተጋድሞ ዐቀፈውና፣ “ሕይወቱ በውስጡ ስላለች ሁከት አትፍጠሩ” አላቸው።

11ተመልሶም እንደ ገና ወደ ፎቁ ወጣ፤ እንጀራውንም ቈርሶ በላ፤ እስኪነጋም ድረስ ብዙ ከተናገረ በኋላ ተነሥቶ ሄደ።

12ሰዎችም ያን ጐበዝ ሕያው ሆኖ ወሰዱት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ።

13እኛ ግን ጳውሎስን ለመቀበል ቀድመን ወደ መርከቡ ሄድን፤ ከዚያም በመርከብ ወደ አሶን ተጓዝን፤ ይህን ያደረግነውም ጳውሎስ በየብስ በእግሩ ሊሄድ ስላሰበ ነበር።

14በአሶን ከተገናኘንም በኋላ፣ ተቀብለነው አብረን በመርከብ ወደ ሚጢሊኒ ሄድን።

15በማግስቱም በመርከብ ተጒዘን ከኪዩ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን።

16ጳውሎስም በእስያ አውራጃ ብዙ መቈየት ስላልፈለገ፣ ወደ ኤፌሶን ሳይገባ ዐልፎ ለመሄድ ወሰነ፤ ቢቻል በዓለ ኀምሳን በኢየሩሳሌም ለመዋል ቸኵሎ ነበርና።

17ከሚሊጢንም ወደ ኤፌሶን ሰው ልኮ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሽማግሌዎች አስጠራ፤

18በመጡም ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ አውራጃ ከገባሁባት ከመጀመሪያዋ ዕለት አንሥቶ ዘወትር ከእናንተ ጋር እንዴት እንደኖርሁ ታውቃላችሁ።

19ምንም እንኳ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ መከራ ቢያደርሱብኝም፣ ጌታን በታላቅ ትሕትናና በእንባ ከማገልገል አልተቈጠብሁም፤

20በአደባባይም ሆነ ከቤት ቤት በመዘዋወር፣ እናንተን ከማስተማርና ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብሁትን ከመስበክ ወደ ኋላ አላልሁም።

21በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ።

22“አሁንም እዚያ ስደርስ የሚደርስብኝን ባላውቅም፣ መንፈስ ቅዱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንድሄድ ግድ እያለኝ ነው።

23ነገር ግን በምሄድባቸው ከተሞች ሁሉ እስራትና መከራ እንደሚጠብቀኝ መንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።

24ይሁን እንጂ ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን ሩጫዬንና የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎቴን ብፈጽም፣ ለእኔ ሕይወቴ ከምንም እንደማይቈጠር እንደ ከንቱ ነገር ናት።

25“አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ።

26ስለዚህ ከሰው ሁሉ ደም ንጹሕ መሆኔን በዚች ቀን እመሰክርላችኋለሁ፤

27የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ የተቈጠብሁበት ጊዜ የለምና።

28ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።

29እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ነጣቂ ተኵላዎች መጥተው በመካከላችሁ ሰርገው እንደሚገቡና ለመንጋውም እንደማይራሩ ዐውቃለሁ።

30ከእናንተው መካከል እንኳ የራሳቸውን ደቀ መዛሙርት ለማፍራት እውነትን የሚያጣምሙ ይነሣሉ።

31ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ሦስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን ምንም ያህል ሳላቋርጥ በእንባ እያንዳንዳችሁን እንደ መከርኋችሁ አስታውሱ።

32“አሁንም ለእግዚአብሔር፣ እንዲሁም ሊያንጻችሁና በቅዱሳኑ ሁሉ መካከል ርስት ሊያወርሳችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ።

33የማንንም ብር ወይም ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም፤

34እነዚህ እጆቼ ለእኔና ከኔ ጋር ላሉት በሚያስፈልገን ነገር እንዳገለገሉን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።

35በጒልበታችን ደክመን ችግረኞችን መርዳት እንዳለብን ባደረግሁት ሁሉ አሳይቻችኋለሁ፤ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለውን የጌታ የኢየሱስን ቃል እናስታውስ።”

36ይህን ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋር ጸለየ።

37ሁሉም እጅግ አለቀሱ፤ ጳውሎስንም አንገቱን ዐቅፈው ሳሙት፤

38ከሁሉም በላይ ልባቸውን የነካው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቱን እንደማያዩ የተናገራቸው ቃል ነበር። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።

ማብራሪያ

20:1-6 ሁከት ወይም ተቃውሞ አንድን ክርስቲያን ከቦታው እንዲነሳ ወይም ዓላማውን እንዲቀይር ሊያስገድደው ይችላል፤ ነገር ግን ወደ የትም ቢሄድ ስራውና ደስታው ተመሳሳይ ይሆናል። ጳውሎስ ወደ ጢሮአስ ለመሄድ አምስት ቀናትን ማሳለፉን ዋጋ ያለው እንደሆነ አሰበ፣ እዚያ የሚቆየው ለሰባት ቀናት ብቻ ቢሆንም። ነገር ግን እርሱ ያውቅ ነበር፣ እኛም እንዲሁ ማወቅ አለብን፤ የጉዞን ጊዜ እንኳ እንዴት መዋጀት እንደሚቻል፣ እንዲሁም ለበጎ ነገር ማዋል እንደሚቻል።

፳፡፯-፲፪ ደቀ መዛሙርቱ በተናጠል ቢያነቡም፣ ቢያሰላስሉም፣ ቢጸልዩም፣ ቢዘምሩም፣ በዚህም ከእግዚአብሔር ጋር ህብረትን ቢያደርጉም፣ አሁንም እግዚአብሔርን ለማምለክ አንድ ላይ ተሰበሰቡ፣ በዚህም እርስ በእርሳቸው ህብረታቸውን ጠበቁ። በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣ በጌታ ቀን፣ ተሰብስበው ነበር። ይህ ቀን በክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ሁሉ በቅድስና ሊከበር ይገባል። እንጀራውን በመቁረስ፣ ስለ ኃጢአታችን መሥዋዕት እንዲሆን የክርስቶስ አካል መሰበር ብቻ ሳይሆን፣ ለነፍሳችን ምግብና ግብዣ እንዲሆን የክርስቶስ አካል ለእኛ መሰበርም ይወከላል። በቀድሞ ዘመን፣ በየጌታው ቀን የጌታን እራት መቀበል ልማድ ነበር፤ በዚህም የክርስቶስን ሞት መታሰቢያ ያደርጉ ነበር።

በዚህ ስብሰባ ጳውሎስ ሰበከ። የወንጌል ስብከት ከቅዱስ ቁርባን ጋር አብሮ መሄድ አለበት። እነርሱም ለመስማት ፈቃደኞች ነበሩ፤ እርሱም ይህን አይቶ፣ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ንግግሩን ቀጠለ። ቃሉን በሚሰሙበት ጊዜ መተኛት ክፉ ነገር ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ዝቅ አድርጎ የመመልከት ምልክት ነው። እንቅልፍ እንዳይወስደን የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን፤ ራሳችንን ወደ እንቅልፍ ሳንጥል፣ የምንሰማው ቃል ልባችንን እንዲነካ በማድረግ እንቅልፍን ከእኛ እንዲርቅ ማድረግ አለብን። ድካም ርኅራኄን ይጠይቃል፤ ንቀት ግን ጥብቅነትን ይጠይቃል።

የሐዋርያውን ስብከት ቢያቋርጥም፣ ስብከቱን ለማረጋገጥ ሆኖ ተገኘ። እውጢኮስም ወደ ሕይወት ተመለሰ። የጳውሎስን ኅብረት ዳግመኛ መቼ እንደሚያገኙ ስለማያውቁ፣ በተቻላቸው መጠን በአግባቡ ተጠቀሙበት፣ ለዚያ ዓላማ የአንድ ሌሊት እንቅልፍን ማጣት ትርጉም ያለው መስዋዕትነት እንደሆነ ቆጠሩት። ለጸሎትና ለአምልኮ ዓላማ የእረፍት ሰዓታት እምብዛም አይቋረጡም! ለቀላል መዝናኛ ወይም ለኃጢአተኛ ደስታ ግን ስንት ጊዜ ይቋረጣሉ! መንፈሳዊ ሕይወት በሰው ልብ ውስጥ እንዲያድግ እንዴት ከባድ ነው! ሥጋዊ ተግባራት ግን በዚያ እንዴት በተፈጥሮ ያብባሉ!

20:13-16 ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ተጣደፈ፣ ነገር ግን ከቦታ ወደ ቦታ ሲያልፍ፣ መልካም ሰው ሁሉ ማድረግ እንደሚገባው በመንገድ በጎ ለማድረግ ሞከረ። የእግዚአብሔርን ሥራ ስንሠራ፣ የእኛ ፈቃድና የጓደኞቻችን ፈቃድ ብዙ ጊዜ መሻር አለባቸው። ግዴታ ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲጠራን፣ ከእነርሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የለብንም።

፳፥፲፯-፳፯ ሽማግሌዎቹ ጳውሎስ ተንኮለኛ፣ ራስ ወዳድ ሰው አለመሆኑን ያውቁ ነበር። በየትኛውም አገልግሎት ጌታን በአግባቡ ለማገልገልና ለሌሎችም ጠቃሚ ለመሆን የሚሹ ሁሉ በትህትና ሊያደርጉት ይገባል። እርሱ ግልጽ አስተማሪ ነበር፤ መልእክቱን በሚገባ ሊገባ በሚችል መንገድ ይናገር ነበር።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6