1መልካም ሚስት ያለው ባል እንደምን የተባረከ ነው፤ ዕድሜውም በእጥፍ ይረዝማል።
2ጥሩ ሚስት ለባልዋ ደስታ ናት፤ ሕይወቱም ሰላም የሰፈነባት ትሆናለች።
3መልካም ሚስት እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ከተተው ድርሻዎች፤ ከሁሉም የላቀችው ናት።
4ሃብታም ሆኑ ድሀ፥ ልቦቻቸው በደስታ ይሞላሉ፤ በማንኛውም ወቅት ፊቶቻቸው የብርሃን ጸዳል ይለብሳሉ።
5ሦስት የሚያስደነግጡኝ ነገሮች አሉ፤ አራተኛውም ያስፈራኛል፤ በመላው ከተማ የሚነገር ሐሜት፤ የሕዝብ ሁከተትና የሐሰት ክስ፥ ከሞት የከፋ አስደንጋጭ ድርጊቶች ናቸው።
6በሴት የምትቀና ሴት ግን የልብ ቁስል ናት፤ ይህም የምላስ መቅሰፍት ነው።
7ክፉ ሚስት በትክክል እንደማይገጥም ቀምበር ናት፤ እርሷን ለመግራት መሞከር ጊንጥ እንደ መያዝ ነው።
8ጠጪ ሚስት እጅግ ታስቆጣለች፥ ውርደቷን ልትደብቅም አትችልም።
9የሴት ዘማዊነት በድፍረቷ ይታወቃል፤ ቅንድቧም ይመሰክርባታል።
10ከደፋሯ ሴት ልጅህን በሚገባ ጠብቅ፤ ካልሆነ ግን ምንም ከማድረግ አትመለስም።
11ኀፍረት የማያውቁ ዐይኖቿን ተከታተል፤ ብታዋርድህ አይድነቅህ።
12ጥም እንዳቃጠለው መንገደኛ አፏን ትከፍታለች፤ የገኘችውንም ውሃ ትጠጣለች፤ በየድንኳኑ ፊት ለፊት ትቀመጣለች፤ ለመጣው ፍላጻም ሰገባዋን ትከፍታለች።
13የሚስት ሞገስ ባልዋን ያስደስታል፤ አያያዟም ኃይልን ይሰጠዋል።
14ረጋ ያለች ሚስት የእግዚአብሔር ስጦታ ናት፤ መልካም አስተዳደግ በዋጋ አይተመንም።
15ትሑት ሚስት እጥፍ ትርፍ ናት፤ ከንጹሕ ባሕርይ በላይ የሚወደድ የለም።
16በእግዚአብሔር ተራሮች ላይ እንደምታብራው ፀሐይ ሁሉ፥ በጥሩ ቤት ውስጥ ያለ የመልካም ሴት ውበት እንዲሁ ነው።
17በመልካም ቁመና ላይ የሚታይ ቁንጅና፥ በተቀደሰ መቅረዝ ላይ እንደሚያበራ ፋኖስ ነው።
18ቀጥ ባሉ ተረከዞች ላይ የተሰኩ ውብ ባቶች፥ በብር መሠረት ላይ እንደተተከሉ የወርቅ ምሰሶዎች ናቸው።
28ልቤን የማያሳዝኑት ሁለት ነገሮች አሉ፤ ሦስተኛው ደግሞ ያስቆጣኛል። በድኀነቱ የተነሣ ወድቆ የሚቀር ጀግና፥ በጥላቻ ዐይን የሚታይ ጠቢብ፥ ከደግነት ወደ ኃጢአት ፊቱን የመሰለ ሰው፥ እግዚአብሔር ለአሰቃቂ ሞት መርጦታል።
29ነጋዴ ከስሕተት፥ አትራፊ ከኃጢአት ይነጻል ለማለት እጅጉን ይከብዳል።