2ኛ ተሰሎንቄ 1

AMHEVGአማርኛ9 ጥቅሶች1:59 አዳምጥ
አዳምጥ 1:59 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር በአባታችን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤

2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።

3ወንድሞች ሆይ፥ እምነታችሁ እጅግ ስለሚያድግ የሁላችሁም የእያንዳንዳችሁ ፍቅር እርስ በርሳችሁ ስለሚበዛ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግድ አለብን፤

4ስለዚህ በምትታገሱበት በስደታችሁና በመከራችሁ ሁሉ ከመጽናታችሁና ከእምነታችሁ የተነሣ በእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ስለ እናንተ ራሳችን እንመካለን።

5ስለ እርሱ ደግሞ መከራ ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት የምትበቁ ሆናችሁ ትቈጠሩ ዘንድ፥ ይህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ ምልክት ነው።

6ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፥ መከራን ለሚያሳዩአችሁ መከራን፥ መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና።

8እግዚአብሔርን የማያውቁትን፥ ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤

9በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር፥ ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊገረም ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኃይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።

11ስለዚህም ደግሞ እንደ አምላካችን እንደ ጌታም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእናንተ ዘንድ ሊከብር እናንተም በእርሱ ዘንድ ልትከብሩ፥ አምላካችን ለመጥራቱ የምትበቁ አድርጎ ይቈጥራችሁ ዘንድ፥ የበጎነትንም ፈቃድ ሁሉ የእምነትንም ሥራ በኃይል ይፈጽም ዘንድ ስለ እናንተ ሁልጊዜ እንጸልያለን።

ማብራሪያ

1:1-4 የጸጋ እውነት ባለበት ስፍራ፣ የእርሱም ጭማሪ ይኖራል። የጻድቅ መንገድ፣ እስከ ፍጹም ቀን ድረስ እየጨመረ እንደሚያበራ ብርሃን ነው። የጸጋም ጭማሪ ባለበት፣ ክብሩ ሁሉ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው። እምነት በሚያድግበት ስፍራ ፍቅር ይበዛል፤ እምነት በፍቅር ይሠራልና። ከእግዚአብሔር የሚመጡ መከራዎችና ከሰዎች የሚደርስ ስደት የእነዚያን ጸጋዎች ትግበራ በሚያፋጥኑበት ጊዜ፣ ለሌሎች ምሳሌ ሆኖ ሊቀርብ የሚችል እምነትንና ትዕግሥትን ያሳያል። ሐዋርያው የተመካባቸው ትዕግሥትና እምነት እነርሱን ደግፈው ሁሉንም መከራዎቻቸውን እንዲጸኑ አስችለዋቸዋልና።

1:5-10 ሃይማኖት ዋጋ ያላት ከሆነ፣ የሁሉንም ነገር ዋጋ ናት፤ ሃይማኖት የሌላቸው፣ ወይም ሊኖራቸው የማይገባ፣ ወይም እንዴት ማድነቅ እንዳለባቸው የማያውቁ ሰዎች፣ ስለርሷ ለመሰቃየት ልባቸው አይፈቅድላቸውም። በምንም ዓይነት መከራችን፣ እንዲሁም በአገልግሎታችን፣ መንግስተ ሰማይን መብቃት አንችልም፤ ነገር ግን በመከራ ውስጥ ባለን ትዕግስት፣ ለተስፋው ደስታ እንዘጋጃለን። ለዘላለማዊ ጥፋት ሰውን ከሚያመላክቱ ነገሮች ሁሉ እጅግ የላቀው ምልክት የእግዚአብሔርን ስምና ሕዝቡን ማሳደድና መጥላት ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚያስጨንቁትን ያስጨንቃቸዋል። ለእግዚአብሔር ሕዝብም ዕረፍት አለ፤ ይህም ከኃጢአትና ከሐዘን ዕረፍት ነው። የወደፊቱ ምንዳ እርግጠኛነት በእግዚአብሔር ጽድቅ የተረጋገጠ ነው። ይህን ማሰብ ለክፉዎች አስፈሪ ሲሆን፣ ለጻድቃን ግን ማጽናኛ ነው።

ታላቁን ቀን የሚመለከት እምነት፣ ለማያምኑት ግራ የሚያጋባ የሚመስለውን የእግዚአብሔርን አሳብ (አስተዳደር) በከፊል ለመረዳት ያስችለዋል። በዚያ ቀን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማይ ይገለጣል/ይታያል። በሰማያዊው ዓለም ክብርና ኃይል ይመጣል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6