2ኛ ቆሮንቶስ 1

AMHNIVአማርኛ24 ጥቅሶች4:35 አዳምጥ
አዳምጥ 4:35 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፤ በቆሮንቶስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ፤

2ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

3የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።

4እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።

5የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ የመብዛቱን ያህል መጽናናታችንም በክርስቶስ በኩል ይበዛልናል።

6መከራ ብንቀበል ስለ እናንተ መጽናናትና መዳን ነው። ብንጽናናም እኛ የተቀበልነውን መከራ በመቀበል በትዕግሥት እንድትጸኑ ስለ እናንተ መጽናናት ነው።

7ስለ እናንተ ያለን ተስፋ ጽኑ ነው፤ ምክንያቱም በመከራችን እንደ ተካፈላችሁ ሁሉ በመጽናናታችንም እንደምትካፈሉ እናውቃለን።

8ወንድሞች ሆይ፤ በእስያ ስለ ደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ በሕይወት ለመኖር እንኳ ተስፋ እስከምንቈርጥ ድረስ ከዐቅማችን በላይ የሆነ ጽኑ መከራ ደርሶብን ነበር።

9በርግጥም የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደብን ይሰማን ነበር፤ ይህም የሆነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንድንታመን እንጂ፣ በራሳችን እንዳንታመን ነው።

10እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደ ፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል።

11እናንተም በጸሎታችሁ ደግፉን፤ በብዙዎች ጸሎት ስለ ተሰጠን ስጦታ ብዙ ሰዎች ስለ እኛ ምስጋና ያቀርባሉ።

12እንግዲህ ትምክህታችን ይህ ነው፤ በዚህ ዓለም በተለይም ከእናንተ ጋር ባለን ግንኙነት፣ ከእግዚአብሔር በሆነ ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን ኅሊናችን ይመሰክራል፤ ይህም በሰው ጥበብ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ነው።

13ልታነቡት ወይም ልትረዱት የማትችሉትን ነገር አንጽፍላችሁም፤ ሁሉንም እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ።

14እናንተ በእኛ እንደምትመኩ ሁሉ እኛም በእናንተ እንደምንመካ አሁን የተረዳችሁን በከፊል ቢሆንም፣ በጌታ ኢየሱስ ቀን ሁሉን ትረዳላችሁ።

15በዚህ ርግጠኛ ስለ ነበርሁ በዕጥፍ እንድትጠቀሙ፣ በመጀመሪያ ልጐበኛችሁ ዐቅጄ ነበር።

16ወደ መቄዶንያ ስሄድ እግረ መንገዴን ልጐበኛችሁና ከመቄዶንያም በእናንተ በኩል ተመልሼ ወደ ይሁዳ ስሄድ በጒዞዬ እንድትረዱኝ ዐቅጄ ነበር።

17ይህን ሳቅድ በሚገባ ሳላስብ ያደረግሁት ይመስላችኋልን? ወይስ በዓለማዊ ልማድ አንዴ፣ “አዎን፣ አዎን” ወዲያው ደግሞ፣ “አይደለም፣ አይደለም” የምል ይመስላችኋልን?

18እግዚአብሔር ታማኝ እንደሆነ ሁሉ፣ ለእናንተ የምንናገረው ቃላችን፣ “አዎን” እና “አይደለም” ሊሆን አይችልም፤

19ምክንያቱም እኔም ሆንሁ ሲላስና ጢሞቴዎስ፣ እኛ የሰበክንላችሁ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ “አዎን” እና “አይደለም” አልነበረም፤ ነገር ግን በእርሱ ዘወትር፣ “አዎን” ነው።

20በእግዚአብሔር የተሰጡ ተስፋዎች ሁሉ፣ “አዎን” የሚሆኑት በእርሱ ነውና፤ እኛም በእርሱ አማካይነት ለእግዚአብሔር ክብር፣ “አሜን” የምንለው በዚህ ምክንያት ነው።

21እንግዲህ፣ እኛንም እናንተንም በክርስቶስ ጸንተን እንድንቆም የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው፤ የቀባንም እርሱ ነው፤

22የእርሱ ለመሆናችን ማኅተሙን ያተመብን ደግሞም ወደ ፊት ለምናገኘው ነገር የመንፈሱን ዋስትና በልባችን ያኖረ እርሱ ነው።

23ወደ ቆሮንቶስ ተመልሼ ያልመጣሁት እንዳላሳዝናችሁ ብዬ ነው፤ ይህ እውነት ካልሆነ እግዚአብሔር ይመስክርብኝ።

24ጸንታችሁ የምትቆሙት በእምነት ስለ ሆነ፣ ደስ እንዲላችሁ ከእናንተ ጋር እንሠራለን እንጂ በእምነታችሁ ላይ ለመሠልጠን አይደለም።

ማብራሪያ

1:1-11 በሚያስፈልገን ጊዜ የሚረዳ ጸጋን ለማግኘትና ምሕረትን እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንድንቀርብ እንበረታታለን። ጌታ ለተጨነቀ ህሊና ሰላምን ሊሰጥ፣ የነፍስንም የሚናደዱ ፍላጎቶች ሊያረጋጋ ይችላል። እነዚህ በረከቶች ቤዛነት ላገኛት ቤተሰቡ አባት በሆነው በእርሱ ይሰጣሉ። "ልባችሁ አይጨነቅ" የሚለው አዳኛችን ነው። ሁሉም መጽናናት ከእግዚአብሔር ይመጣሉ፤ ጣፋጭ መጽናናታችንም በእርሱ ነው። እርሱ የኃጢአትን ነፃ ስርየት በመስጠት ለነፍሳት ሰላምን ይናገራል፤ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሰጪ ተጽዕኖዎችና በጸጋው ባለ ጠጋ ምሕረቶች ያጽናናቸዋል። እርሱ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለመጠገን፣ በጣም የሚያምሙ ቁስሎችን ለመፈወስ፣ እንዲሁም በከባድ ሀዘኖች ውስጥ ተስፋና ደስታን ለመስጠት ይችላል። እግዚአብሔር የሚሰጠን ውለታዎች እኛን ደስተኛ ለማድረግ ብቻ ሳይሆኑ፣ ለሌሎችም ጠቃሚ እንድንሆን ነው። እርሱን በብቸኝነት ለሚታመኑና ለሚያገለግሉት ለመደገፍ በቂ መጽናናትን ይልካል። እኛ ሕይወትንም እንኳ ተስፋ እስከመቁረጥ ድረስ በጣም ዝቅ ብንልም፣ ከሞትም እንኳ መልሶ ማምጣት የሚችለውን እግዚአብሔርን አሁንም መታመን እንችላለን። ተስፋቸውና እምነታቸው በከንቱ አልነበረም፤ ጌታን የሚታመኑም አያፍሩም። ያለፉ ልምምዶች እምነትንና ተስፋን ያበረታታሉ፤ ወደፊትም እግዚአብሔርን እንድንታመን ግዴታ ውስጥ ያስገባሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ በአካይያ አገር ሁሉ ከሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ ጋር በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ አማርኛ ENGNIV Paul, an apostle of Christ Jesus by the will of God, and Timothy our brother, To the church of God in Corinth, together… English BCV ብፍቓድ እግዚኣብሄር፥ ሃዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስ ካብ ዝኾነ ጳውሎስን፥ ካብ ሓውና ጢሞቴዎስን፥ ናብታ ኣብ ቆሮንቶስ ዘላ ቤተ ክርስቲያን እግዚኣብሄርን፥ ምስቶም ኣብ ኵላ ሃገር ኣካይያ ዘለዉ … ትግርኛ GAZBIB Ani Phaawulos fedha Waaqayyootiin ergamaa Kristos Yesus kanan ta'e, Ximotewos obboleessaa wajjin, gara waldaa Waaqayyoo… Afaan Oromoo BCV GIZ እምጳውሎስ ሐዋርያሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃደ እግዚአብሔር ወጢሞቴዎስ እኁነ ለቤተ ክርስቲያን ዘማኅበረ እግዚአብሔር ዘሀገረ ቆሮንቶስ ወለኵሎሙ ቅዱሳን እለ ሀገረ አካይያ። giz GAZGAZ Ani Phaawulos fedha Waaqayyootiin ergamaa Kristos Yesus kanan ta'e, Ximotewos obboleessaa wajjin, gara waldaa Waaqayyoo… Afaan Oromoo BCV aksum ብፍቓድ እግዚኣብሄር፥ ሃዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስ ካብ ዝኾነ ጳውሎስን፥ ካብ ሓውና ጢሞቴዎስን፥ ናብታ ኣብ ቆሮንቶስ ዘላ ቤተ ክርስቲያን እግዚኣብሄርን፥ ምስቶም ኣብ ኵላ ሃገር ኣካይያ ዘለዉ … ትግርኛ SWAHSUV Paulo, mtume wa Kristo Yesu kwa mapenzi ya Mungu, na Timotheo ndugu yetu; kwa kanisa la Mungu lililoko Korintho, pamoja… Kiswahili