2ኛ ቆሮንቶስ 1

AMHEVGአማርኛ22 ጥቅሶች3:52 አዳምጥ
አዳምጥ 3:52 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ በአካይያ አገር ሁሉ ከሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ ጋር በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤

2ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

3የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።

4እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል፥ ስለዚህም እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን።

5የክርስቶስ ሥቃይ በእኛ ላይ እንደ በዛ፥ እንዲሁ መጽናናታችን ደግሞ በክርስቶስ በኩል ይበዛልናልና።

6ዳሩ ግን መከራ ብንቀበል፥ ስለ መጽናናታችሁና ስለ መዳናችሁ ነው፤ ብንጽናናም፥ እኛ ደግሞ የምንሣቀይበት በዚያ ሥቃይ በመጽናት ስለሚደረግ ስለ መጽናናታችሁ ነው።

7ተስፋችንም ስለ እናንተ ጽኑ ነው፤ ሥቃያችንን እንደ ተካፈላችሁ እንዲሁም መጽናናታችንን ደግሞ እንድትካፈሉ እናውቃለንና።

8በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤

9አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር።

10እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፥ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፥ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል።

12ትምክህታችን ይህ ነውና፤ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ሳይሆን፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ እንደኖርን የሕሊናችን ምስክርነት ነው።

13ከምታነቡትና ከምታስተውሉት በቀር ሌላ አንጽፍላችሁምና፤ በጌታችን በኢየሱስ ቀን እናንተ ደግሞ ትምክህታችን እንደምትሆኑ እንዲሁ ትምክህታችሁ እንድንሆን፥ በከፊል ስለ እኛ እንዳስተዋላችሁ ፈጽማችሁ ታስተውሉት ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ።

15በዚህም ታምኜ፥ ሁለተኛ ጸጋ ታገኙ ዘንድ አስቀድሜ ወደ እናንተ እንድመጣ፥

16በእናንተም መካከል ወደ መቄዶንያ እንዳልፍ ደግሞም ከመቄዶንያ ወደ እናንተ መጥቼ ወደ ይሁዳ በጉዞዬ እንድትረዱኝ አሰብሁ።

17እንግዲህ ይህን ሳስብ ያን ጊዜ ቅሌትን አሳየሁን? ወይስ በእኔ ዘንድ አዎን አዎን አይደለም አይደለም ማለት እንዲሆን ያን የማስበው በዓለማዊ ልማድ ነውን?

18እግዚአብሔር ግን የታመነ ነው፥ ለእናንተም የሚነገረው ቃላችን አዎንና አይደለም አይሆንም።

19በእኛ ማለት በእኔና በስልዋኖስ በጢሞቴዎስም በመካከላችሁ የተሰበከ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አዎንና አይደለም አልነበረም፥ ነገር ግን በእርሱ አዎን ሆኖአል።

20እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና፥ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስለ ክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው።

21በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥

22ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።

23እኔ ግን ልራራላችሁ ስል እንደ ገና ወደ ቆሮንቶስ እንዳልመጣሁ በነፍሴ ላይ እግዚአብሔርን ምስክር እጠራለሁ።

24ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን እንጂ፥ በእምነታችሁ በእናንተ ላይ የምንገዛ አይደለንም። በእምነታችሁ ቆማችኋልና።

ማብራሪያ

1:1-11 በሚያስፈልገን ጊዜ የሚረዳ ጸጋን ለማግኘትና ምሕረትን እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንድንቀርብ እንበረታታለን። ጌታ ለተጨነቀ ህሊና ሰላምን ሊሰጥ፣ የነፍስንም የሚናደዱ ፍላጎቶች ሊያረጋጋ ይችላል። እነዚህ በረከቶች ቤዛነት ላገኛት ቤተሰቡ አባት በሆነው በእርሱ ይሰጣሉ። "ልባችሁ አይጨነቅ" የሚለው አዳኛችን ነው። ሁሉም መጽናናት ከእግዚአብሔር ይመጣሉ፤ ጣፋጭ መጽናናታችንም በእርሱ ነው። እርሱ የኃጢአትን ነፃ ስርየት በመስጠት ለነፍሳት ሰላምን ይናገራል፤ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሰጪ ተጽዕኖዎችና በጸጋው ባለ ጠጋ ምሕረቶች ያጽናናቸዋል። እርሱ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለመጠገን፣ በጣም የሚያምሙ ቁስሎችን ለመፈወስ፣ እንዲሁም በከባድ ሀዘኖች ውስጥ ተስፋና ደስታን ለመስጠት ይችላል። እግዚአብሔር የሚሰጠን ውለታዎች እኛን ደስተኛ ለማድረግ ብቻ ሳይሆኑ፣ ለሌሎችም ጠቃሚ እንድንሆን ነው። እርሱን በብቸኝነት ለሚታመኑና ለሚያገለግሉት ለመደገፍ በቂ መጽናናትን ይልካል። እኛ ሕይወትንም እንኳ ተስፋ እስከመቁረጥ ድረስ በጣም ዝቅ ብንልም፣ ከሞትም እንኳ መልሶ ማምጣት የሚችለውን እግዚአብሔርን አሁንም መታመን እንችላለን። ተስፋቸውና እምነታቸው በከንቱ አልነበረም፤ ጌታን የሚታመኑም አያፍሩም። ያለፉ ልምምዶች እምነትንና ተስፋን ያበረታታሉ፤ ወደፊትም እግዚአብሔርን እንድንታመን ግዴታ ውስጥ ያስገባሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

ENGNIV Paul, an apostle of Christ Jesus by the will of God, and Timothy our brother, To the church of God in Corinth, together… English BCV ብፍቓድ እግዚኣብሄር፥ ሃዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስ ካብ ዝኾነ ጳውሎስን፥ ካብ ሓውና ጢሞቴዎስን፥ ናብታ ኣብ ቆሮንቶስ ዘላ ቤተ ክርስቲያን እግዚኣብሄርን፥ ምስቶም ኣብ ኵላ ሃገር ኣካይያ ዘለዉ … ትግርኛ GAZBIB Ani Phaawulos fedha Waaqayyootiin ergamaa Kristos Yesus kanan ta'e, Ximotewos obboleessaa wajjin, gara waldaa Waaqayyoo… Afaan Oromoo BCV GIZ እምጳውሎስ ሐዋርያሁ ለኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃደ እግዚአብሔር ወጢሞቴዎስ እኁነ ለቤተ ክርስቲያን ዘማኅበረ እግዚአብሔር ዘሀገረ ቆሮንቶስ ወለኵሎሙ ቅዱሳን እለ ሀገረ አካይያ። giz GAZGAZ Ani Phaawulos fedha Waaqayyootiin ergamaa Kristos Yesus kanan ta'e, Ximotewos obboleessaa wajjin, gara waldaa Waaqayyoo… Afaan Oromoo BCV aksum ብፍቓድ እግዚኣብሄር፥ ሃዋርያ ኢየሱስ ክርስቶስ ካብ ዝኾነ ጳውሎስን፥ ካብ ሓውና ጢሞቴዎስን፥ ናብታ ኣብ ቆሮንቶስ ዘላ ቤተ ክርስቲያን እግዚኣብሄርን፥ ምስቶም ኣብ ኵላ ሃገር ኣካይያ ዘለዉ … ትግርኛ AMHNIV በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፤ በቆሮንቶስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ፤ አማርኛ SWAHSUV Paulo, mtume wa Kristo Yesu kwa mapenzi ya Mungu, na Timotheo ndugu yetu; kwa kanisa la Mungu lililoko Korintho, pamoja… Kiswahili