2ኛ ቆሮንቶስ 13

AMHNIVአማርኛ14 ጥቅሶች2:38 አዳምጥ
አዳምጥ 2:38 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ መሆኑ ነው፤ “ማንኛውም ነገር በሁለት ወይም በሦስት ምስክር ይጸናል።”

2በሁለተኛው ጒብኝቴ እናንተ ዘንድ በነበርሁበት ጊዜ አስጠንቅቄአችሁ ነበር፤ አሁንም በሩቅ ሆኜ እንደ ገና አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ወደ እናንተም ተመልሼ ስመጣ ከዚህ በፊት ኀጢአት ለሠሩትም ሆነ ለሌሎች አልራራላቸውም፤

3ይህም የሚሆነው ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንደሚናገር ማስረጃ በመፈለጋችሁ ነው። እርሱም በመካከላችሁ ብርቱ እንጂ ደካማ አልነበረም።

4የተሰቀለው በድካም ቢሆንም፣ በእግዚአብሔር ኀይል ሕያው ሆኖ ይኖራል። እኛም በእርሱ ደካሞች ብንሆንም፣ እናንተን ለማገልገል ግን በእግዚአብሔር ኀይል ከእርሱ ጋር ሕያዋን ሆነን እንኖራለን።

5በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በስተቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?

6እኛ ግን ብቁ መሆናችንን እንደምትገነዘቡ ተስፋ አደርጋለሁ።

7አሁንም ምንም ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም እኛ ብቁዎች እንደሆንን ሰዎች እንዲያዩልን አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ምንም እንኳ ብቁዎች ባንሆንም እናንተ መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው።

8ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ማድረግ አንችልምና።

9እኛ ደካሞች ስንሆን፣ እናንተ ግን ብርቱዎች ስትሆኑ ደስ ይለናል፤ ጸሎታችንም እናንተ ፍጹማን እንድትሆኑ ነው።

10ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኀይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።

11በተረፈ ወንድሞች ሆይ፤ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሆኑ፤ ምክሬን ስሙ፤ አንድ ሐሳብ ይኑራችሁ፤ በሰላምም ኑሩ። የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።

12በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።

13ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

14የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

ማብራሪያ

13:1-6

ኃጢአተኞችን በትዕግስት መታገስ የእግዚአብሔር ጸጋ የሞላበት መንገድ ቢሆንም፣ ሁልጊዜ ግን አይታገስም። በመጨረሻም ይመጣል፣ ግትርና ንስሐ የማይገቡትንም አይምራቸውም። ክርስቶስ በመስቀል ላይ በነበረበት ጊዜ ደካማና ረዳት የሌለው ሰው ሆኖ የታየ ቢሆንም፣ ትንሣኤውና ሕይወቱ ግን መለኮታዊ ኃይሉን አሳየ። እንዲሁ ሐዋርያትም ለዓለም ምን ያህል የተናቁና የተዋረዱ ቢመስሉም፣ እንደ መሳሪያ ግን የእግዚአብሔርን ኃይል ገለጡ። እነሱም የባሕርያቸውን፣ የአካሄዳቸውንና የልምምዳቸውን እውነተኛነት ወርቅ በሙከራ ድንጋይ እንደሚፈተን ሁሉ ይፈትኑ። እነርሱ ራሳቸው በክርስቶስ ውድቅ እንዳልተደረጉ ማረጋገጥ ከቻሉ፣ እርሱም በክርስቶስ ውድቅ ያልተደረገ መሆኑን እነርሱም እንደሚረዱት ተስፋ አደረገ። በመንፈሱ ተጽዕኖዎች፣ ጸጋዎችና መንፈሱ በውስጣቸው በመኖሩ፣ እንዲሁም መንግሥቱ በልባቸው ውስጥ በመመሥረቱ ክርስቶስ ኢየሱስ በውስጣቸው እንዳለ ማወቅ ይገባቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6