2ኛ ቆሮንቶስ 13

AMHEVGአማርኛ13 ጥቅሶች2:00 አዳምጥ
አዳምጥ 2:00 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ ሁሉ ነገር በሁለትና በሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።

2ሁለተኛ በእናንተ ዘንድ በነበርሁ ጊዜ እንደ ተናገርሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንዲናገር ማስረጃ ከፈለጋችሁ፥ እንደ ገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ላደረጉት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ ብዬአለሁ፥ አስቀድሜም እላለሁ። ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም ነገር ግን በእናንተ ኃይለኛ ነው።

4በድካም ተሰቅሎአልና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንደክማለንና፥ ነገር ግን ስለ እናንተ በሆነ በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን።

5በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን?

6እኛ ግን የማንበቃ እንዳይደለን ልታውቁ ተስፋ አደርጋለሁ።

7ክፉ ነገርንም ከቶ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ እኛ የምንበቃ ሆነን እንገለጥ ዘንድ አይደለም ነገር ግን እኛ ምንም እንደማንበቃ ብንሆን፥ እናንተ መልካሙን ታደርጉ ዘንድ ነው።

8ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና።

9እኛ ስንደክም እናንተም ኃይለኞች ስትሆኑ ደስ ብሎናልና፤ እናንተ ፍጹማን ትሆኑ ዘንድ ለዚህ ደግሞ እንጸልያለን።

10ስለዚህ ጌታ ለማፍረስ ያይደለ ለማነጽ እንደ ሰጠኝ ሥልጣን፥ ከእናንተ ጋር ሳለሁ በቁርጥ እንዳልሠራ በሩቅ ሆኜ ይህን እጽፋለሁ።

11በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ደኅና ሁኑ። ፍጹማን ሁኑ፥ ምክሬን ስሙ፥ በአንድ ልብ ሁኑ፥ በሰላም ኑሩ፥ የፍቅርና የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።

12በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ።

13ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

14የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።

ማብራሪያ

13:1-6

ኃጢአተኞችን በትዕግስት መታገስ የእግዚአብሔር ጸጋ የሞላበት መንገድ ቢሆንም፣ ሁልጊዜ ግን አይታገስም። በመጨረሻም ይመጣል፣ ግትርና ንስሐ የማይገቡትንም አይምራቸውም። ክርስቶስ በመስቀል ላይ በነበረበት ጊዜ ደካማና ረዳት የሌለው ሰው ሆኖ የታየ ቢሆንም፣ ትንሣኤውና ሕይወቱ ግን መለኮታዊ ኃይሉን አሳየ። እንዲሁ ሐዋርያትም ለዓለም ምን ያህል የተናቁና የተዋረዱ ቢመስሉም፣ እንደ መሳሪያ ግን የእግዚአብሔርን ኃይል ገለጡ። እነሱም የባሕርያቸውን፣ የአካሄዳቸውንና የልምምዳቸውን እውነተኛነት ወርቅ በሙከራ ድንጋይ እንደሚፈተን ሁሉ ይፈትኑ። እነርሱ ራሳቸው በክርስቶስ ውድቅ እንዳልተደረጉ ማረጋገጥ ከቻሉ፣ እርሱም በክርስቶስ ውድቅ ያልተደረገ መሆኑን እነርሱም እንደሚረዱት ተስፋ አደረገ። በመንፈሱ ተጽዕኖዎች፣ ጸጋዎችና መንፈሱ በውስጣቸው በመኖሩ፣ እንዲሁም መንግሥቱ በልባቸው ውስጥ በመመሥረቱ ክርስቶስ ኢየሱስ በውስጣቸው እንዳለ ማወቅ ይገባቸዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6