1ኛ ጢሞቴዎስ 6

AMHNIVአማርኛ21 ጥቅሶች4:20 አዳምጥ
አዳምጥ 4:20 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱም እንዳይሰደቡ፣ በባርነት ቀንበር ሥር ያሉ ሁሉ፣ ጌቶቻቸው ሙሉ ክብር እንደሚገባቸው አድርገው ይቊጠሩ።

2የሚያምኑ ጌቶች ያሏቸውም፣ ወንድሞች ስለሆኑ የሚገባቸውን ክብር አይንፈጓቸው፤ ይልቁንም በአገልግሎታቸው የሚጠቀሙ አማኞችና ወዳጆቻቸው ስለሆኑ የበለጠ ሊያገለግሏቸው ይገባል። እነዚህን ነገሮች አስተምር፤ ምከርም።

3ማንም የሐሰት ትምህርት ቢያስተምር፣ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጤናማ ቃልና እውነተኛ መንፈሳዊነትን ከሚያጐለብት ትምህርት ጋር የማይስማማ ቢሆን፣

4ያ ሰው በትዕቢት ተወጥሮአል፤ አንዳችም አያስተውልም። ስለ ቃላት ለመከራከርና ለመጣላት ክፉ ጒጒት አለው፤ እነዚህም ቅናትን፣ ጥልን፣ ስድብን፣ መጥፎ ጥርጣሬን ያስከትላሉ፤

5እውነትን በተቀሙና መንፈሳዊው ነገር ትርፍ ማግኛ በሚመስላቸውና አእምሮ በጐደላቸው ሰዎች መካከል የማያባራ ንትርክ ያመጣሉ።

6ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት ጋር ትልቅ ትርፍ ነው።

7ምክንያቱም ወደ ዓለም ያመጣነው ምንም ነገር የለም፤ ምንም ነገር ይዘን መሄድም አንችልም።

8ነገር ግን ምግብና ልብስ ካለን፣ ያ ይበቃናል።

9ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ ግን ወደ ፈተናና ወደ ወጥመድ፣ እንዲሁም ሰዎችን ወደ መፍረስና ወደ ጥፋት ወደሚያዘቅጠው ወደ ብዙ ከንቱና ክፉ ምኞት ይወድቃሉ።

10ምክንያቱም የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነው፤ አንዳንዶች ባለጠጋ ለመሆን ካላቸው ጒጒት የተነሣ ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል፤ ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።

11የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፣ እውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ትዕግሥትንና ገርነትን ተከታተል።

12መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ በብዙ ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትንና የተጠራህበትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ።

13ለሁሉም ሕይወትን በሚሰጥ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁም በጳንጥዮስ ጲላጦስ ፊት እውነትን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት ዐደራ የምልህ፣

14ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ፣ ይህን ትእዛዝ ያለ ዕድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ እንድትጠብቅ ነው፤

15ያም መገለጥ፣ የተባረከውና ብቻውን ገዥ የሆነው የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ የሚያሳየው ነው፤

16እርሱ ብቻ ኢመዋቲ ነው፤ ሊቀረብ በማይቻል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እርሱን ያየ ማንም የለም፤ ሊያየውም የሚችል የለም። ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤ አሜን።

17በዚህ ዓለም ባለጠጎች የሆኑት እንዳይታበዩ፣ ደስም እንዲለን ሁሉን ነገር አትረፍርፎ በሚሰጠን በእግዚአብሔር እንጂ አስተማማኝነት በሌለው በሀብት ላይ ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።

18መልካም እንዲሠሩ፣ ቸሮችና ለማካፈል ፈቃደኞች የሆኑ እንዲሆኑ እዘዛቸው።

19በዚህ ዐይነት እውነተኛ የሆነውን ሕይወት ያገኙ ዘንድ፣ ለሚመጣው ዘመን ጽኑ መሠረት የሚሆን ሀብት ለራሳቸው ያከማቻሉ።

20ጢሞቴዎስ ሆይ፤ በዐደራ የተቀበልኸውን ሁሉ ጠብቅ፤ እግዚአብሔርን ከማያስከብር ከከንቱ ልፍለፋና ለተቃውሞ በውሸት ዕውቀት ከተባለ ፍልስፍና ራቅ፤

21የዚህ ዐይነት ዕውቀት አለን ሲሉ የነበሩ አንዳንዶች ይህን በማድረጋቸው ከእምነት መንገድ ስተው ሄደዋል።

ማብራሪያ

፮፥፩-፭ ክርስቲያኖች፣ የሃይማኖት ዕውቀት ወይም የክርስቲያን መብቶች፣ አረማውያን የሆኑ ጌቶቻቸውን ለመናቅ፣ ወይም ሕጋዊ ትእዛዛትን ላለመታዘዝ፣ ወይም ስህተቶቻቸውን ለሌሎች ለማጋለጥ ማንኛውንም መብት እንደሰጣቸው ሊያስቡ አይገባም ነበር። እንዲሁም ከሚያምኑ ጌቶች ጋር የመኖር ልዩ መብት ያገኙትም፣ በሃይማኖታዊ መብቶች ረገድ እኩል ስለሆኑ ተገቢውን አክብሮትና ክብር ሊከለክሏቸው አይገባም ነበር፤ ይልቁንም በክርስቶስ ባላቸው እምነት የተነሳ፣ እንዲሁም በነጻ ቤዛነቱ ተካፋይ በመሆናቸው ምክንያት፣ በሁለት እጥፍ ትጋትና በደስታ ማገልገል ነበረባቸው። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ካልሆነ በስተቀር፣ ማንኛውንም ቃል ጤናማ እንደሆነ ልንቀበል አይገባም። ለእነዚህ ደግሞ ቅን ስምምነት ልንሰጥ ይገባል። አብዛኛውን ጊዜ እጅግ በጣም የሚኮሩት የሚያውቁት ነገር ጥቂት የሆኑት ናቸው፤ ራሳቸውን አያውቁምና። ከዚህም የተነሳ ቅንዓት፣ ጠብ፣ ስድብ፣ ክፉ ጥርጣሬዎች፣ እንዲሁም እውነትንና የቅድሳት ኃይሉን የማያውቁ፣ የዓለም ጥቅማቸውን የሚሹ፣ በተበላሹና ሥጋዊ አስተሳሰብ ባላቸው ሰዎች መካከል በተንኮል የተሞሉና መሠረት የሌላቸው ክርክሮች ይመጣሉ።

6:6-10 ክርስትናን ለዚህ ዓለም ጥቅም የንግድ ሥራ የሚያደርጉ ሰዎች ይከስማሉ፤ ነገር ግን እንደ ጥሪያቸው አድርገው ለሚያስተውሉት፣ አሁን ስላለችው ሕይወትም ሆነ ስለሚመጣው ሕይወት ተስፋ እንዳለው ያገኛሉ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው በሚመጣው ዓለም ደስታን ማግኘቱ የተረጋገጠ ነው፤ በዚህም ዓለም ባለው ሁኔታው ከረካ፣ በቂ አለው፤ ሁሉም በእውነት እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች ረክተዋል። እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስንሆን እንኳ፣ ወደዚህ ዓለም ከመጣንበት ጊዜ የበለጠ ድሆች መሆን አንችልም፤ የመግነዝ ጨርቅ፣ የሬሳ ሣጥንና መቃብር ዓለም ላይ ያለ ሀብታም ሰው ሁሉ ከሀብቱ ሊያገኘው የሚችለው ያ ብቻ ነው። ተፈጥሮ በትንሽ ነገር መርካት ካለባት፣ ጸጋ ደግሞ ባነሰ ነገር መርካት አለበት። ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑት ነገሮች የእውነተኛ ክርስቲያን ፍላጎቶችን ይወስናሉ፣ በእነዚህም ለመርካት ይጥራል።

እዚህ ላይ የስግብግብነትን ክፋት እንመለከታለን።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ አንዳይሰደብ፥ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች ክብር ሁሉ እንደ ተገባቸው ይቍጠሩአቸው። አማርኛ ENGNIV All who are under the yoke of slavery should consider their masters worthy of full respect, so that God's name and our … English BCV ስም እግዚኣብሄርን፥ እቲ እንሰብኮ ትምህርትን፥ ምእንቲ ኸይንቀፍ፥ እቶም ኣብ ትሕቲ ኣርዑት ባርነት ዘለዉ ዅሎም፥ ነቶም ጐይተቶም ምሉእ ኽብሪ ኸም ዝግብኦም ይቝፀርዎም። ትግርኛ GAZBIB Warri waanjoo garbummaa jala jiran Waaqayyo, barsiifni keenyas maqaa gadhee akka hin godhannetti, warra isaan bulchan a… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኵሉ ነባሪ ወቅኑይ አክብሩ አጋእዝቲክሙ በኵሉ ከመ ኢይፅርፉ ላዕለ ስመ እግዚአብሔር ወላዕለ ትምህርቱ። giz GAZGAZ Warri waanjoo garbummaa jala jiran Waaqayyo, barsiifni keenyas maqaa gadhee akka hin godhannetti, warra isaan bulchan a… Afaan Oromoo BCV aksum ስም እግዚኣብሄርን፥ እቲ እንሰብኮ ትምህርትን፥ ምእንቲ ኸይንቀፍ፥ እቶም ኣብ ትሕቲ ኣርዑት ባርነት ዘለዉ ዅሎም፥ ነቶም ጐይተቶም ምሉእ ኽብሪ ኸም ዝግብኦም ይቝፀርዎም። ትግርኛ SWAHSUV Wo wote walio chini ya kongwa, hali ya utumwa, na wawahesabie bwana zao kuwa wamestahili heshima yote, jina la Mungu li… Kiswahili