1ኛ ጴጥሮስ 5

AMHNIVአማርኛ14 ጥቅሶች2:42 አዳምጥ
አዳምጥ 2:42 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1እንግዲህ ከእነርሱ ጋር እኔም ሽማግሌና የክርስቶስ መከራ ምስክር የሆንሁ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤

2በእናንተ ኀላፊነት ሥር ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቁትም ከእግዚአብሔር እንደሚጠበቅባችሁ በግድ ሳይሆን በፈቃደኝነት፣ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን ለማገልገል ባላችሁ ጽኑ ፍላጎት ይሁን፤

3እንዲሁም በዐደራ ለተሰጣችሁ መንጋ መልካም ምሳሌ በመሆን እንጂ በላያቸው በመሠልጠን አይሁን።

4የእረኞች አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን አክሊል ትቀበላላችሁ።

5ጐልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”

6ስለዚህ እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤

7እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።

8ራሳችሁን የምትገዙ ሁኑ፤ ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል።

9በዓለም ዙሪያ ያሉት ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እንደሚቀበሉ ዐውቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።

10በክርስቶስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ፣ ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ እርሱ ራሱ መልሶ ያበረታችኋል፤ አጽንቶም ያቆማችኋል።

11ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።

12እንደ ታማኝ ወንድም በምቈጥረው በስልዋኖስ አማካይነት ይህንን አጭር መልእክት ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍሁላችሁም ልመክራችሁና ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልመሰክርላችሁ ብዬ ነው። በዚህ ጸጋ ጸንታችሁ ቁሙ።

13ከእናንተ ጋር የተመረጠችው፣ በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ እንዲሁም ልጄ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።

14በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን።

ማብራሪያ

5:1-4 ሐዋርያው ጴጥሮስ አያዝም፤ ይልቁንም ይመክራል። በሁሉም እረኞችና አብያተ ክርስቲያናት ላይ የመግዛት ሥልጣን አይጠይቅም። የክርስቶስ መከራ ምስክሮች መሆን የጴጥሮስና የጥቂት ሌሎች ልዩ ክብር የነበረ ቢሆንም፤ የሚገለጠው ክብር ተካፋዮች መሆን ግን የሁሉም እውነተኛ ክርስቲያኖች መብት ነው። እነዚህ ድሆች፣ የተበተኑና መከራ የሚቀበሉ ክርስቲያኖች፣ በታላቁ እረኛ ለእግዚአብሔር የተቤዠቁ፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መሠረት በቅዱስ ፍቅርና ኅብረት የሚኖሩ የእግዚአብሔር መንጋ ነበሩ። በተጨማሪም እነርሱ የእግዚአብሔር ርስት ወይም የእርሱ የተለየ ዕጣ በሚለው ስም ከፍ ተደርገዋል፤ ልዩ ሞገሱን ለመቀበልና ልዩ አገልግሎት ሊያደርጉለትም ለራሱ ሕዝብነት የተመረጡ ናቸው። ክርስቶስ የጠቅላላው የእግዚአብሔር መንጋና ርስት ዋና እረኛ ነው። ሁሉም ታማኝ አገልጋዮች ደግሞ ከዓለም ሥልጣን፣ ሀብትና ደስታ ሁሉ እጅግ የላቀና የበለጠ ክቡር የሆነ የማትጠፋ የክብር አክሊል ይቀበላሉ።

፭፥፭-፱ ትሕትና በሁሉም ክርስቲያናዊ አብያተ ክርስቲያናትና ማኅበራት ውስጥ ሰላምንና ሥርዓትን ይጠብቃል፤ ትዕቢት ግን ያውካቸዋል። እግዚአብሔር ትሕትናን በሚሰጥበት ቦታ፣ ጥበብን፣ እምነትንና ቅድስናን ይሰጣል። ትሑት መሆን እና ከታረቀን አምላካችን በታች መገዛት፣ ከትዕቢትና ከሥልጣን ፍላጎት መርካት ይልቅ ለነፍስ ታላቅ መጽናናትን ያመጣል። ነገር ግን በጊዜው ይሆናል፤ በራስህ በታሰበው ጊዜ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር በጥበብ በተወሰነው ጊዜ ነው። እርሱ ይጠብቃል፣ አንተስ አትጠብቅምን? በእርሱ ጥበብ፣ ኃይልና መልካምነት ላይ ያለው ጽኑ እምነት የማይሻገረው ምን ዓይነት ችግር አለ! እንግዲህ በእጁ ሥር ትሑት ሁን።

ጭንቀቶቻችሁን ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ጣሉ፤ የግል ጭንቀቶችን፣ የቤተሰብ ጭንቀቶችን፣ የአሁንና የወደፊት ጭንቀቶችን፣ ለራሳችሁ፣ ለሌሎችና ለቤተ ክርስቲያን ያላችሁን ጭንቀቶች።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤ አማርኛ ENGNIV To the elders among you, I appeal as a fellow elder, a witness of Christ's sufferings and one who also will share in th… English BCV ኣነ ኸምኣቶም ሽማግለ(ሀ) ዝኾንኩ፥ ናይቲ ክርስቶስ ዝተቐበሎ ስቓይ መስካሪ፥ ኣብቲ ደሓር ክግለፅ ዘለዎ ኽብሪውን ተኻፋሊ ዝኾንኩ፥ ነቶም ኣብ ማእኸልኩም ዘለዉ ሽማግለታት፥ እምዕዶም ኣለኹ። ትግርኛ GAZBIB Ani akkuma isaanii maanguddoo, dhuga-baatuu dhiphina Kristos akkasumas hirmaattuu ulfina isa mul'achuuf jiruu ta'ee, ma… Afaan Oromoo BCV GIZ ወለእለኒ ይትለሀቁ እምኔክሙ አስተበቍዖሙ አነ ልሂቅ ካልኦሙ ወሰማዕት በእንተ ሕማሙ ለክርስቶስ ዘሀለዎ ያስተርኢ በስብሐቲሁ ከመ ትኩኑ ሱታፎ። giz GAZGAZ Ani akkuma isaanii maanguddoo, dhuga-baatuu dhiphina Kristos akkasumas hirmaattuu ulfina isa mul'achuuf jiruu ta'ee, ma… Afaan Oromoo BCV aksum ኣነ ኸምኣቶም ሽማግለ(ሀ) ዝኾንኩ፥ ናይቲ ክርስቶስ ዝተቐበሎ ስቓይ መስካሪ፥ ኣብቲ ደሓር ክግለፅ ዘለዎ ኽብሪውን ተኻፋሊ ዝኾንኩ፥ ነቶም ኣብ ማእኸልኩም ዘለዉ ሽማግለታት፥ እምዕዶም ኣለኹ። ትግርኛ SWAHSUV Nawasihi wazee walio kwenu, mimi niliye mzee, mwenzi wao, na shahidi wa mateso ya Kristo, na mshirika wa utukufu utakao… Kiswahili