1ኛ ቆሮንቶስ 6

AMHNIVአማርኛ20 ጥቅሶች3:33 አዳምጥ
አዳምጥ 3:33 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከመካከላችሁ አንድ ሰው ከሌላው ጋር ሙግት ቢኖረው፣ ጒዳዩን በቅዱሳን ፊት በማቅረብ ፈንታ እንዴት ደፍሮ በማያምኑ ሰዎች ፊት ለመፋረድ ያቀርባል?

2ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ እንግዲያው፣ በትንሹ ነገር ላይ ለመፍረድ አትበቁምን?

3በምድራዊ ሕይወት ጒዳይ ቀርቶ፣ በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን?

4እንግዲህ እንዲህ ያለ ጒዳይ ሲያጋጥማችሁ፣ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጅ አድርጋችሁ ሹሟ!

5ይህንንም የምለው ላሳፍራችሁ ብዬ ነው። ለመሆኑ ከመካካላችሁ ወንድሞችን ለማስታረቅ የሚበቃ አስተዋይ ሰው የለምን?

6ነገር ግን ወንድም ወንድሙን ለመክሰስ ፍርድ ቤት ይሄዳል፤ ያውም በማያምኑ ሰዎች ፊት!

7እንግዲህ በመካከላችሁ መካሰስ መኖሩ ራሱ ውድቀታችሁን ያሳያል። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን?

8እናንተ ግን ራሳችሁ ትበድላላችሁ፤ ታታልላላችሁም፤ ያውምኮ ወንድሞቻችሁን።

9ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ አመንዝሮች፣ ወንደቃዎች፣ ግብረ ሰዶማውያን፣

10ወይም ሌቦች፣ ስግብግቦች፣ ሰካራሞች፣ ተሳዳቢዎችና ቀማኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

11ከእናንተ አንዳንዶቻችሁ እንደዚህ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋል።

12“ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ይሁን እንጂ ሁሉም ነገር አይጠቅምም፤ “ሁሉ ነገር ተፈቅዶልኛል፤” ይሁን እንጂ ምንም ነገር በእኔ ላይ አይሠለጥንም።

13ደግሞም፣ “ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው።

14እግዚአብሔር ጌታን ከሙታን አንዳስነሣው፣ እኛንም ደግሞ በኀይሉ ከሙታን ያስነሣናል።

15ሰውነታችሁ የክርስቶስ የአካሉ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን? ታዲያ፣ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ ከዝሙት አዳሪ ሴት ብልቶች ጋር አንድ ላድርገውን? ከቶ አይገባም!

16ወይስ ከዝሙት አዳሪ ጋር የሚተባበር ሰው ከእርሷ ጋር አንድ ሥጋ እንደሚሆን አታውቁምን? “ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ” ተብሎአልና።

17ነገር ግን ከጌታ ጋር የሚተባበር ከእርሱ ጋር አንድ መንፈስ ይሆናል።

18ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል።

19ለመሆኑ፣ ሰውነታችሁ በውስጣችሁ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን? ይህም መንፈስ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት ነው። እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም፤

20በዋጋ ተገዝታችኋልና፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

ማብራሪያ

6:1-8

ክርስቲያኖች እርስ በርሳቸው መጋደል የለባቸውም፣ ምክንያቱም ወንድማማቾች ናቸውና። ይህ በትኩረት ከተስተዋለ ብዙ የፍርድ ቤት ክሶችን ይከለክል ነበር፤ እንዲሁም ብዙ ጠቦችንና ክርክሮችን ያበቃ ነበር። በራሳችን ወይም በቤተሰቦቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት በሚደርስበት ጊዜ ራሳችንን ለማረም ህጋዊ ዘዴዎችን መጠቀም እንችላለን፤ ነገር ግን ክርስቲያኖች ይቅር ባይ መንፈስ ሊኖራቸው ይገባል። የክርክር ጉዳዮችን፣ በነሱ ምክንያት ወደ ፍርድ ቤት ከመሄድ ይልቅ፣ አሳልፎ መስጠት ይገባል። እነሱ ኢምንት ጉዳዮች ናቸውና፣ በመጀመሪያ የራሳችሁን መንፈስ ካሸነፋችሁ በቀላሉም ሊፈቱ ይችላሉ። ታገሡና ተቻችሉ፣ በእናንተ መካከል በጣም ጥቂት ብልሃት ያላቸው ሰዎችም ጠባችሁን ሊያቆሙ ይችላሉ። በክርስቲያኖች መካከል ትናንሽ ጠቦች እንዲህ ያለ ደረጃ ድረስ ማደጉ፣ በወንድሞች ሊፈቱ እስኪቸግራቸው ድረስ መድረሱ የሚያሳፍር ነው። የአንድ ሰው የራሱ የአእምሮ ሰላም እና የአካባቢውም ሰላም ከድል ይበልጣል። የፍርድ ቤት ክርክሮች በወንድማማቾች መካከል ሊከሰቱ አይችሉም ነበር፤ በመካከላቸው በደል ባይኖር ኖሮ።

6:9-11 ቆሮንቶሳውያን ቀደም ሲል ተጠያቂ የነበሩባቸውን ብዙ ታላላቅ ክፋቶች እንዳይሠሩ ተገስጸዋል። እነዚህ ጥያቄዎች የተላኩለት ሕዝብ በጥበብና በእውቀት ከሌሎች እንደሚበልጥ በሐሳቡ የኮራና በትዕቢት የተነፋፋ መሆኑን ስታስቡት፣ የሚያስተጋቡት ኃይል ታላቅ ነው። ሁሉ ዓመፅ ኃጢአት ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመፀኞች ፊት ሊፋረድ ይደፍራልን? አማርኛ ENGNIV If any of you has a dispute with another, dare he take it before the ungodly for judgment instead of before the saints? English BCV ሓደ ኻባኻትኩም ምስ ብፃዩ ኽርክር እንተ ሃልይዎ፥ ጉዳዩ ኣብ ቅድሚ ቅዱሳን ክንዲ ምቕራብ፥ ከመይ ደፊሩ ኣብ ቅድሚ ዘይኣምኑ፥ ንምፍራድ ይቐርብ? ትግርኛ GAZBIB Isin keessaa namni tokko obboleessa tokko irraa hadheessa yoo qabaate, namoota Waaqayyoof qulqullaa'an duratti dubbicha… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኢትትኀበሉ እንከ ትትዋቀሡ በኀበ ጸኣልያን ቦኑ ዘይክል ይትዋቀሥ ምስለ ካልኡ በኀበ ዐማፅያን አኮኑ በኀበ ኄራን ወለእመቦ ዘቦ ተስናን ምስለ ቢጹ ለይትዋቀሥ በኀበ ቅዱሳን ወአኮ በኀበ ጸኣ… giz GAZGAZ Isin keessaa namni tokko obboleessa tokko irraa hadheessa yoo qabaate, namoota Waaqayyoof qulqullaa'an duratti dubbicha… Afaan Oromoo BCV aksum ሓደ ኻባኻትኩም ምስ ብፃዩ ኽርክር እንተ ሃልይዎ፥ ጉዳዩ ኣብ ቅድሚ ቅዱሳን ክንዲ ምቕራብ፥ ከመይ ደፊሩ ኣብ ቅድሚ ዘይኣምኑ፥ ንምፍራድ ይቐርብ? ትግርኛ SWAHSUV Je! Mtu wa kwenu akiwa ana daawa juu ya mwenzake athubutu kushitaki mbele ya wasio haki, wala si mbele ya watakatifu? Kiswahili