1ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣ ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣
2አራተኛ ልጁን ኖሐን፣ አምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ።
3የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ አዳር፣ ጌራ፣ አቢሁድ፣
4አቢሱ፣ ናዕማን፣ አሖዋ፣
5ጌራ፣ ሰፉፋ፣ ሒራም።
6በጌባ ይኖሩ የነበሩትና በኋላም በምርኮ ወደ መናሐት የተወሰዱት የኤሁድ ዘሮች እነዚህ ናቸው፤
7ናዕማን፣ አኪያ፣ ጌራ፤ በምርኮ ጊዜ እየመራ የወሰዳቸው የዖዛና የአሒሑድ አባት ጌራ ነበረ።
8ሸሐራይም ሚስቶቹን ሑሺምንና በዕራን ከፈታ በኋላ በሞዓብ ምድር ወንዶች ልጆች ወለደ።
9ከሚስቱ ከሖዴሽ ዮባብን፣ ዲብያን፣ ማሴን፣ ማልካምን፣
10ይዑጽን፣ ሻክያንና ሚርማን ወለደ፤ እነዚህም የቤተ ሰብ አለቆች የነበሩ ልጆቹ ናቸው።
11ሑሺም ከተባለች ሚስቱ አቢጡብና ኤልፍዓል የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት።
12የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች፤ ዔቤር፣ ሚሻም እንዲሁም ኦኖንና ሎድ የተባሉ ከተሞችን ከነ መንደሮቻቸው የቈረቈረ ሻሜድ፣
13በኤሎን ይኖሩ ለነበሩ ቤተ ሰቦች አለቆችና የጋት ነዋሪዎችን አስወጥተው ያሳደዱ በሪዓና ሽማዕ።
14አሒዮ፣ ሻሻቅ፣ ይሬምት፣
15ዝባድያ፣ ዓራድ፣ ዔድር፣
16ሚካኤል፣ ይሽጳና ዮሐ የበሪዓ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
17ዝባድያ፣ ሜሱላም፣ ሕዝቂ፣ ሔቤር፣
18ይሽምራይ፣ ይዝሊያና ዮባብ የኤልፍዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ።
19ያቂም፣ ዝክሪ፣ ዘብዲ፣
20ኤሊዔናይ፣ ጺልታይ፣ ኤሊኤል፣
21ዓዳያ፣ ብራያና፣ ሺምራት የሰሜኢ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
22ይሽጳን፣ ዔቤር፣ ኤሊኤል፣
23ዓብዶን፣ ዝክሪ፣ ሐናን፣
24ሐናንያ፣ ኤላም፣ ዓንቶትያ
25ይፍዴያና ፋኑኤል የሶሴቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ።
26ሽምሽራይ፣ ሽሃሪያ፣ ጎቶልያ፣
27ያሬሽያ፣ ኤልያስና፣ ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።
28እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
29የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ፤ ሚስቱ መዓካ ትባል ነበር።
30የበኵር ልጁም አብዶን ይባል ነበር፤ የእርሱም ተከታዮች ዱር፣ ቂስ፣ በኣል፣ ኔር፣ ናዳብ፣
31ጌዶር፣ አሒዮ፣ ዛኩርና
32የሺምዓ አባት ሚቅሎት ነበሩ። እነዚህም ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም ከተማ አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
33ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፣ ሜልኪሳን፣ አሚናዳብን፣ አስበኣልን ወለደ።
34የዮናታን ወንድ ልጅ መሪበኣል፤ እርሱም ሚካን ወለደ።
35የሚካ ወንዶች ልጆች፤ ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬዓ፣ አካዝ።
36አካዝ ይሆዓዳን ወለደ፤ ይሆዓዳም ዓሌሜትን፣ ዓዝሞትን፣ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ሞጻን ወለደ።
37ሞጻ ቢንዓን ወለደ፤ ቢንዓ ረፋያን ወለደ፤ ረፋያ ኤልዓሣን ወለደ፤ ኤልዓሣም ኤሴልን ወለደ።
38ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦ ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሽዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ይባላል፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ነበሩ።
39የወንድሙ የኤሴቅ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛ ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛ ልጁ ኤሊፋላት።
40የኡላም ልጆች በቀስት መንደፍ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ እነርሱም ባጠቃላይ ቍጥራቸው አንድ መቶ ሃምሳ ወንዶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩአቸው፤ እነዚህ ሁሉ የብንያም ትውልዶች ነበሩ።