1ኛ ዜና መዋዕል 24

AMHNIVአማርኛ31 ጥቅሶች4:38 አዳምጥ
አዳምጥ 4:38 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የአሮን ልጆች አመዳደብ እንደሚከተለው ነበረ፤ የአሮን ልጆች ናዳብ፣ አብዩድ፣ አልዓዛር፣ ኢታምር ነበሩ።

2ናዳብና አብዩድ ግን ዘር ሳይተኩ ከአባታቸው በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ አልዓዛርና ኢታምር ካህናት ሆነው ያገለግሉ ነበር።

3ዳዊትም የአልዓዛር ዘር የሆነው ሳዶቅና የኢታምር ዘር የሆነው አቢሜሌክ እየረዱት እንደየአገልግሎታቸው ሥርዐት እየለየ መደባቸው።

4ከኢታምር ይልቅ በአልዓዛር ዘሮች መካከል ብዙ መሪዎች ተገኙ፤ አከፋፈላቸውም እንደሚከተለው ነበር፤ ከአልዓዛር ዘሮች ዐሥራ ስድስት የቤተ ሰብ አለቆች፤ ከኢታምርም ዘሮች ስምንት የቤተ ሰብ አለቆች።

5ከአልዓዛርና ከኢታምር ዘሮች መካከል የመቅደሱ ሹማምትና የእግዚአብሔር ሹማምት ስለ ነበሩ፣ ያለ አድልዎ በዕጣ ለዩአቸው።

6የሌዋዊው የናትናኤል ልጅ ጸሓፊው ሸማያ በንጉሡና በሹማምቱ፣ በካህኑ በሳዶቅ፣ በአብያታር ልጅ በአቤሜሌክ እንዲሁም በካህናቱና በሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ፊት ስማቸውን ጻፈ፤ የጻፈውም አንዱን ቤተ ሰብ ከአልዓዛር ሌላውን ደግሞ ከኢታምር በመውሰድ ነው፤

7የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሪብ፣ ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ፤

8ሦስተኛው ለካሪም፣ አራተኛው ለሥዖሪም፣

9አምስተኛው ለመልክያ፣ ስድስተኛው ለሚያሚን፣

10ሰባተኛው ለአቆስ፣ ስምንተኛው ለአብያ፣

11ዘጠነኛው ለኢያሱ፣ ዐሥረኛው ለሴኬንያ፣

12ዐሥራ አንደኛው ለኤሊያሴብ፣ ዐሥራ ሁለተኛው ለያቂም፣

13ዐሥራ ሦስተኛው ለኦፖ፣ ዐሥራ አራተኛው ለየሼብአብ፣

14ዐሥራ አምስተኛው ለቢልጋ፣ ዐሥራ ስድስተኛው ለኢሜር፣

15ዐሥራ ሰባተኛው ለኤዚር፣ ዐሥራ ስምንተኛው ለሃፊጼጽ፣

16ዐሥራ ዘጠነኛው ለፈታያ፣ ሃያኛው ለኤዜቄል፣

17ሃያ አንደኛው ለያኪን፣ ሃያ ሁለተኛው ለጋሙል፣

18ሃያ ሦስተኛው ለድላያ፣ ሃያ አራተኛ ለመዓዝያ ወጣ።

19የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር።

20ከቀሩት የሌዊ ዘሮች ደግሞ፦ ከእንበረም ወንዶች ልጆች፤ ሱባኤል፤ ከሱባኤል ወንዶች ልጆች፤ ዬሕድያ።

21ከረዓብያ ወንዶች ልጆች፤ አለቃው ይሺያ።

22ከይስዓራውያን ወገን፤ ሰሎሚት ከሰሎሚት ወንዶች ልጆች፤ ያሐት።

23የኬብሮን ወንዶች ልጆች፤ የመጀመሪያው ይሪያ፣ ሁለተኛው አማርያ፣ ሦስተኛው የሕዚኤል፣ አራተኛው ይቀምዓም።

24የዑዝኤል ልጅ፤ ሚካ። ከሚካ ወንዶች ልጆች ሻሚር።

25የሚካ ወንድም ይሺያ፤ ከይሺያ ወንዶች ልጆች ዘካርያስ።

26የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ሙሲ። የያዝያ ወንድ ልጅ በኖ።

27የሜራሪ ወንዶች ልጆች፤ ከያዝያ በኖ፣ ሾሃም፣ ዘኩር፣ ዔብሪ።

28ከሞሖሊ፤ አልዓዛር፤ ይህ ሰው ወንዶች ልጆች አልነበሩትም።

29ከቂስ፤ የቂስ ወንድ ልጅ፤ ይረሕምኤል።

30የሙሲ ወንዶች ልጆች፤ ሞሖሊ፣ ዔዳር፣ ኢያሪሙት። እነዚህ እንግዲህ እንደየቤተ ሰባቸው የተቈጠሩ ሌዋውያን ነበሩ።

31ወንድሞቻቸው የአሮን ዘሮች እንዳደረጉት ሁሉ፣ እነዚህም በንጉሥ ዳዊት፣ በሳዶቅ፣ በአቢሜሌክ እንዲሁም የካህናቱና የሌዋውያኑ ቤተ ሰብ አለቆች ባሉበት ዕጣ ተጣጣሉ፤ የበኵሩም ቤተ ሰቦች እንደ ትንሹ ወንድም ቤተ ሰብ እኩል ዕጣ ተጣለላቸው።

ማብራሪያ

24:1-31 የካህናትና የሌዋውያን ክፍፍል። እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ቦታና ሥራ ሲያገኝ፣ ሲያውቅና ሲጠብቅ፣ ብዙ በሆኑ ቁጥር የተሻለ ይሆናል። በክርስቶስ ምስጢራዊ አካል ውስጥ፣ እያንዳንዱ አባል ለመላው አካል ጥቅም የራሱ የሆነ ተግባር አለው። ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቤት ላይ ሊቀ ካህናት ነው፣ እርሱንም ካህናት የተደረጉ አማኞች ሁሉ ሊገዙለት ይገባል። በክርስቶስ ውስጥ፣ በባሪያና በነጻ፣ በሽማግሌና በታናሽ መካከል ምንም ልዩነት የለም። ታናናሾቹ ወንድሞች ታማኞችና ቅኖች ከሆኑ፣ በክርስቶስ ዘንድ ከሽማግሌዎቹ/ከአባቶች ያነሰ ተቀባይነት አይኖራቸውም። ሁላችንም የጌታ ልጆች ሆነን፣ በላይ ባለው መቅደሱ ውስጥ ለዘላለም ምስጋናውን ለመዘመር የተዘጋጀን እንሁን።

ምዕራፍ 24 ይህ ምዕራፍ ካህናትና ሌዋውያን ቤተሰቦቻቸውን መሠረት በማድረግ የየራሳቸውን አገልግሎት በሥርዓት እንዲያከናውኑ ወደየክፍላቸው ስለተከፋፈሉበት ሁኔታ በዝርዝር ይነግረናል።

I. ስለ ካህናት (ቁ. 1-19)።

II. ስለ ሌዋውያን (ቁ. 20-31)።

ቁጥር 1-19 የእነዚህ ሥርዓቶች ዝርዝር መግለጫ አሁን ለእኛ ብዙም ጥቅም የለውም፤ ነገር ግን ዕዝራ ባሳተመው ጊዜ፣ ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ የቤተ ክርስቲያናቸውን ጉዳዮች ወደ ቀድሞው ሥርዓት ለመመለስ ታላቅ ጥቅም ነበረው። የዚህ መዝገብ ርዕስ ቁጥር 1 ላይ እናገኘዋለን—እነዚህም የአሮን ልጆች ክፍሎች ናቸው፤ እርስ በእርሳቸው የተከፋፈሉበት ወይም የተጣሉበት ሳይሆን (በእስራኤል ልጆች መካከል፣ በተለይም በአሮን ልጆች መካከል እንዲህ ያለ ክፍፍል መኖሩ ያሳዝናል)፣ ነገር ግን ሥራቸውን እርስ በእርሳቸው ለመከፋፈል የተደረገ ክፍፍል ነው። ይህ ክፍፍል እግዚአብሔር ያደረገውና ለእርሱ የተደረገ ነበር።

1. ይህ ክፍፍል የተደረገው የሥራቸውን ግዴታዎች በበለጠ ሥርዓት ለማከናወን ነው። እግዚአብሔር የሥርዓት አምላክ ነው እንጂ የግርግር አምላክ አይደለም፣ በተለይም በአምልኮው ጉዳዮች። ሥርዓት የሌለው ቁጥር እንቅፋትና የግርግር መንስኤ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ሁሉም ሰው ቦታውንና ሥራውን ሲያውቅና ሲጠብቅ፣ ቁጥሩ በጨመረ ቁጥር የተሻለ ይሆናል። በምሥጢራዊው አካል ውስጥ፣ እያንዳንዱ አባል ለጠቅላላው ጥቅም የራሱ የሆነ አገልግሎት አለው (ሮሜ 12:4, 5፤ 1 ቆሮ. 12:12)።

2. ይህ የተደረገው ዕጣ በመጣል ነበር፣ ስለዚህም አወጋገዱ ከእግዚአብሔር እንዲሆን፣ እናም ሁሉም ጠብና ክርክር እንዲወገድ፣ ማንም ሰው በአድልዎ ሊከሰስ እንዳይችል፣ ወይም ማንም ሰው በደል ደርሶብኛል ሊል እንዳይችል ነበር። እግዚአብሔር የሥርዓት አምላክ እንደሆነ ሁሉ፣ የሰላም አምላክም ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6