1እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
2የዕለት ጒርስ ለማግኘት በመጣር፣ ማልዳችሁ መነሣታችሁ፣ አምሽታችሁም መተኛታችሁ ከንቱ ነው፤ እርሱ ለሚወዳቸው እንቅልፍን ያድላልና።
3እነሆ፤ ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው፤ የማሕፀንም ፍሬ ከቸርነቱ የሚገኝ ነው።
4በወጣትነት የተገኙ ወንዶች ልጆች፣ በጦረኛ እጅ እንዳሉ ፍላጾች ናቸው።
5ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ፣ የተባረከ ሰው ነው፤ ከጠላቶቻቸው ጋር በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።