መጽሐፈ ምሳሌ 29

AMHNIVአማርኛ27 ጥቅሶች3:28 አዳምጥ
አዳምጥ 3:28 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ከብዙ ተግሣጽ በኋላ ዐንገቱን የሚያደነድን ሰው፣ በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።

2ጻድቃን ሥልጣን ሲይዙ ሕዝብ ሐሤት ያደርጋል፤ ክፉዎች ሲገዙ ግን ሕዝብ ያቃስታል።

3ጥበብን የሚወድ ሰው አባቱን ደስ ያሰኛል፤ የአመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያባክናል።

4ፍትሕን በማስፈን ንጉሥ አገርን ያረጋጋል፤ ጒቦ ለማግኘት የሚጐመጅ ግን ያፈራርሳታል።

5ባልንጀራውን የሚሸነግል፣ ለገዛ እግሩ መረብ ይዘረጋል።

6ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤ ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል።

7ጻድቅ ለድኾች ፍትሕ ይጨነቃል፤ ክፉ ሰው ግን ደንታ የለውም።

8ተሳዳቢዎች ከተማን ያውካሉ፤ ጠቢባን ግን ቊጣን ያበርዳሉ።

9ጠቢብ ሰው ከተላላ ጋር ወደ ሸንጎ ቢሄድ፣ ተላላ ይቈጣል፤ ያፌዛል፤ ሰላምም አይኖርም።

10ደም የተጠሙ ሰዎች ሐቀኛን ሰው ይጠላሉ፤ ቅን የሆነውንም ለመግደል ይሻሉ።

11ተላላ ሰው ቍጣውን ያለ ገደብ ይለቀዋል፤ ጠቢብ ሰው ግን ራሱን ይቈጣጠራል።

12ገዥ የሐሰት ወሬ የሚሰማ ከሆነ፣ ሹማምቱ ሁሉ ክፉዎች ይሆናሉ።

13ድኻውና ጨቋኙ የጋራ ነገር አላቸው፤ እግዚአብሔር ለሁለቱም የዐይን ብርሃንን ሰጥቶአቸዋል።

14ንጉሥ ለድኻ ትክክለኛ ፍርድ ቢሰጥ፣ ዙፋኑ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል።

15የተግሣጽ በትር ጥበብን ታጐናጽፋለች፤ መረን የተለቀቀ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል።

16ክፉዎች ሥልጣን ሲይዙ ኀጢአት ይበዛል፤ ጻድቃን ግን የእነርሱን ውድቀት ያያሉ።

17ልጅህን ቅጣው፤ ሰላም ይሰጥሃል፤ ነፍስህንም ደስ ያሰኛታል።

18ራእይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው።

19አገልጋይ በቃል ብቻ ሊታረም አይችልም፤ ቢያስተውለውም እንኳ በጀ አይልም።

20በችኰላ የሚናገርን ሰው ታያለህን? ከእርሱ ይልቅ ተላላ ተስፋ አለው።

21ሰው አገልጋዩን ከልጅነቱ ጀምሮ ቢያቀማጥል፣ የኋላ ኋላ ሐዘን ያገኘዋል።

22ቊጡ ሰው ጠብን ይጭራል፤ ግልፍተኛም ብዙ ኀጢአት ይሠራል።

23ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል፤ ትሑት መንፈስ ያለው ግን ክብርን ይጐናጸፋል።

24የሌባ ግብረ አበር የገዛ ራሱ ጠላት ነው፤ የመሐላውን ርግማን እየሰማ ጭጭ ይላል።

25ሰውን መፍራት ወጥመድ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን በሰላም ይኖራል።

26ብዙዎች በገዥ ፊት ተደማጭነት ማግኘት ይሻሉ፤ ሰው ፍትሕ የሚያገኘው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

27ጻድቃን አታላዮችን ይጸየፋሉ፤ ክፉዎችም ቅኖችን ይጠላሉ።

ማብራሪያ

29:1 አምላክ ቢያቆስል፥ ማን ሊፈውስ ይችላል? የእግዚአብሔር ቃል ሁሉንም ከሚመጣው ቁጣ እንዲሸሹና በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ፊት ወደ ተቀመጠው ተስፋ እንዲጠጉ ያስጠነቅቃል። 2. ሕዝቡ ገዥዎቻቸው ጻድቃን ወይም ክፉዎች እንደሆኑ በመወሰን ለመደሰት ወይም ለማዘን ምክንያት አላቸው። 3. መለኮታዊ ጥበብ ከሚያጠፉ ምኞቶች በተሻለ ሁኔታ ይጠብቀናል። 4. ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ እውነተኛ ፍርድን የሚሰጥ ንጉሥ ነው። 5. አሞሌዎች ሰዎችን ጥንቃቄ የጎደላቸው ያደርጋሉ፥ ይህም ወደ ሞኝነት ምግባር አሳልፎ ይሰጣቸዋል። 6. መተላለፎች ሁልጊዜ በመረበሽ ያከትማሉ። ጻድቃን ሰዎች በነጻነትና በደኅንነት ይሄዳሉ። 7. ይህ ጥቅስ ለድሆች ጭንቀት በሚደረግ ርኅራኄና በክፉዎች በሚታየው ስሜት የሌለው ቸልተኝነት ላይ ተፈጻሚነት አለው። 8. ተሳዳቢዎች በተቀደሱና በቁም ነገር ላይ ይሳለቃሉ። ሃይማኖትን የሚያስተዋውቁ ሰዎች፥ እርሱም እውነተኛ ጥበብ ነው፥ የእግዚአብሔርን ቁጣ ያርቃሉ። 9. አንድ ጠቢብ ሰው ከትዕቢተኛ ተከራካሪ ጋር ቢከራከር፥ በቁጣ ወይም በፌዝ ይስተናገዳል፤ ምንም መልካም ነገርም አይደረግም። 10. ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ በሁሉም ሰዎች እንደሚጠሉ ነገራቸው። ጻድቃን፥ ደም የጠሙ ሰዎች የሚጠሏቸው ቢሆኑም፥ ለሚጠሉአቸው መዳን በደስታ ማንኛውንም ነገር ያደርጋሉ።

29:11. የሚያውቀውን ሁሉ የሚናገርና ምስጢርን (ወይም ምክርን) መያዝ የማይችል ሰው ሞኝ ነው። 12. አስመሳዮችን የሚወድድና የሐሜተኞችን ቃል የሚሰማ ባሪያዎቹን ውሸታሞችና ሐሰተኛ ከሳሾች እንዲሆኑ ያደርጋል። 13. አንዳንዶች ድሆች ናቸው፤ ሌሎች ደግሞ እጅግ ብዙ አታላይ ሀብት አላቸው። በዚህ ዓለም ጉዳይ ይገናኛሉ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6