መጽሐፈ ምሳሌ 27

AMHNIVአማርኛ27 ጥቅሶች3:28 አዳምጥ
አዳምጥ 3:28 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ነገ በሚሆነው አትመካ፤ ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና።

2ሌላው ያመስግንህ እንጂ የገዛ አፍህ አይደለም፤ ሌላ ሰው ያወድስህ እንጂ የገዛ ከንፈርህ አይሁን።

3ድንጋይ ይከብዳል፤ አሸዋም ሸክም ነው፤ የተላላ ሰው ጒነጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።

4ንዴት ጨካኝ፣ ቊጣም ጐርፍ ነው፤ በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?

5የተገለጠ ዘለፋ፣ ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል።

6ከጠላት ደጋግሞ መሳም ይልቅ፣ የወዳጅ ማቊሰል ይታመናል።

7ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።

8ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ ጎጆዋን ለቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።

9ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ የወዳጅ ማስደሰትም ከቅን ምክሩ ይመነጫል።

10የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ አትተው፤ መከራ በሚያጋጥምህ ጊዜ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፤ ሩቅ ካለ ወንድም ቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።

11ልጄ ሆይ፤ ጠቢብ ሁን፤ ልቤን ደስ አሰኘው፤ ለሚንቁኝ ሁሉ መልስ መስጠት እችል ዘንድ።

12ጥንቁቅ አደጋን አይቶ ይሸሸጋል፤ ማስተዋል የጐደለው ግን ወደዚያው ይሄዳል፤ ይጐዳልም።

13ለማይታወቅ ሰው የተዋሰን ልብሱን ግፈፈው፤ ለዘልዛላ ሴት ከተዋሰማ አግተው።

14ሰው ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን በማለዳ ቢመርቅ፣ እንደ ርግማን ይቈጠራል።

15ጨቅጫቃ ሚስት፣ በዝናብ ቀን እንደሚወርድ የማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት፤

16እርሷን ለመግታት መሞከር፣ ነፋስን እንደ መግታት ወይም ዘይትን በእጅ እንደ መጨበጥ ነው።

17ብረት ብረትን እንደሚስል፣ ሰውም ሌላውን ሰው እንደዚሁ ይስለዋል።

18በለስን የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ ጌታውን የሚያገለግልም ክብርን ይጐናጸፋል።

19ውሃ ፊትን እንደሚያሳይ፣ የሰውም ልብ ማንነቱን ገልጦ ያሳያል።

20ሲኦልና የሙታን ዓለም እንደማይጠግቡ ሁሉ፣ የሰውም ዐይን አይረካም።

21ብር በማቅለጫ፣ ወርቅ በከውር እንደሚፈተን፣ ሰውም በሚቀበለው ምስጋና ይፈተናል።

22ጅልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣ እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቀው፣ ጅልነቱን ልታስወግድለት አትችልም።

23በጎችህ በምን ሁኔታ እንዳሉ ደህና አድርገህ ዕወቅ፤ መንጋህንም ተንከባከብ፤

24ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤ ዘውድም ከትውልድ ወደ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም።

25ደረቁ ሣር ተወግዶ፣ አዲሱ ብቅ ሲል፣ በየኰረብታው ላይ ያለው ሣር ተሰብስቦ ሲገባ፣

26ከበግ ጠቦቶች ልብስ ታገኛለህ፤ ፍየሎችም የዕርሻ መሬት መግዣ ይሆኑሃል።

27አንተንና ቤተ ሰብህን፣ ገረዶችህንም ጭምር ለመመገብ፣ የተትረፈረፈ የፍየል ወተት ይኖርሃል።

ማብራሪያ

27:1

አንድ ቀን ምን እንደሚያመጣ አናውቅም። ይህ ለነገ መዘጋጀትን አይከለክልም፤ ነገር ግን በነገ ላይ መተማመንን ነው። የመመለስን ታላቅ ሥራ፣ ያንን እጅግ አስፈላጊ የሆነውን አንድ ነገር፣ ማዘግየት የለብንም።

2.

ራሳችንን ለማጽደቅ ምክንያት ሊኖረን ይችላል፤ ነገር ግን ራሳችንን ለማወደስ አይደለም።

3,4.

ስሜታቸውን መቆጣጠር የማይችሉ ሰዎች በሸክሙ ይሰጥማሉ።

5,6.

ግልጽና ታማኝ ተግሣጾች ከድብቅ ጥላቻ ብቻ ሳይሆን፣ ለነፍስ ጉዳት ከሚያደርስ በኃጢአት ከሚያሞካሽ ፍቅር ይሻላሉ።

7.

ድሆች ከሀብታሞች ይልቅ ባላቸው ነገር ይበልጥ ይደሰታሉ፤ ብዙውን ጊዜም ይበልጥ አመስጋኞች ናቸው። በተመሳሳይ መልኩ ትዕቢተኞችና በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎች ወንጌልን ይንቃሉ፤ ነገር ግን ለጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ ሰዎች፣ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ከሚያመሰክረው እጅግ ቀላል መጽሐፍ ወይም ስብከት መጽናናትን ያገኛሉ።

8.

እያንዳንዱ ሰው በኅብረተሰብ ውስጥ የራሱ የሆነ ትክክለኛ ቦታ አለው፤ በዚያም ደኅንነትና ምቾት ሊያገኝ ይችላል።

27:9,10.

ለዕርዳታ በዘመድህ ላይ ዝምድናውን ብቻ በመመልከት አትደገፍ፤ ይልቁንም በአቅራቢያህ ላሉትና በችግርህ ጊዜ ለመርዳት ፈቃደኛ ለሆኑት ቅረብ። ነገር ግን ከወንድም ይልቅ የሚጠጋጋ ወዳጅ አለ፤ በእርሱም ላይ ፍጹም እምነት እንጣልበት። 11. አፍቃሪ ወላጅ ልጁ ልቡን የሚያስደስት አስተዋይ ምግባር እንዲኖረው ያሳስበዋል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6