መጽሐፈ ምሳሌ 18

AMHNIVአማርኛ24 ጥቅሶች2:48 አዳምጥ
አዳምጥ 2:48 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ ቅን የሆነውን ፍርድ ሁሉ ይቃወማል።

2ተላላ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤ የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል።

3ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ ከዕፍረትም ጋር ውርደት ትመጣለች።

4ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤ የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።

5ለክፉ ሰው ማድላት፣ ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።

6የተላላ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤ አፉም በትር ይጋብዛል።

7ተላላ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

8የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤ ወደ ሰው ውስጣዊ ክፍል ዘልቆ ይገባል።

9ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣ የአጥፊ ወንድም ነው።

10የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።

11የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ እንደማይወጣ ረጅም ግንብም ይቈጥሩታል።

12ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።

13ከማዳመጡ አስቀድሞ የሚመልስ፣ ቂልነትና ዕፍረት ይሆንበታል።

14በሕመም ጊዜ፣ ሰውን መንፈሱ ትደግፈዋለች፤ የተሰበረውን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?

15የአስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይገበያል፤ የጠቢብም ጆሮ አጥብቆ ይሻታል።

16እጅ መንሻ ለሰጪው መንገድ ትከፍትለታለች፤ ታላላቅ ሰዎች ፊትም ታቀርበዋለች።

17አስቀድሞ ጒዳዩን የሚያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ ይኸውም ባላንጣው መጥቶ እስከሚመረመር ድረስ ነው።

18ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።

19የተበደለ ወንድም ከተመሸገ ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤ ጠቡም እንደ ጠንካራ የግንብ መዝጊያ ነው።

20ሰው በአንደበቱ ፍሬ ሆዱ ይጠግባል፤ በከንፈሩም ምርት ይረካል።

21አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።

22ሚስት የሚያገኝ መልካም ነገርን ያገኛል፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን ይቀበላል።

23ድኻ በመለማመጥ ምሕረት ይለምናል፤ ሀብታም ግን በማናለብኝነት ይመልሳል።

24ወዳጅ የሚያበዛ ሰው ራሱን ለጥፋት ይዳርጋል፤ ነገር ግን ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ።

ማብራሪያ

፩፰፥፩ እውቀትንና ጸጋን ለማግኘት ከፈለግን ራሳችንን ለማሻሻል ሁሉንም ዘዴዎች መሞከር አለብን። ፪. ብቸኛ ዓላማቸው ለመመኪያነት የሚሆን ነገር ማግኘት የሆኑ ሰዎች፣ ትምህርትንም ሆነ ሃይማኖትን ከንቱ ያደርጉታል። ፫. ኃጢአት እንደገባ፣ እፍረት ተከተለ።

እባክዎን ከታች ያለውን ትርጉም ይመልከቱ።

18:4. በአማኝ ልብ ውስጥ ያለው የጥበብ ምንጭ ያለማቋረጥ የጥበብ ቃላትን ያፈልቃል። 5. ሊታይ የሚገባው የጉዳዩ ትክክለኛነት እንጂ ሰው አይደለም። 6,7. ክፉ ሰዎች ባልተገራ አንደበታቸው በራሳቸው ላይ ምንኛ ጥፋት ያመጣሉ! 8. ጠብ የሚዘሩ ሰዎች ምንኛ ነውረኞች ናቸው! ከቅናት ትንሽ ጅማሮዎችም ምንኛ ገዳይ ውጤቶች ይጠበቃሉ! 9. ግዴታን አለመፈጸም፣ እንዲሁም በግዴታ ውስጥ ያሉ መዘናጋቶች፣ ኃጢአትን እንደመፈጸም ሁሉ ለነፍስ ገዳይ ናቸው። 10,11. በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠውና በእርሱ በኩል የሚሠራው መለኮታዊ ኃይል፣ በጌታ ለሚታመን አማኝ ጠንካራ ግንብ ይፈጥራል። በዚህ ዓለም ድርሻውንና መዝገቡን ያደረገው ባለጸጋ መከላከያው ምንኛ አታላይ ነው! በራሱ ግምት ጠንካራ ከተማና ከፍ ያለ ግንብ ነው፤ ምክንያቱም እጅግ በሚያስፈልገው ጊዜ ይከዳዋል። እንደ አዳኝ የናቁትን የዚያን ዳኛ ጻድቅ ቁጣ ይጋለጣሉ። 12. ልብ በኩራት ከተነሳ በኋላ ውድቀት ይመጣል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6