መጽሐፈ ምሳሌ 16

AMHNIVአማርኛ33 ጥቅሶች4:01 አዳምጥ
አዳምጥ 4:01 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የልብ ዕቅድ የሰው ነው፤ የአንደበት መልስ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

2ለሰው መንገዱ ሁሉ ንጹሕ መስሎ ይታየዋል፤ መነሻ ሐሳቡ ግን በእግዚአብሔር ይመዘናል።

3የምታደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ዐደራ ስጥ፤ ዕቅድህም ሁሉ ይሳካልሃል።

4እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ለራሱ ዐላማ ሠርቶአል፤ ክፉዎችንም እንኳ ለጥፋት ቀን አዘጋጅቶአል።

5እግዚአብሔር በልብ የሚታበዩትን ሁሉ ይጸየፋል፤ እነርሱም ከቅጣት እንደማያመልጡ በርግጥ ዕወቅ።

6በፍቅርና በታማኝነት ኀጢአት ይሰረያል፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ሰው ከክፋት ይርቃል።

7የሰው መንገድ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሰኘው፣ ጠላቶቹ እንኳ አብረውት በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል።

8ከጽድቅ ጋር ጥቂቱ ነገር፣ በግፍ ከሚገኝ ብዙ ትርፍ ይሻላል።

9ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ እግዚአብሔር ግን ርምጃውን ይወስንለታል።

10የንጉሥ ከንፈሮች እንደ አምላክ ቃል ይናገራሉ፤ አንደበቱ ፍትሕን ያዛባ ዘንድ አይገባም።

11ሐቀኛ መስፈሪያና ሚዛን ከእግዚአብሔር ናቸው፤ በከረጢት ውስጥ ያሉት መመዘኛዎችም ሁሉ ሥራዎቹ ናቸው።

12ክፋትን ማድረግ ለነገሥታት አጸያፊ ነው፤ ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና።

13ነገሥታት በታማኝ ከንፈሮች ደስ ይላቸዋል፤ እውነት የሚናገረውን ሰው ይወዱታል።

14የንጉሥ ቊጣ የሞት መልእክተኛ ነው፤ ጠቢብ ሰው ግን ቊጣውን ያበርዳል።

15የንጉሥ ፊት ሲፈካ ሕይወት አለ፤ በጎነቱም ዝናብ እንዳዘለ የበልግ ደመና ነው።

16ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት፣ ከብርም ማስተዋልን መምረጥ ምንኛ ይበልጣል!

17የቅኖች ጐዳና ከክፋት የራቀ ነው፤ መንገዱንም የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል።

18ትዕቢት ጥፋትን፣ የእብሪት መንፈስም ውድቀትን ትቀድማለች።

19በተዋረደ መንፈስ ከተጨቈኑት ጋር መሆን፣ ከትዕቢተኞች ጋር ብዝበዛን ከመካፈል ይሻላል።

20ምክርን የሚሰማ ይለመልማል፤ በእግዚአብሔርም የሚታመን ቡሩክ ነው።

21ልባቸው ጠቢብ የሆነ አስተዋዮች ይባላሉ፤ ደስ የሚያሰኙ ቃላትም ዕውቀትን ያዳብራሉ።

22ማስተዋልን ገንዘብ ላደረጋት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ቂልነት ግን በተላሎች ላይ ቅጣት ታመጣባቸዋለች።

23የጠቢብ ሰው ልብ አንደበቱን ይመራል፤ ከንፈሮቹም ዕውቀትን ያዳብራሉ።

24ደስ የሚያሰኝ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ፣ ለዐጥንትም ፈውስ ነው።

25ለሰው ቀና መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤ በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል፤

26ሠራተኛን የዕለት ጒርስ ፍላጎቱ ታታሪ ያደርገዋል፤ ራቡም ይገፋፋዋል።

27ወራዳ ሰው ክፋትን ያውጠነጥናል፤ ንግግሩም እንደሚለበልብ እሳት ነው።

28ጠማማ ሰው ጠብን ይዘራል፤ ሐሜተኛም የቅርብ ወዳጆችን ይለያያል።

29ክፉ ሰው ባልንጀራውን ያባብለዋል፤ መልካም ወዳልሆነውም መንገድ ይመራዋል።

30በዐይኑ የሚጠቅስ ሰው ጠማማነትን ያውጠነጥናል፤ በከንፈሩ የሚያሽሟጥጥም ወደ ክፋት ያዘነብላል።

31ሽበት የክብር ዘውድ ነው፤ የሚገኘውም በጽድቅ ሕይወት ነው።

32ታጋሽ ሰው ከጦረኛ፣ ስሜቱን የሚገዛም ከተማን በጒልበቱ ከሚይዝ ይበልጣል።

33ዕጣ በጕያ ውስጥ ይጣላል፤ ውሳኔው በሙሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

ማብራሪያ

16:1 የእግዚአብሔር የሚያድሰው ጸጋ ብቻውን ልብን ለእያንዳንዱ መልካም ሥራ ያዘጋጃል። ይህ እኛ ማንኛውንም ጥበባዊና መልካም ነገር ለማሰብ ወይም ለመናገር ከራሳችን በራሳችን በቂ እንዳልሆንን ያስተምረናል። 2. ድንቁርና፣ ትዕቢትና ራስን ማሞገስ ስለራሳችን ምግባር ከፊል ዳኞች ያደርጉናል። 3. የእንክብካቤህን ሸክም በእግዚአብሔር ላይ ጣል፤ በእርሱ በማመንና በመደገፍም ከእርሱ ዘንድ ተወው።

16:4. እግዚአብሔር ክፉዎችን እርስ በእርሳቸው ጻድቅ ፍርድን እንዲፈጽሙባቸው ይጠቀማል፤ በመጨረሻም በጥፋታቸው ይከብራል። 5. ኃጢአተኞች ራሳቸውንም እርስ በእርሳቸውም ቢያበረቱም፣ ከእግዚአብሔር ፍርድ አያመልጡም። 6. በክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ምሕረትና እውነት፣ የአማኞች ኃጢአቶች ይወገዳሉ፤ የኃጢአትም ኃይል ይሰበራል። 7. ሁሉንም ልቦች በእጁ የያዘው እርሱ፣ የሰውን ጠላቶች ከእርሱ ጋር ሰላም እንዲሆኑ ማድረግ ይችላል። 8. በሐቀኝነት የተገኘ ትንሽ ንብረት፣ በክፋት ከተገኘ ትልቅ ንብረት ይልቅ የተሻለ ጥቅም ይሰጣል። 9. ሰዎች የእግዚአብሔርን ክብር አላማቸው አድርገው፣ ፈቃዱንም መመሪያቸው ቢያደርጉ፣ እርሱ በመንፈሱና በጸጋው እርምጃቸውን ይመራል። 10. የምድር ነገሥታትና ፈራጆች ጻድቅ ይሁኑ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ይግዙ። 11. በሰውና በሰው መካከል ባሉ ግብይቶች ፍትሕን መፈጸም የእግዚአብሔር ሥርዓት ነው።

16:12. ሥልጣኑን በአግባቡ የሚጠቀም መሪ፣ ያ ለእርሱ እጅግ አስተማማኝ ጥበቃው መሆኑን ያገኛል። 16:13. ዓላማቸውን በአግባቡ መግለጽ የሚያውቁትን ሰዎች ሥልጣን ላይ አስቀምጡ። 16:14,15.

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6