የማቴዎስ ወንጌል 20

AMHNIVአማርኛ34 ጥቅሶች5:03 አዳምጥ
አዳምጥ 5:03 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1“መንግሥተ ሰማይ ለወይኑ ቦታ ሠራተኞችን ለመቅጠር ማልዶ የወጣን የአትክልት ስፍራ ባለቤት ትመስላለች።

2በቀን አንዳንድ ዲናር ሊከፍላቸው ከተስማሙ በኋላ ሠራተኞቹን በወይኑ ቦታ አሰማራቸው።

3“ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ በመውጣት ሥራ ፈትተው በገበያ ቦታ የቆሙትን ሌሎች ሰዎች አግኝቶ፣

4‘እናንተም ሄዳችሁ በወይኔ ቦታ ሥሩ፤ ተገቢውን ክፍያ እሰጣችኋለሁ’ አላቸው፤

5እነርሱም ሄዱ። “ከቀኑ በስድስት ሰዓትና በዘጠኝ ሰዓት ላይ ወጥቶ ሌሎች የቀን ሠራተኞችን ቀጠረ።

6ከሰዓት በኋላ በዐሥራ አንድ ሰዓት ገደማ ወጥቶ ቆመው የነበሩ ሌሎች ሰዎች አገኘና፣ ‘ቀኑን ሙሉ ያለ ሥራ እዚህ ለምን ትቆማላችሁ?’ በማለት ጠየቃቸው።

7“እነርሱም፣ ‘የሚቀጥረን ሰው ስለ አጣን ነው’ አሉት። “እርሱም፣ ‘እናንተም ሄዳችሁ በወይኔ ቦታ ሥሩ’ አላቸው።

8“በመሸም ጊዜ የወይኑ አትክልት ባለቤት የሠራተኞቹን ተቈጣጣሪ፣ ‘ኋላ ከመጡት ጀምረህ መጀመሪያ እስከመጡት ድረስ ያሉትን ሠራተኞች በሙሉ ጥራና ደመወዛቸውን ክፈላቸው’ አለው።

9“በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ገደማ የተቀጠሩት ሠራተኞች ቀርበው፣ እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ።

10በመጀመሪያ የተቀጠሩት ሲቀርቡ ብልጫ ያለው ክፍያ የሚያገኙ መስሎአቸው ነበር፤ ነገር ግን እነርሱም አንዳንድ ዲናር ተከፈላቸው።

11ክፍያውን ሲቀበሉ በባለቤቱ ላይ በማጕረምረም፣

12‘እነዚህ በመጨረሻ የተቀጠሩት አንድ ሰዓት ብቻ ሲሠሩ፣ ቀኑን ሙሉ በሥራ ስንደክምና በፀሐይ ስንንቃቃ ከዋልነው ጋር እንዴት እኩል ትከፍለናለህ?’ አሉት።

13“እርሱም አንደኛውን ሠራተኛ እንዲህ አለው፤ ‘ወዳጄ ሆይ፤ በደል አላደረስሁብህም፤ በአንድ ዲናር ለመሥራት ከእኔ ጋር ተስማምተህ አልነበረምን?

14በል ድርሻህን ይዘህ ሂድ፤ ለአንተ የሰጠሁትን ያህል በመጨረሻ ለመጣውም ሰው መስጠት እፈልጋለሁ።

15ታዲያ በራሴ ገንዘብ የፈለግሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ ቸር በመሆኔ ምቀኝነት ያዘህን?’

16“ስለዚህ ኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።”

17ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ላይ ሳለ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወስዶ እንዲህ አላቸው፤

18“እንግዲህ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ የሰው ልጅ ለካህናት አለቆችና ለኦሪት ሕግ መምህራን አልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም እንዲሞት ይፈርዱበታል፤

19እንዲያላግጡበት፣ እንዲገርፉትና እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሣል።”

20ከዚያም፣ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋር ወደ ኢየሱስ ቀርባ በፊቱ ተንበርክካ እየሰገደች፣ አንድ ነገር እንዲያደርግላት ለመነችው።

21እርሱም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም፣ “እነዚህ ሁለት ልጆቼ፣ በመንግሥትህ አንዱ በቀኝህ፣ አንዱ በግራህ እንዲቀመጡ ፍቀድ” አለችው።

22ኢየሱስም፣ “የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ትችላላችሁን?” አላቸው። እነርሱም፣ “እንችላለን” አሉት።

23እርሱም፣ “ከጽዋዬ በርግጥ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን በቀኜና በግራዬ መቀመጥ አባቴ ላዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምፈቅደው ነገር አይደለም” አላቸው።

24ዐሥሩም ይህንን በሰሙ ጊዜ፣ ሁለቱን ወንድማማቾች ተቈጧቸው።

25ኢየሱስም አንድ ላይ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “የአሕዛብ ገዢዎች በሕዝባቸው ላይ ጌቶች እንደሚሆኑ፣ ባለ ሥልጣኖቻቸውም በኀይል እንደሚገዟቸው ታውቃላችሁ፤

26በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም። ከእናንተ ትልቅ መሆን የሚፈልግ አገልጋያችሁ ይሁን፤

27የበላይ ለመሆን የሚሻም የእናንተ የበታች ይሁን፤

28የሰው ልጅ እንዲያገለግሉት ሳይሆን፣ ለማገልገልና ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ለመስጠት መጥቶአልና።”

29ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከኢያሪኮ ወጥተው ሲሄዱ ብዙ ሕዝብ ተከተለው።

30በዚያም ሁለት ዐይነ ስውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው ነበር፤ ኢየሱስም በዚያ ማለፉን ሲሰሙ፣ “ጌታ ሆይ፤ የዳዊት ልጅ ማረን!” በማለት ጮኹ።

31ሕዝቡም በግሣጼ ቃል ዝም እንዲሉ ነገሯቸው፤ እነርሱ ግን አምርረው በመጮኽ፣ “ጌታ ሆይ፤ የዳዊት ልጅ ማረን!” አሉ።

32ኢየሱስም ቆም ብሎ ጠራቸውና፣ “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው።

33እነርሱም፣ “ዐይኖቻችን እንዲያዩ እንፈልጋለን” አሉት።

34ኢየሱስም ራራላቸው፤ ዐይኖቻቸውንም ዳሰሰ፣ ወዲያው አዩ፤ ተከተሉትም።

ማብራሪያ

ማቴዎስ 20:1-16 የዚህ ምሳሌ ቀጥተኛ ዓላማ፣ አይሁድ በመጀመሪያ ወደ ወይን እርሻው ቢጠሩም እንኳ፣ በመጨረሻ ወንጌል ለአሕዛብ ይሰበካል እንዲሁም ከአይሁድም ጋር እኩል መብቶችንና ጥቅሞችን እንደሚያገኙ ማሳየት ይመስላል። ምሳሌው በአጠቃላይ መልኩም ሊተገበር የሚችል ሲሆን፣ የሚከተሉትን ያሳያል፦ 1. እግዚአብሔር ለማንም ዕዳ የለበትም። 2. ብዙዎች በሃይማኖት የመጨረሻ ሆነው የጀመሩት እና ትንሽ ተስፋ የነበራቸው፣ አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሔር በረከት፣ ብዙ እውቀት፣ ጸጋ እና ጠቃሚነት ላይ እንደሚደርሱ። 3. የዋጋ ክፍያ ለቅዱሳን እንደሚሰጥ፣ ነገር ግን እንደ ንስሐ መግባታቸው ጊዜ ሳይሆን።

የሚታየውን ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ይገልጻል፣ እንዲሁም 'የኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ' የሚለውን አዋጅ በተለያዩ ትርጉሞቹ ያብራራል። ወደ እግዚአብሔር አገልግሎት እስክንቀጠር ድረስ፣ ቀኑን ሙሉ በስራ ፈትነት እንቆማለን፦ ኃጢአተኛ ሁኔታ፣ ለሰይጣን የባርነት ሁኔታ ቢሆንም፣ የስራ ፈትነት ሁኔታ ተብሎ ሊጠራ ይችላል። ገበያው ዓለም ነው፣ ከዚያም በወንጌል ተጠርተናል። ኑ፣ ከዚህ ገበያ ውጡ። ለእግዚአብሔር የሚሰራ ስራ ቸልተኝነትን አይቀበልም። አንድ ሰው በስራ ፈትነት ወደ ገሃነም መሄድ ይችላል፣ ነገር ግን ወደ ሰማይ ለመሄድ የሚፈልግ ትጉ መሆን አለበት።

የሮማው ዲናር በዘመናችን ገንዘብ ሰባት ተኩል ሳንቲም አካባቢ ነበር፤ በዚያን ጊዜም ለአንድ ቀን ድጋፍ የሚበቃ ደሞዝ ነበር። ይህ ለእግዚአብሔር የምናደርገው ታዛዥነት ዋጋ ከስራዎች ወይም ከዕዳ የመጣ መሆኑን አያረጋግጥም፤ ሁሉንም ባደረግን ጊዜ፣ የማንጠቅም ባሮች ነን፤ ነገር ግን ከፊት ለፊታችን ሽልማት እንዳለ ያመለክታል፤ ሆኖም ማንም በዚህ ግምት ተነስቶ ንስሐን እስከ እርጅናው አያስተላልፍ። አንዳንዶች በአሥራ አንደኛው ሰዓት ወደ ወይን እርሻው ተላኩ፤ ነገር ግን ከዚያ በፊት ማንም አልቀጠራቸውም ነበር። አሕዛብ በአሥራ አንደኛው ሰዓት ገቡ፤ ወንጌል ከዚህ በፊት ለእነሱ አልተሰበከም ነበር። በሦስተኛው ወይም በስድስተኛው ሰዓት የወንጌል ጥሪ ተደርጎላቸው የካዱት፣ በአሥራ አንደኛው ሰዓት፣ እነዚህ እንዳሉት፣ 'ማንም አልቀጠረንም' ማለት አይኖርባቸውም። ስለዚህ፣ ማንንም ተስፋ ለማስቆረጥ ሳይሆን፣ ሁሉንም ለማንቃት፣ 'አሁን ተቀባይነት ያለው ጊዜ ነው' የሚለው መታወስ አለበት።

የመለኮታዊው ጸጋ ብልጽግና በትዕቢተኞች ፈሪሳውያንና በስም ክርስቲያኖች ዘንድ በግልጽ ያጉረመርማሉ። በእኛ ውስጥ የትንሽነት ስሜት፣ ሌሎች ደግሞ የእግዚአብሔርን ሞገስ ምልክቶች ከልክ በላይ እንዳላቸው የማሰብ ዝንባሌ አለ፤ እኛም ብዙ እንደምንሰራ፣ ሌሎች ደግሞ ለእግዚአብሔር ስራ ትንሽ እንደሚያደርጉ የማሰብ ዝንባሌ አለ። ነገር ግን እግዚአብሔር ለሌሎች ጸጋ ከሰጠ፣ ለእነሱ ደግነት ነው እንጂ ለእኛ በደል አይደለም። ሥጋውያን ዓለማውያን በዚህ ዓለም ላለ የዲናር ዋጋቸው ከእግዚአብሔር ጋር ይስማማሉ፤ የሕይወታቸውንም ክፍል በዚህ ዓለም ይመርጣሉ። ታዛዥ ምእመናን ደግሞ በሌላው ዓለም ላለ የዲናር ዋጋቸው ከእግዚአብሔር ጋር ይስማማሉ፣ እናም እንዲህ እንደተስማሙ ማስታወስ አለባቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6