ሰቆቃው ኤርምያስ 1

AMHNIVአማርኛ22 ጥቅሶች6:20 አዳምጥ
አዳምጥ 6:20 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ፣ እንዴት የተተወች ሆና ቀረች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው፣ እርሷ እንዴት እንደ መበለት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፣ አሁን ባሪያ ሆናለች።

2በሌሊት አምርራ ታለቅሳለች፤ እንባዋ በጉንጮቿ ላይ ይወርዳል፤ ከወዳጆቿ ሁሉ መካከል፣ የሚያጽናናት ማንም የለም፤ ባልንጀሮቿ ሁሉ ከድተዋታል፤ ጠላቶቿም ሆነዋል።

3በመከራና በመረገጥ ብዛት ይሁዳ ተማርካ ሄደች፤ በሕዝቦችም መካከል ተቀመጠች፤ የምታርፍበትንም ስፍራ አጣች፤ በጭንቀቷ መካከል ሳለች፣ አሳዳጆቿ ሁሉ አገኟት።

4የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ፤ በዓላቷን ለማክበር የሚመጣ የለምና፤ በበሮቿ ሁሉ የሚገባና የሚወጣ የለም፤ ካህናቷ ይቃትታሉ፤ ደናግሏ ክፉኛ አዝነዋል፤ እርሷም በምሬት ትሠቃያለች።

5ባላጋሮቿ ገዦቿ ሆኑ፤ ጠላቶቿ ተመችቶአቸዋል፤ ከኀጢአቷ ብዛት የተነሣ፣ እግዚአብሔር ከባድ ሐዘን አምጥቶባታል። ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው፣ ወደ ግዞት ሄደዋል።

6የጽዮን ሴት ልጅ፣ ግርማ ሞገሷ ሁሉ ተለይቶአታል፤ መሳፍንቶቿ፣ መሰማሪያ እንዳጣ ዋልያ ናቸው፤ በአሳዳጆቻቸው ፊት፣ በድካም ሸሹ።

7በተጨነቀችባቸውና በተንከራተተችባቸው ቀናት፣ ኢየሩሳሌም በጥንት ዘመን የነበራትን፣ ሀብት ሁሉ ታስባለች፤ ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ፣ የረዳት ማንም አልነበረም፤ ጠላቶቿ ተመለከቷት፤ በመፈራረሷም ሣቁ።

8ኢየሩሳሌም ከባድ ኀጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህም የረከሰች ሆናለች፤ ያከበሯት ሁሉ ናቋት፤ ዕራቍቷን ሆና አይተዋታልና፤ እርሷ ራሷ ታጒረመርማለች፤ ወደ ኋላዋም ዘወር ብላለች።

9ርኵሰቷ በቀሚሷ ላይ ታየ፤ ወደ ፊት የሚሆንባትን አላሰበችም፤ አወዳደቋ አስደንጋጭ ሆነ፤ የሚያጽናናትም አልነበረም፤ “እግዚአብሔር ሆይ፤ መከራዬን ተመልከት፤ ጠላት ድል አድርጎአልና!”

10በሀብቷ ሁሉ ላይ፣ ጠላት እጁን ዘረጋ፤ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ፣ የከለከልሀቸው፣ ጣዖት የሚያመልኩ አሕዛብ፣ ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።

11እንጀራ በመፈለግ፣ ሕዝቧ ሁሉ በሥቃይ ይጮኻል፤ በሕይወት ለመኖር፣ የከበረ ሀብታቸውን በምግብ ይለውጣሉ፤ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ ተመልከተኝም፤ እኔ ተዋርጃለሁና።”

12“እናንት መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ፤ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? ተመልከቱ፤ እዩም፤ በጽኑ ቍጣው ቀን፣ እግዚአብሔር ያመጣብኝን፣ በእኔ ላይ የደረሰውን፣ የእኔን መከራ የመሰለ መከራ አለን?

13“ከከፍታ ስፍራ እሳትን ላከ፤ ወደ ታች ወደ ዐጥንቶቼም ሰደደው፤ በእግሮቼ ላይ መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም ጣለኝ፤ ቀኑን ሙሉ በማድከም፣ ባዶ አድርጎ አስቀመጠኝ።

14“ኀጢአቶቼ ቀንበር ሆኑ፤ በእጆቹ አንድ ላይ ተገመዱ፤ በዐንገቴም ላይ ተጭነዋል፤ ኀይሌንም አዳከመ፤ ልቋቋማቸው ለማልችላቸው፣ እርሱ አሳልፎ ሰጠኝ።

15“በውስጤ ያሉትን ተዋጊዎች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ተቃወመ፤ ጒልማሶቼን ለማድቀቅ፣ ሰራዊት በላዬ ላይ ጠራ፤ ድንግሊቱን የይሁዳ ሴት ልጅ፣ እግዚአብሔር በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረገጣት።

16“የማለቅሰው ስለ እነዚህ ነገሮች ነው፤ ዐይኖቼ በእንባ ተሞልተዋል፣ ሊያጽናናኝ የቀረበ፣ መንፈሴንም ሊያረጋጋ የሞከረ ማንም የለም፤ ጠላት በርትቶአልና ልጆቼ ተጨንቀዋል።”

17ጽዮን እጆቿን ዘረጋች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ ጎረቤቶቹ ጠላቶቹ እንዲሆኑ፣ እግዚአብሔር በያዕቆብ ላይ ትእዛዝ አውጥቶአል፤ ኢየሩሳሌምም በመካከላቸው፣ እንደ ርኵስ ነገር ተቈጠረች።

18“እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔ ግን በትእዛዙ ላይ ዐመፅ አድርጌ ነበር፤ እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ወይዛዝርቶቼና ጐበዛዝቶቼ፣ ተማርከው ሄደዋል።

19“ወዳጆቼን ጠራኋቸው፤ እነርሱ ግን ከዱኝ፤ ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ፣ ሕይወታቸውን ለማትረፍ፣ ምግብ ሲፈልጉ፣ በከተማዪቱ ውስጥ አለቁ።

20“አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት ተጨንቄአለሁ! በውስጤ ተሠቃይቼአለሁ፤ በልቤ ታውኬአለሁ፤ እጅግ ዐመፀኛ ሆኛለሁና፤ በውጭ ሰይፍ ይፈጃል፤ በቤትም ውስጥ ሞት አለ።

21“ሰዎች የሥቃይ ልቅሶዬን ሰሙ፤ የሚያጽናናኝ ግን ማንም የለም፤ ጠላቶቼ ሁሉ ጭንቀቴን ሰሙ፤ አንተ ባደረግኸውም ደስ አላቸው፤ አቤቱ የተናገርኻት ቀን ትምጣ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሁኑ።

22“ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይቅረብ፤ ከኀጢአቴ ሁሉ የተነሣ፣ በእኔ ላይ እንዳደረግኽብኝ፣ በእነርሱም ላይ አድርግባቸው፤ የሥቃይ ልቅሶዬ በዝቶአል፤ ልቤም ደክሞአል።”

ማብራሪያ

፩፥፩-፲፩ ነቢዩ አንዳንድ ጊዜ በራሱ አንደበት ይናገራል፤ ሌሎች ጊዜያት ደግሞ ኢየሩሳሌም እንደተቸገረች ሴት ትናገራለች፥ ወይም ደግሞ አንዳንድ አይሁዳውያን። ይህ መግለጫ የአይሁድን ሕዝብ መከራ ያሳያል። ኢየሩሳሌም በኃጢአቷ ብዛት የተነሳ ምርኮኛና ባሪያ ሆነች፤ ከመከራም ዕረፍት አላገኘችም። ታላቁን ጠላታችን የሆነውን ኃጢአትን በእኛ ላይ እንዲነግሥ ከፈቀድን፥ በፍትሕ ሌሎች ጠላቶችም በእኛ ላይ እንዲነግሡ ይፈቀድላቸዋል። ሕዝቡ ጫፍ የደረሰ ረሃብና መከራን ታገሰ። በዚህ አሳዛኝ ሁኔታ ኢየሩሳሌም ኃጢአቷን ተናዘዘች፥ ጌታም ጉዳይዋን እንዲመለከት ተማጸነችው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ መካከል ታላቅ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፤ በአውራጆች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሆናለች። አማርኛ ENGNIV How deserted lies the city, once so full of people! How like a widow is she, who once was great among the nations! She … English BCV ኣሌፍ። እዛ ብህዝቢ መሊኣ ዝነበረት ከተማ፥ ከመይ ኢላ ሰብ ዘይብላ ተረፈት! እዛ ኣብ ማእኸል ህዝብታት ዓባይ ዝነበረት፥ ሕዚ ኸመይ ኢላ መበለት ኮነት! እዛ ኣብ ማእኸል ኣውራጃታት ልዕልቲ… ትግርኛ GAZBIB Mandarri dur namni keessa guutee ture, amma attamitti duwwaatti hafte! Isheen saba warra kaan gidduutti guddoo turte, a… Afaan Oromoo BCV GIZ አሌፍ። እፎ ነበረት ባሕቲታ ሀገር እንተ ምልእት ሕዝበ ወኮነት መበለተ እንተ ትኳንን እሕዛበ ወትኴንን በሓውርተ ገብአት ውስተ እደ ጸዋር። giz GAZGAZ Mandarri dur namni keessa guutee ture, amma attamitti duwwaatti hafte! Isheen saba warra kaan gidduutti guddoo turte, a… Afaan Oromoo BCV aksum ኣሌፍ። እዛ ብህዝቢ መሊኣ ዝነበረት ከተማ፥ ከመይ ኢላ ሰብ ዘይብላ ተረፈት! እዛ ኣብ ማእኸል ህዝብታት ዓባይ ዝነበረት፥ ሕዚ ኸመይ ኢላ መበለት ኮነት! እዛ ኣብ ማእኸል ኣውራጃታት ልዕልቲ… ትግርኛ SWAHSUV Jinsi mji huu ukaavyo ukiwa, Huo uliokuwa umejaa watu! Jinsi alivyokuwa kama mjane, Yeye aliyekuwa mkuu kati ya mataifa… Kiswahili