ትንቢተ ኤርምያስ 39

AMHNIVአማርኛ18 ጥቅሶች4:06 አዳምጥ
አዳምጥ 4:06 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ኢየሩሳሌም የተያዘችው እንዲህ ነበር፤ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰራዊቱን ሁሉ አሰልፎ በመምጣት ኢየሩሳሌምን ከበባት።

2በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ አንደኛው ዓመት በአራተኛው ወር፣ በወሩም በዘጠነኛው ቀን የከተማዪቱ ቅጥር ተሰበረ።

3የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፦ የሳምጋሩ ኤርጌል ሳራስር፣ ዋና አዛዡ ናቦሠርሰኪም፣ ከፍተኛው ሹም ኤርጌል ሳራሳር እንዲሁም ሌሎቹ የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ገብተው በመካከለኛው በር ተቀመጡ።

4የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ እነርሱን ባዩ ጊዜ ሸሹ፤ በሌሊት በንጉሡ አትክልት ስፍራ በኩል አድርገው በሁለቱ ቅጥር መካከል ከከተማዪቱ ወጡ፤ ወደ ዓረባም አመሩ።

5የባቢሎን ሰራዊት ግን ተከትሎ አሳደዳቸው፣ በኢያሪኮም ሜዳ ደርሶባቸው ሴዴቅያስን ያዘ፤ ማርከውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ በዚያም ፍርድ ወሰነበት።

6የባቢሎንም ንጉሥ በሪብላ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች፣ አባታቸው እያየ ዐረዳቸው፤ የይሁዳን መሳፍንት ሁሉ ገደላቸው፤

7የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ ወደ ባቢሎን ሊወስደውም በናስ ሰንሰለት አሰረው።

8ባቢሎናውያን ቤተ መንግሥቱንና የሕዝቡን ቤት በእሳት አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ።

9የባቢሎን መንግሥት የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፤ በከተማዪቱ የቀረውን ሕዝብ ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።

10ንብረት ያልነበራቸውን ድኾች ግን የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ በይሁዳ ምድር ተዋቸው፤ በዚያ ጊዜም የወይን አትክልት ቦታና የዕርሻ መሬት ሰጣቸው።

11የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በክብር ዘበኞቹ አዛዥ በናቡዘረዳን በኩል ስለ ኤርምያስ እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤

12“ውሰደውና እንክብካቤ አድርግለት፤ የሚፈልገውን ነገር ፈጽምለት እንጂ አትጒዳው።

13የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ ዋና አዛዡ ናቡሸዝባን፣ ከፍተኛ ሹሙ ኤርጌል ሳራስር እንዲሁም ሌሎች የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፣

14ልከው ኤርምያስን ከዘበኞች አደባባይ አስወጡት፤ የሳፋን ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወደ ቤቱ እንዲወስደው በዐደራ ሰጡት፤ ኤርምያስም በራሱ ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።

15ኤርምያስ በዘበኞች አደባባይ ታስሮ በነበረበት ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ እንዲህ ሲል መጣ፤

16“ሂድና ለኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ ‘የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እድገት ሳይሆን ጥፋት በማምጣት በዚህች ከተማ ላይ ቃሌን እፈጽማለሁ፤ በዚያ ጊዜ በዐይንህ እያየህ ይህ ይፈጸማል።

17አንተን ግን በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ለምትፈራቸው ሰዎች ዐልፈህ አትሰጥም።

18እታደግሃለሁ፤ በእኔ ታምነሃልና በሕይወት ታመልጣለህ እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ”

ማብራሪያ

39:1-10 ኢየሩሳሌም እጅግ ብርቱ ነበረችና ነዋሪዎቿ ጠላት ሊገባባት እንደማይችል ያምኑ ነበር። ነገር ግን ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቆጣ፣ ጥበቃውንም እንዲያነሳ ስላደረገ፣ ከዚያም እንደሌሎች ከተሞች ደካማ ሆነች። ሴዴቅያስ ዓይኖቹ ወጡለት፤ ስለዚህም የእግዚአብሔርን ቃል ብሩህ ብርሃን የጨፈነ እርሱ በጨለማ ተፈረደበት። የእግዚአብሔርን ቃል የማያምኑት፣ በክስተቱ ይረጋገጥላቸዋል። የአምላካዊው አሠራር አስደናቂ ለውጦችን ተመልከቱ፤ የምድራዊ ንብረት ምን ያህል እንደማይጸናም እዩ። የአምላካዊው አሠራር ጽድቅንም እዩ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት፤ አማርኛ ENGNIV This is how Jerusalem was taken: In the ninth year of Zedekiah king of Judah, in the tenth month, Nebuchadnezzar king o… English BCV ኢየሩሳሌም ምስ ተትሓዘት፥ ሴዴቅያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ብታሽዓይ ዓመት ብዓስራይ ወርሒ ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎንን ኵሎም ሰራዊቱን መፂኦም ንኢየሩሳሌም ከበብዋ። ትግርኛ GAZBIB Zedeqiiyaan mootii Yihudaa erga ta'ee waggaa salgaffaa isaatti, waggichattiis ji'a kurnaffaatti Nebukadnezaar mootiin B… Afaan Oromoo BCV GIZ ወኮነ ሶበ ተእኀዘት ኢየሩሳሌም በታስዕ ዓመተ መንግሥቱ ለሴዴቅያስ ንጉሥ ይሁዳ በዓሥር ወርኅ መጽአ ናቡከደነፆር ንጉሠ ባቢሎን ወኵሉ ኃይሉ ኀበ ኢየሩሳሌም፤ ወዐገትዋ ለኢየሩሳሌም ወተቃተሉ። giz GAZGAZ Zedeqiiyaan mootii Yihudaa erga ta'ee waggaa salgaffaa isaatti, waggichattiis ji'a kurnaffaatti Nebukadnezaar mootiin B… Afaan Oromoo BCV aksum ኢየሩሳሌም ምስ ተትሓዘት፥ ሴዴቅያስ ኣብ ይሁዳ ምስ ነገሰ፥ ብታሽዓይ ዓመት ብዓስራይ ወርሒ ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎንን ኵሎም ሰራዊቱን መፂኦም ንኢየሩሳሌም ከበብዋ። ትግርኛ SWAHSUV Hata ikawa, Yerusalemu ulipotwaliwa, (katika mwaka wa kenda wa Sedekia, mfalme wa Yuda, katika mwezi wa kumi, Nebukadre… Kiswahili