ትንቢተ ኤርምያስ 34

AMHNIVአማርኛ22 ጥቅሶች5:34 አዳምጥ
አዳምጥ 5:34 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደናፆርና ሰራዊቱ ሁሉ፣ በግዛቱም ሥር ያሉ መንግሥታትና ሕዝቦች ሁሉ ኢየሩሳሌምንና በአካባቢዋ የሚገኙትን ከተሞች ይወጉ በነበረ ጊዜ፣ እንዲህ የሚል ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፤

2“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሴዴቅያስ ሄደህ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ አሳልፌ ልሰጣት ነው፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል፤

3አንተም በእርግጥ ትያዛለህ ዐልፈህም ለእርሱ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም። የባቢሎንን ንጉሥ በዐይኖችህ ታየዋለህ፤ ፊት ለፊትም ያነጋግርሃል፤ ወደ ባቢሎንም ትሄዳለህ።

4“ ‘ነገር ግን፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፤ በሰይፍ አትሞትም፤

5በሰላም ትሞታለህ። ሕዝቡ ከአንተ በፊት ለነበሩት ነገሥታት አባቶችህ ክብር በቀብራቸው ጊዜ እሳት እንዳነደዱ፣ በቀብርህም ጊዜ ስለ ክብርህ እሳት ያነዳሉ፤ “ዋይ ዋይ ጌታችን!” እያሉም ያለቅሱልሃል፤ እኔ ራሴ ይህን ቃል ተናግሬአለሁና፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ”

6ነቢዩ ኤርምያስ ይህን ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው፤

7በዚህም ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳ ከተሞች ለኪሶንና ዓዜቃን እየወጋ ነበር፤ ከተመሸጉት የይሁዳ ከተሞችም የቀሩት እነዚሁ ብቻ ነበሩና።

8ንጉሡ ሴዴቅያስ ባሪያዎችን ነጻ ለማውጣት ከኢየሩሳሌም ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ካደረገ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ።

9እያንዳንዱ ሰው፣ ዕብራዊ የሆነውን ወንድ ባሪያውንና ዕብራዊት የሆነችውን ሴት ባሪያውን ነጻ ማውጣት ነበረበት፤ ማንም ሰው አይሁዳዊ ወንድሙን በባርነት መግዛት አልነበረበትም።

10በዚህ ቃል ኪዳን የተስማሙት ባለሥልጣኖችና ሕዝቡ ሁሉ ወንድ ወይም ሴት ባሪያዎቻቸውን ነጻ ለመልቀቅና ከእንግዲህ ባሪያ አድርገው ላይገዟቸው ተስማሙ።

11በኋላ ግን ሐሳባቸውን ቀይረው ነጻ የለቀቋቸው ባሪያዎቻቸውን እንዲመለሱ አደረጓቸው፤ እንደ ገናም ባሪያ አድርገው ገዟቸው።

12ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፤

13“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በባርነት ከተገዙበት ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ፣ ከአባቶቻችሁ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ፤

14‘ራሱን በባርነት ለእናንተ የሸጠውን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ በየሰባት ዓመቱ ነጻ ትለቃላችሁ፤ ስድስት ዓመት ከተገዛላችሁ በኋላ ነጻ ታወጡታላችሁ።’ አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም ወደ እኔ አላዘነበሉም።

15እናንተም አሁን ንስሓ በመግባት በፊቴ ትክክለኛ ነገር አደረጋችሁ፤ እያንዳንዳችሁም ለወገኖቻችሁ ነጻነት ዐወጃችሁ፤ ስሜ በሚጠራበት ቤትም በፊቴ ቃል ኪዳን ገባችሁ።

16ነገር ግን ተመልሳችሁ ስሜን አረከሳችሁ፤ ወደ ፈለጉበት እንዲሄዱ ነጻ የለቀቃችኋቸውንም ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎቻችሁን መለሳችሁ፤ እንደ ገናም ባሪያዎቻችሁ አደረጋችኋቸው።

17“ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ለወንድሞቻችሁና ለወገኖቻችሁ ነጻነት አላወጃችሁምና አልታዘዛችሁኝም። እንግዲህ እኔ ‘ነጻነት’ ዐውጅላችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር። ይኸውም በሰይፍ፣ በቸነፈርና በራብ የምትወድቁበት ‘ነጻነት’ ነው። ለምድር መንግሥታት ሁሉ መሠቀቂያ አደርጋችኋለሁ።

18ኪዳኔን ያፈረሱትንና በፊቴ የገቡትን የኪዳኑን ቃል ያልፈጸሙትን ሰዎች ሥጋውን ሁለት ቦታ ከፍለው በመካከሉ እንዳለፉት፣ እንደ እንቦሳው አደርጋቸዋለሁ።

19የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን መሪዎች፣ የቤተ መንግሥቱን ባለሟሎች፣ ካህናቱንና በእንቦሳው ሥጋ መካከል ያለፉትን ሕዝብ ሁሉ፣

20ነፍሳቸውን ለሚሹ ጠላቶቻቸው አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።

21“የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን፣ ነፍሳቸውን ለሚሹ ጠላቶቻቸው ይኸውም ለጊዜው እናንተን ከመውጋት ለተመለሱ ለባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።

22እነሆ፤ አዛቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደዚህችም ከተማ እንደ ገና እመልሳቸዋለሁ። እነርሱም ይወጓታል፤ ይይዟታል፤ በእሳትም ያቃጥሏታል። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባቸው፣ ባድማ አደርጋቸዋለሁ።

ማብራሪያ

34:1-7 ሰደቅያስ ከተማይቱ እንደምትወድቅ፣ እርሱም ምርኮኛ ሆኖ እንደሚሞት፣ ሆኖም በተፈጥሮ ሞት እንደሚሞት ተነገረው። በወህኒ ቤት ውስጥ በንስሐ መኖርና መሞት፣ በቤተ መንግሥት ውስጥ ንስሐ ሳይገቡ ከመኖርና ከመሞት ይመረጣል።

34:8-22 አንድ አይሁዳዊ ከሰባት ዓመት በላይ ባርነት ውስጥ መያዝ የለበትም። ይህን ሕግ እነርሱም አባቶቻቸውም አፍርሰው ነበር። የውጊያ ከበባው እንደሚነሳ ተስፋ በተደረገ ጊዜ፣ የለቀቋቸውን አገልጋዮች እንደገና ወደ አገልግሎ…

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያ… አማርኛ ENGNIV While Nebuchadnezzar king of Babylon and all his army and all the kingdoms and peoples in the empire he ruled were figh… English BCV ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎንን ኵሉ ሰራዊቱን፥ እቶም ኣብ ትሕቲ ኢዱ ዝግዝኡ ዝነበሩ ዅሎም መንግስታት ምድርን ኵሎም ህዝብታትን፥ ምስ ኢየሩሳሌምን ምስ ኵለን ከተማታታን፥ ይዋግኡ ኣብ ዝነበሩሉ… ትግርኛ GAZBIB Yeroo Nebukadnezaar mootiin Baabilon loltoota isaa hundumaa fi mootummoota biyya lafaa irra jiran warra harka isaa jala… Afaan Oromoo BCV GIZ ቃል ዘኮነ ኀበ ኤርምያስ እምኀበ እግዚአብሔር፡ ናቡከደነፆር ንጉሠ ባቢሎን ወኵሉ ሠራዊቱ፡ ወኵሎሙ መንግሥታተ ምድር ያነሥኡ እደ፡ ወኵሉ አሕዛበ ምድር ይትቃተልዋ ለኢየሩሳሌም፡ ወለኵሉ አሕጉ… giz GAZGAZ Yeroo Nebukadnezaar mootiin Baabilon loltoota isaa hundumaa fi mootummoota biyya lafaa irra jiran warra harka isaa jala… Afaan Oromoo BCV aksum ናቡከደነፆር ንጉስ ባቢሎንን ኵሉ ሰራዊቱን፥ እቶም ኣብ ትሕቲ ኢዱ ዝግዝኡ ዝነበሩ ዅሎም መንግስታት ምድርን ኵሎም ህዝብታትን፥ ምስ ኢየሩሳሌምን ምስ ኵለን ከተማታታን፥ ይዋግኡ ኣብ ዝነበሩሉ… ትግርኛ SWAHSUV Neno hili ndilo lililomjia Yeremia, kutoka kwa Bwana, hapo Nebukadreza, mfalme wa Babeli, na jeshi lake lote, na falme … Kiswahili