ትንቢተ ኢሳይያስ 29

AMHNIVአማርኛ24 ጥቅሶች5:08 አዳምጥ
አዳምጥ 5:08 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1ዳዊት የሰፈረብሽ ከተማ፣ አርኤል፣ አርኤል ወዮል ዓመት በዓመት ላይ ጨምሪ፣ ዐውደ ዓመትሽም ይቀጥል።

2ነገር ግን አርኤልን እከባለሁ፤ ታለቅሳለች፤ ዋይ ዋይ ትላለች፤ ለእኔም እንደ መሠዊያ ስፍራ ትሆንልኛለች።

3በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤ በቅጥር እከብሻለሁ፤ የከበባ ዐምባም ሠርቼ አስጨንቅሻለሁ።

4ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ ንግግርሽ ከትቢያ እየተጒተመተመ ይወጣል፤ ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።

5ነገር ግን ብዙ ጠላቶችሽ እንደ ትቢያ ብናኝ፣ መንጋ ጨካኞችም በነፋስ እንደሚነጻ ገለባ ይሆናሉ። ድንገት ሳይታሰብም፣

6የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በነጐድጓድ፣ በምድር መናወጥና በታላቅ ድምፅ፣ በዐውሎ ነፋስና በኀይለኛ ሞገድ ፈጽሞ በሚባላም የእሳት ነበልባል ይመጣል።

7አርኤልን የሚወጋ የአሕዛብ ሁሉ መንጋ፣ በእርሷና በምሽጓ ላይ አደጋ የሚጥልና የሚከባት፣ እንደ ሕልም በሌሊትም እንደሚታይ ራእይ ይሆናል።

8የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ዐድሮ፣ ነገር ግን ሲነቃ ራቡ እንዳልለቀቀው፣ የጠማውም ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ዐድሮ፣ ነገር ግን ሲነቃ እንደ ዛለና ጥማቱም እንዳልተወው፣ የጽዮንን ተራራ የሚወጋ፣ የአሕዛብ መንጋ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።

9ነሁሉሉ፤ ተደነቁም፤ ተጨፈኑ፤ እስከ ወዲያኛውም ታውራችሁ ቅሩ፤ በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ስከሩ፤ በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገዳገዱ።

10እግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ጥሎባችኋል፤ ዐይኖቻችሁን፣ ነቢያትን ጨፍኖባችኋል፤ ራሶቻችሁን፣ ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል።

11ይህ ሁሉ ራእይ በጥቅልል መጽሐፍ ውስጥ እንደ ታሸገ ቃል ሆኖባችኋል። ጥቅልሉንም መጽሐፍ ማንበብ ለሚችል ሰው፣ “እባክህ አንብልን” ብላችሁ ብትሰጡት፣ “ታሽጓልና አልችልም” ይላችኋል።

12ደግሞም ጥቅልሉን መጽሐፍ ማንበብ ለማይችል ሰው፣ “እባክህን አንብብልን” ብላችሁ ብትሰጡ፣ “ማንበብ አልችልም” ይላችኋል።

13እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ የሚያመልከኝም፣ ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ብቻ ነው።

14ስለዚህ ይህን ሕዝብ በድንቅ ላይ ድንቅ ነገር እያደረግሁ፣ ዳግመኛ አስገርመዋለሁ፤ የጥበበኞች ጥበብ ይጠፋል፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ይበናል።”

15ሐሳባቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ፣ ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ለሚወርዱ ሥራቸውንም በጨለማ ለሚያከናውኑ፣ “ማን ያየናል? ማንስ ያውቅብናል” ለሚሉ ወዮላቸው!

16እናንተ ነገሮችን ትገለብጣላችሁ ሸክላ ሠሪውን እንደ ሸክላ ትመለከታላችሁ፤ ለመሆኑ፣ ተሠሪ ሠሪውን፣ “እርሱ አልሠራኝም” ይለዋልን? ሸክላ የሠራውን፣ “እርሱ ምንም አያውቅም” ይለዋልን?

17ሊባኖስ ወደ ለም ዕርሻነት ለመለወጥ፣ ለም የሆነውም መሬት ወደ ዱርነት ለመለወጥ ጥቂት ጊዜ አልቀረውምን?

18በዚያን ጊዜ ደንቈሮ የጥቅልሉን መጽሐፍ ቃል ይሰማል፤ የዐይነ ስውሩም ዐይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ።

19ትሑታን በእግዚአብሔር፣ ምስኪኖችም በእስራኤል ቅዱስ እንደ ገና ሐሤት ያደርጋሉ።

20ጨካኞች እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ፌዘኞችም በነው ይጠፋሉ፤ ለክፋት ያደፈጡ ሁሉ ይወገዳሉ።

21ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፣ በተከሳሽ ላይ ወጥመድ የሚዘረጉ፣ በሐሰት ምስክር ፍትሕን ከንጹሓን የሚቀሙ ይቈረጣሉ።

22ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው እግዚአብሔር ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፤ “ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም፤ ፊቱም ከእንግዲህ አይለዋወጥም።

23በመካከላቸው የእጄ ሥራ የሆኑ፣ ልጆቻቸውን ሲያዩ፣ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብን ቅዱስ ቅድስና ያውቃሉ፤ በእስራኤልም አምላክ ፊት በፍርሀት ይቆማሉ።

24በመንፈስ የሳቱ ያስተውላሉ፤ የሚያጒረመርሙም ምክር ይቀበላሉ።”

ማብራሪያ

29:1-8 አርኤል የሚለው ቃል የሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያን ሊያመለክት ይችላል። ኢየሩሳሌም የውጭ ሃይማኖታዊ አገልግሎቶች ሰዎችን ከፍርድ ነፃ እንደማያደርጓቸው ታውቅ። ግብዞች ፈጽሞ እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም፣ ከእርሱም ጋር ሰላም ሊያደርጉ አይችሉም። እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ ለረጅም ጊዜ፣ በመላእክት ሠራዊት አማካይነት፣ ኢየሩሳሌምን ለመጠበቅና ለማዳን በዙሪያዋ ሰፍሮ ነበር፤ አሁን ግን እርሱ በእርሷ ላይ ተዋጋ። ትዕቢተኛ እይታዎችና ትዕቢተኛ ንግግሮች ትሕትናን በሚያመጡ መለኮታዊ አደራሮች ይወርዳሉ። የኢየሩሳሌም ጠላቶች ጥፋት ትንቢት ተነግሮለታል። የሰናክሬም ሠራዊት እንደ ሕልም አለፈ፤ እንዲሁ በየዘመናቱ ሁሉ በእግዚአብሔር መሠዊያና አምልኮ ላይ የሚዋጉ ብዙኃን ይወድቃሉ። ኃጢአተኞች ከሚያጽናኗቸው ሕልሞቻቸው በፍጥነት በሲኦል ሥቃይ ውስጥ ይነቃሉ።

29:9-16 የኃጢአተኞች በኃጢአት መንገዳቸው የመዘናጋት ሁኔታ ለልቅሶና ለድንጋጤ ምክንያት ነው። ምሁራኑ በጭፍን ጥላቻ ምክንያት መለኮታዊ ትንቢቶች ግልጽ ያልሆኑ መሆናቸውን ተናገሩ፤ ድሆቹም የመማር እጦታቸውን አሳበቡ። መጽሐፍ ቅዱስ የተማረም ይሁን ያልተማረ ሰው፣ በቀና ልብና በሚማር መንፈስ ማጥናት እስኪጀምር ድረስ የታተመ መጽሐፍ ነው፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን እውነትና ፈቃድ ይማር ዘንድ። እግዚአብሔርን ማምለክ እርሱን መቅረብ ነው። ልብ በፍቅሩና በፍርሃቱ የተሞላ ከሆነ፣ ከአፌታው አፍ ይናገራል፤ ነገር ግን ሃይማኖታቸው የከንፈር አገልግሎት ብቻ የሆኑ ብዙዎች አሉ። ወደ እግዚአብሔር የሚያወሩ መስለው ሲቀርቡ፣ የብዙ ከንቱ ነገሮችን እያሰቡ ነው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6