ትንቢተ ሕዝቅኤል 11

AMHNIVአማርኛ25 ጥቅሶች4:45 አዳምጥ
አዳምጥ 4:45 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፤ ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር አመጣኝ። በበሩም መግቢያ ላይ ሃያ አምስት ሰዎች ነበሩ፤ በእነርሱም መካከል የሕዝቡን መሪዎች የዓዙርን ልጅ ያእዛንያንና የበናያስን ልጅ ፈላጥያንን አየሁ።

2እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ሰዎች ክፋትን የሚያቅዱና በዚህችም ከተማ ላይ ተንኰልን የሚመክሩ ናቸው።

3እነርሱም፣ “ቤቶች የሚሠሩበት ጊዜ ቅርብ አይደለምን? ይህች ከተማ ድስት ናት፤ እኛም ሥጋ ነን’ ብለዋል።

4ስለዚህ ትንቢት ተናገርባቸው፤ የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር።”

5የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዬ ወረደ እንዲህም አለኝ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፤ እናንተ እንዲህ ብላችኋል፤ እኔ ግን የልባችሁን ሐሳብ ዐውቃለሁ።

6በዚህች ከተማ ብዙ ሰው ገድላችኋል፤ መንገዶቿንም ሬሳ በሬሳ አድርጋችኋል።’

7“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዚያ የጣላችኋቸው ሬሳዎች እነርሱ ሥጋ ናቸው፤ ይህችም ከተማ ድስት ናት፤ እናንተን ግን ከውስጧ አወጣችኋለሁ።

8ሰይፍን ፈርታችኋል፤ እኔም ሰይፍ እልክባችኋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

9ከከተማዪቱ አውጥቼ ለባዕዳን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ፍርድንም አመጣባችኋለሁ።

10በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ በዚያ ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

11ይህች ከተማ ድስት አትሆንላችሁም፤ እናንተም በውስጧ ሥጋ አትሆኑም፤ በእስራኤልም ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤

12በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እናንተ በዙሪያችሁ ያሉትን አሕዛብ ሥርዐት ተከተላችሁ እንጂ ትእዛዜን አልፈጸማችሁም ሕጌንም አልጠበቃችሁምና።”

13ትንቢት እየተናገርሁ ሳለ፣ የበናያስ ልጅ ፈላጥያ ሞተ፤ እኔም በግንባሬ ተደፍቼ፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮ! የእስራኤልን ቅሬታ ፈጽመህ ታጠፋለህን?” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኽሁ።

14የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

15“የሰው ልጅ ሆይ፤ ወንድሞችህ፣ የራስህ ዘመዶችና የእስራኤል ቤት ሁሉ፤ ‘ከእግዚአብሔር ርቀዋል፤ ይህች ምድር ርስት ሆና ለኛ ተሰጥታናለች’ ብለው የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የተናገሩባቸው ናቸው።

16“ስለዚህ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በአሕዛብ መካከል ብሰድዳቸውም፤ በአገሮች መካከል ብበታትናቸውም፣ በሄዱባቸው አገሮች ሁሉ ለጥቂት ጊዜ መቅደስ ሆኜአቸዋለሁ’ ”።

17“ስለዚህ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ከአሕዛብ መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸው አገሮች እመልሳችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እንደ ገና እሰጣችኋለሁ።”

18“ወደዚያ በተመለሱ ጊዜ የረከሱ ምስሎቿንና ጸያፍ ተግባሯን ያስወግዳሉ።

19የማያወላውል ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ አዲስ መንፈስ በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ድንጋዩን ልብ ከውስጣቸው አወጣለሁ፤ ሥጋ ልብም እሰጣቸዋለሁ።

20ስለዚህ ትእዛዜን ይፈጽማሉ፤ ሕጌን ይጠብቃሉ። እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።

21ነገር ግን ልባቸው ወደ ረከሱ ምስሎቻቸውና ወደ ጸያፍ ተግባራቸው ያዘነበለውን እንደ ሥራቸው እከፍላቸዋለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”

22ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፤ መንኰራኵሮቹም በአጠገባቸው ነበሩ፤ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበር።

23የእግዚአብሔርም ክብር ከከተማዪቱ ውስጥ ተነሥቶ ወጣ፤ ከከተማዪቱም በስተ ምሥራቅ ካለው ተራራ በላይ ቆም አለ።

24መንፈስም ወደ ላይ አነሣኝ፤ በእግዚአብሔርም መንፈስ በተሰጠው ራእይም በባቢሎን ምድር ወደ ነበሩት ምርኮኞች አመጣኝ። ከዚያም ያየሁት ራእይ ከእኔ ወጥቶ ሄደ፤

25እኔም እግዚአብሔር ያሳየኝን ነገር ሁሉ ለምርኮኞቹ ተናገርሁ።

ማብራሪያ

11:1-13

ሰይጣን ሰዎችን የሚመጣውን ፍርድ እርግጠኛ ያልሆነ እንደሆነ አድርገው እንዲመለከቱት ማሳመን በማይችልበት ጊዜ፣ ሩቅ እንደሆነ አድርገው እንዲያዩት በማሳመን ዓላማውን ያሳካል። እነዚህ ምስኪን ገዥዎች እንዲህ ለማለት ይደፍራሉ፦ “በዚህች ከተማ ውስጥ፣ በፈላ ድስት ውስጥ እንዳለ ሥጋ ደህና ነን፤ የከተማዋ ግንቦች ለእኛ እንደ ናስ ግድግዳ ይሆናሉ፤ ከበባ ከሚያደርጉብን ሰዎች ከድስት እሳት ምንም እንደማይደርስበት ሁሉ፣ እኛም ምንም ጉዳት አይደርስብንም።” ኃጢአተኞች ራሳቸውን ለጥፋት ሲያሞካሹ፣ ከቀጠሉ ሰላም እንደማያገኙ የመንገር ጊዜው አሁን ነው። በከተማይቱ ውስጥ የሚቀሩት በእሷ ውስጥ የሚቀበሩት ብቻ ይሆናሉ። በጣም ደህና ነን ብለው የሚመኩ ሰዎች እጅግ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ናቸው። እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ አንዳንድ ኃጢአተኞችን ለይቶ ለሌሎች ማስጠንቀቂያ እንዲሆኑ በማድረግ ደስ ይለዋል። ጰልትያ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም እንደሞተ፣ ወይስ የትንቢቱ ፍጻሜ ሲቃረብ እንደሆነ እርግጠኛ አይደለም።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG መንፈስም አነሣኝ፤ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደሚመለከት ወደ እግዚአብሔር ቤትም ወደ ምሥራቁ በር አመጣኝ። እነሆም፥ በበሩ መግቢያ ሀያ አምስት ሰዎች ነበሩ፥ በመካከላቸውም የሕዝቡን አለቆች የዓዙር… አማርኛ ENGNIV Then the Spirit lifted me up and brought me to the gate of the house of the Lord that faces east. There at the entrance… English BCV መንፈስ ኣልዓለኒ፤ ናብቲ ወገን ምብራቕ፥ ናብቲ ናብ ምብራቕ ኣቢሉ ዝርኢ ደገ ቤት እግዚኣብሄር ድማ ወሰደኒ፤ እንሆ ኸዓ፥ ኣብቲ ኣፍ ደገ፥ ዕስራን ሓሙሽተን ሰብኡት ነበሩ፤ ኣብ ማእኸሎም ድ… ትግርኛ GAZBIB Hafuurri ol na fuudhee, gara karra mana Waaqayyoo isa gara ba'a-biiftuutti gara galee jirutti na geesse; balbala karich… Afaan Oromoo BCV GIZ ወአንሥአኒ መንፈስ ወወሰደኒ ኅበ አንቀጸ ቤተ እግዚአብሔር ዘይኔጽር መንገለ አንጻረ ጽባሕ፤ ወረከብኩ ኆኅተ ዴዴ ዕሥራ ወኃምስተ እደው ወርኢክዎ በማእከሎሙ ለመልአኮሙ ለኢኮንያን ወልደ አዙር… giz GAZGAZ Hafuurri ol na fuudhee, gara karra mana Waaqayyoo isa gara ba'a-biiftuutti gara galee jirutti na geesse; balbala karich… Afaan Oromoo BCV aksum መንፈስ ኣልዓለኒ፤ ናብቲ ወገን ምብራቕ፥ ናብቲ ናብ ምብራቕ ኣቢሉ ዝርኢ ደገ ቤት እግዚኣብሄር ድማ ወሰደኒ፤ እንሆ ኸዓ፥ ኣብቲ ኣፍ ደገ፥ ዕስራን ሓሙሽተን ሰብኡት ነበሩ፤ ኣብ ማእኸሎም ድ… ትግርኛ SWAHSUV Tena roho ikaniinua, ikanileta hata lango la upande wa mashariki wa nyumba ya Bwana, lililoelekea upande wa mashariki; … Kiswahili