1ሕያው የሆነው መንፈስህ በሁሉም ነገር ውስጥ ወርዷል!
2ቀስ በቀስም አጥፊዎችን ታርማለህ፥ኃጢአታቸውን ታስታውሳቸዋለህ፥ ትገስጻቸዋለህም፤ጌታ ሆይ ይህንንም ያደረግኸውከክፋት እንዲርቁና ባንተም ያምኑ ዘንድ ነው።
3በቅድስት መሬትህ ላይየነበሩትን የቀደሙ ሰፋሪዎች
4በሥራዎቻቸው አስጸያፊነት ጠላሃቸው፤ያልተቀደሱ ስርዓቶቻቸውንና አስማቶቻቸውን አልወደድህም።
5ሕፃናትን የሚገድሉ ምሕረት የለሾች፥በበዓላት ላይ የሰውን ስጋና ደም፥የሆድ ዕቃውንም የሚበሉ ሰው በላዎች፥የምሥጢራዊ ወንድማማችነት ምልምሎች፥
6እኒያ ራሳቸውን ማዳን የማይችሉ ሕፃናትን የሚገድሉ ወላጆች፥በአባቶቻችን እጅ ይጠፉ ዘንድ ፈረድህ፤
7ከሁሉም በላይ የምትወዳት ይህች መሬትምየእግዚአብሔርን ልጆች ታስተናግድ ዘንድ ፈቀድህ።
8እነኚህንም እንኳ ሰዎች በመሆናቸው ራራኽላቸው፤ከሠራዊትህ ፊት ፊት ተርቦችን በመላክጥቂት በጥቂት አጠፋሃቸው።
9በተፋፋመ ጦርነት መሀል ክፉዎችን በጻድቃኖች እጅ መጣል ችግርህ አልነበረም፤ወይንም እነርሱን በአስፈሪ አውሬዎች አልያም በቁጣ ቃል ልታጠፋቸውም በቻልህ ነበር፤
10ምንም እንኳ እነርሱ በክፋት የተጠነሰሱ መሆናቸውን ብታውቅም፥በተፈጥሮአቸው ክፉዎች ቢሆኑም፥
11ከመጀመሪያው የተረገሙ ዘሮች መሆናቸውሐሳባቸውን እንደማይሽሩ ብትገነዘብም፥ፍርድህን ቀስ በቀስ በማሳየትይጸጸቱ ዘንድ እድል ሰጥተሃቸዋል፤ስለ ኃጢአታቸው ያልቀጣሃቸው ማንንም ፈርተህ አልነበረም።
12ያደረግኸው ምንድነው?በማለት ሊጠይቅህ የሚደፍር፥ፍርድህንም የሚቃወም የለምና።የፈጠርኻቸውን ሕዝቦች ብትደመስስ ከሳሽህ ከቶ ማነው?ክፉዎችን በመደገፍ አንተን የማጋፈጥ ይኖራልን?
13ካንተ በላይ ስለ ሁሉም የሚጨነቅ፥ፍርድህም ትክክለኛ እንደሆነ የምታረጋግጥለት፥ሌላ አምላክ የለም።
14ንጉሥም ቢሆን ፈላጭ ቆራጭ፤ብይንህን ስላሳለፍክባቸው ሰዎችደፍሮ ሊናገርህ አይችልም።
15አንተ ትክክለኛ በመሆንህ፥ዓለምን በፍትህ ታስተዳድራለች፤በንጹሐን ላይ ቅጣትና ፍርድ፥ከኃያልነትህ ጋር የማይሄድ ሆኖ ታየዋለህ።
16ኃያልነትህ አዳኝነትህ፥ልዕልናህ ምሕረትህ ያጐናጽፋሉና፤
17ፍጹማዊ ሥልጣንህን ሰዎች ላለማመን ሲዳዳቸው፥አውቀው የሚደፍሩትንም ግራ አጋባቸው።
18አንተ ግን ኃይልህን ተቆጣጥረህ፥ፍርድህን ሚዛናዊ አድርገህ፥ከታላቅ ምሕረት ጋር ታስተዳድረናለህ፤አንተ ከፈቀድህ ሥልጣኑ በእጅህ ነውና።
19እንዲህ በማድረግህ ሕዝብህን አስተማርህ፤ጻድቅ ሰው ለሌሎች ደግ መሆን እንዳለበት ገለጽህ፤ለልጆችህ መልካም ተስፋን፥ለኃጢአታቸውም ንስሐን ሰጠሃቸው።
20ሞት የተፈረደባቸው ቢሆንም እንኳ፥የልጆችህን ጠላቶች ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታናበላላ መልክ ከቀጣህ፥ከክፋትም ይርቁ ዘንድ ጊዜና ቦታን ከሰጠሃቸው፥
21ለአባቶቻቸው በመሐላ፥ በቃል ኪዳንና በተስፋ ቃልየገባህላቸውን ሰዎች ዘሮችና ያንተን ልጆችትክክለኛውን ትኩረት ሰጥተህ ያልፈረድከውስለምንድን ነው?
22ስለዚህ በጠላቶቻችን ላይ ቅጣትህን ባለማክበድህ፥እኛም በፍርዳችን ላይ ያንተን ደግነትእናስብ ዘንደ አስተማርኸን፤ለፍርድም በቀረብን ጊዜ ምሕረትህን እንጠባበቃለን።
23ከንቱና ክፋት የተሞላበት ሕይወት የሚመሩ ሰዎችበገዛ ራሳቸው መጥፎ ተግባር እንዲሠቃዩ ያደረግኸውም ለዚሁ ነው።
24በስሕተት መንገድ ብዙ ተጉዘዋል፤መርዘኞቹንና የጠሉትን እንስሳት በማምለክ፥ክፉና ደጉን እንዳልለዩ ለጋ ሕፃናትም ታልለዋልና።
25አንተም ምንም እንደማያውቁ ሕፃናትየሰው መሳቂያ በማድረግ ቀጣሃቸው።
26ከተሳልቆው ተግሣጽ ያልተማሩ ግንየእግዚአብሔርን ታላቅ ፍርድ በቶሎ ይቀበላሉ።
27እነርሱን ያሰቃያቸው፥አቤቱታቸውን ያቀረቡባቸው፥አምላኮቻቸው ያደረጉአቸው እነኛው ፍጡራን፥የቀጧቸውም እነርሱ መሆናቸውን በእውነተኛው ብርሃናቸው ተመልክተዋል፤እስከ አሁን ድረስ አናውቅህም ያሉትን ጌታእውነተኛው አምላክ እንደሆነ አወቁ፤የመጨረሻውም ቅጣት በእነርሱ ላይ ወደቀ።