2ኛ ዜና መዋዕል 1

AMHNIVአማርኛ17 ጥቅሶች3:44 አዳምጥ
አዳምጥ 3:44 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበር፣ እጅግም ስላገነነው፣ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን በመንግሥቱ ላይ ተደላድሎ ተቀመጠ።

2ከዚያም ሰሎሞን ለመላው እስራኤል፣ ለሻለቆች፣ ለመቶ አለቆች፣ ለዳኞች፣ ለእስራኤል መሪዎች ሁሉ እንዲሁም ለየቤተ ሰቡ አለቆች ተናገረ።

3የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የአምላክ የመገናኛ ድንኳን በዚያ ስለ ነበር፣ ሰሎሞንና መላው ጉባኤ በገባዖን ወዳለው ኰረብታ ሄዱ።

4በዚያ ጊዜ ዳዊት የአምላክን ታቦት ከቂሪያት ይዓሪም በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎ ወዳዘጋጀለት ስፍራ አምጥቶት ነበር፤

5ይሁን እንጂ የሆር ልጅ፣ የኡሪ ልጅ ባስልኤል የሠራው መሠዊያ በገባዖን በእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ፊት ለፊት ይገኝ ነበር፤ ስለዚህ ሰሎሞንና ጉባኤው ይህንኑ ፈለጉ።

6ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ወዳለው ወደ ናሱ መሠዊያ ወጥቶ በላዩ ላይ አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።

7በዚያ ሌሊት እግዚአብሔር ለሰሎሞን ተገልጦ፣ “እንድሰጥህ የምትፈልገውን ሁሉ ጠይቀኝ” አለው።

8ሰሎሞን እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ በጎነት አድርገህለታል፤ እኔንም በእግሩ ተክተህ አንግሠኸኛል።

9አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ያነገሥኸኝ ብዛቱ እንደ ትቢያ በሆነ ሕዝብ ላይ ስለ ሆነ፣ ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው ተስፋ ይጽና።

10ይህን ሕዝብ ለመምራት እንድችል፣ ጥበብና ዕውቀትን ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ይህን ታላቅ ሕዝብህን ማን ሊገዛ ይችላል?”

11እግዚአብሔርም ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “የልብህ መሻት ይህ ስለ ሆነ፣ ብልጥግናና ሀብት ወይም የጠላቶችህን ነፍስ ወይም ረጅም ዕድሜ ስላልጠየቅህ፣ ነገር ግን ባነገሥሁህ ሕዝቤ ላይ የምትገዛበትን ጥበብና ዕውቀት ስለ ጠየቅህ፣

12ጥበብና ዕውቀት ይሰጥሃል፤ እንዲሁም ከአንተ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ያላገኘውን፣ ከአንተ በኋላም የሚነሣው የማያገኘውን ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር እሰጥሃለሁ።”

13ሰሎሞንም የመገናኛው ድንኳን ካለበት ከገባዖን ኰረብታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በእስራኤልም ላይ ነገሠ።

14ሰሎሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት፤ እነርሱንም በሠረገላ ከተሞችና እርሱ ባለበት በኢየሩሳሌም ከተማ አኖራቸው።

15ንጉሡም ወርቁና ብሩ በኢየሩሳሌም እንደ ተራ ድንጋይ እንዲበዛ፣ ዝግባውም በየኰረብታው ግርጌ እንደሚገኝ የሾላ ዛፍ እንዲበዛ አደረገ።

16የሰሎሞንም ፈረሶች የመጡት ከግብፅና ከቀዌ ነበር፤ ከቀዌ የገዟቸውም የንጉሡ ነጋዴዎች ነበሩ።

17ከግብፅ ያስገቧቸውም አንዱን ሠረገላ በስድስት መቶ ሰቅል ብር፣ አንዱን ፈረስ በአንድ መቶ አምሳ ሰቅል ብር ገዝተው ነው። እነዚህንም ደግሞ ለኬጢያዊያንና ለሦርያውያን ነገሥታት ሁሉ ይሸጡላቸው ነበር።

ማብራሪያ

1:1-17 የሰሎሞን የጥበብ ምርጫ፣ ኃይሉና ሀብቱ።

ሰሎሞን ንግሡን የጀመረው እግዚአብሔርን በሚፈራ መንፈስ ለሕዝብ በሚታይ ሁኔታ የእግዚአብሔርን መሠዊያ በመጎብኘት ነበር። የአሁንን ነገሮች በብርቱ የሚከታተሉ ሰዎች ቅር ይላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አቅርቦት የሚሰጡ ሰዎች፣ እጅግ ብዙ ባይኖራቸውም፣ ታላቅ መጽናናትን ያገኛሉ። ይህንን ዓለም ግባቸው የሚያደርጉ ሰዎች፣ የዘላለምን ዓለም ማግኘት ያቅታቸዋል፣ በዚህ ዓለምም ቅር ይላቸዋል። ነገር ግን የዘላለምን ዓለም ግባቸው የሚያደርጉ ሰዎች፣ ያንን ብቻ ሳይሆን ያገኛሉ፣ በዚያም ውስጥ ሙሉ እርካታን ያገኛሉ፤ በተጨማሪም በሕይወታቸው ጎዳና ለእነርሱ የሚበጅ ከሆነ የዚህን ዓለምም ነገር ያገኛሉ። እንግዲያውስ ሰዎች በአብዛኛው የሚመኟቸውን ታላላቅ ነገሮች ሳንሻ ረክተን እንኑር፣ ነገር ግን እነዚያ ነገሮች አብዛኛውን ጊዜ ለነፍስ ገዳይ ወጥመዶች ይሆናሉ።

ቁጥር 13-17 እዚህ ላይ፣

1. ሰሎሞን መንግሥቱን መጀመሩ (ቁ. 13)፦ ከድንኳኑ ፊት ለፊት መጣና በእስራኤል ላይ ነገሠ።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6