1ኛ ጢሞቴዎስ 5

AMHNIVአማርኛ25 ጥቅሶች4:32 አዳምጥ
አዳምጥ 4:32 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1አረጋዊውን ሰው እንደ አባትህ ቈጥረህ ምከረው እንጂ በኀይለ ቃል አትናገረው። ወጣት ወንዶችን እንደ ወንድሞች ተቀበላቸው፤

2እንዲሁም አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ወጣት ሴቶችን ደግሞ እንደ እኅቶች በፍጹም ንጽሕና አስተናግዳቸው።

3በርግጥ ችግረኛ የሆኑትን መበለቶች ተንከባከባቸው።

4አንዲት መበለት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሯት፣ እነዚህ ልጆች የራሳቸውን ቤተ ሰብ በመርዳትና ለወላጆቻቸውም ብድራትን በመመለስ ከሁሉ በፊት እምነታቸውን በተግባር ለማሳየት መማር ይገባቸዋል፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነውና።

5በርግጥ መበለት የሆነች፣ ብቻዋንም የምትኖር ተስፋዋን በእግዚአብሔር ላይ ታደርጋለች፤ ለጸሎትና የእግዚአብሔርን ርዳታ ለመለመን ሌሊትና ቀን ትተጋለች።

6ምድራዊ ደስታን የምትሻዋ መበለት ግን በሕይወት ብትኖርም የሞተች ናት።

7ማንም የሚነቀፍበት ነገር እንዳይኖር፣ ይህንም ትእዛዝ ለሕዝቡ ስጥ።

8አንድ ሰው ዘመዶቹን፣ በተለይም የቅርብ ቤተ ሰቡን የማይረዳ ከሆነ ሃይማኖቱን የካደ፣ ከማያምንም ሰው ይልቅ የባሰ ክፉ ነው።

9ዕድሜዋ ከሥልሳ ዓመት ያነሰ መበለት በመዝገብ ላይ አትጻፍ፤ ደግሞም የአንድ ባል ሚስት የነበረች ልትሆን ይገባል፤

10ልጆችን በማሳደግ፣ እንግዶችን በመቀበል፣ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ለበጎ ምግባር ሁሉ ራሷን በመስጠት በመልካም ሥራም የተመሰከረላት መሆን አለባት።

11ወጣት መበለቶችን ግን እንዲህ ባለው መዝገብ አትጻፋቸው፤ ምክንያቱም ሥጋዊ ፍላጎታቸው ለክርስቶስ በገቡት ቃል ላይ በሚያይልበት ጊዜ ለማግባት ይሻሉና።

12በዚህም ፍርድን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ፤ በመጀመሪያ የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና።

13በተጨማሪም ሥራ መፍታትንና ከቤት ቤት መዞርን ይለምዳሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን፣ የማይገባውን እየተናገሩ ሐሜተኞችና በሰው ጒዳይም ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ።

14ስለዚህ ባል የሞተባቸው ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ፣ ልጆች እንዲወልዱ፣ ቤታቸውን እንዲያስተዳድሩ፣ ጠላትም የሚነቅፍባቸውን ነገር እንዳያገኝ እመክራለሁ።

15በርግጥ ከዚህ በፊት አንዳንዶቹ ሰይጣንን ለመከተል ዘወር ብለዋል።

16አማኝ የሆነች ማንኛዋም ሴት በቤተ ሰቧ ውስጥ መበለቶች ቢኖሯት፣ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ መበለቶችን ብቻ መርዳት እንድትችል እርሷው ትርዳቸው እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሸክም እንዲሆኑ አትተዋቸው።

17ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ የሚያስተዳድሩ፣ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚተጉ ሽማግሌዎች ዕጥፍ ክብር ይገባቸዋል፤

18መጽሐፍም፣ “እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሠር፤” ደግሞም፣ “ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል” ይላልና።

19በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ካልተደገፈ በቀር በሽማግሌ ላይ የሚቀርብ ክስ አትቀበል።

20ሌሎች አይተው እንዲጠነቀቁ ኀጢአት የሚሠሩትን በጉባኤ ፊት ገሥጻቸው።

21በእግዚአብሔርና በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በተመረጡትም መላእክት ፊት እነዚህን ትእዛዛት ያለ አድልዎ እንድትጠብቅና አንዳችም ነገር በማበላለጥ እንዳታደርግ ዐደራ እልሃለሁ።

22በማንም ላይ እጅ ለመጫን አትቸኵል፤ ከሌሎችም ጋር በኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ።

23ለሆድህና ደጋግሞ ለሚነሣብህ ሕመም፣ ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣበት እንጂ ከእንግዲህ ውሃ ብቻ አትጠጣ።

24የአንዳንድ ሰዎች ኀጢአት ግልጽ ነው፤ ከእነርሱም ቀድሞ ፍርድ ቦታ ይደርሳል፤ ሌሎችን ግን ኀጢአታቸው ይከተላቸዋል።

25መልካም ሥራም እንደዚሁ ግልጽ ነው፤ ግልጽ ያልሆነ ቢኖርም እንኳ ተሰውሮ አይቀርም።

ማብራሪያ

5:1,2 ለዕድሜና ለሥፍራ ክብር ሊሰጥ ይገባል። ወጣቶች ስሕተት ከፈጸሙ፣ ስሕተታቸውን ለመፈለግ ተመኝተን ወይም ለመንቀፍ በማሰብ ሳይሆን፣ ይልቁንም መልካምነታቸውን ለማውጣትና እንዲሻሻሉ በመመኘት ሊገሰጹ ይገባል። ተግሣጽ ለሚገባቸው በሚገሰጹበት ጊዜ፣ ከፍተኛ የዋህነትና ጥንቃቄ አስፈላጊ ነው።

፭፥፫-፰ በእውነት መበለቶች የሆኑትን አክብሩ፣ እርዷቸውና ደግፏቸው። ወላጆቻቸው ችግር ላይ ከሆኑ እና እነርሱም ለመርዳት የሚችሉ ከሆኑ፣ በሙሉ ችሎታቸው ሊረዷቸው ይገባል። መበለትነት የብቸኝነትና የችግር ሁኔታ ነው፤ ነገር ግን መበለቶች በጌታ ይታመኑ፣ በጸሎትም ይዘውት ይቆዩ። በምኞት የሚኖሩ ሁሉ፣ በሕይወታቸው ሳሉ ሞተዋል፤ በመንፈሳዊ ሞት ሞተዋል፣ በበደሎችና በኃጢአት ሞተዋል። ወዮ! በስም ክርስቲያኖች መካከል እስከ ሕይወታቸው መጨረሻ ጊዜ ድረስ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ስንት ብዙ ቁጥር ያላቸው ናቸው! ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት ድሆች የሆኑ ዘመዶቻቸውን የማይደግፉ ከሆነ፣ እነርሱም በተግባር እምነትን ይክዳሉ። ለቤተሰቦቻቸው ቀለብ መሆን ያለበትን ገንዘብ ለምኞታቸውና ለደስታቸው የሚያውሉ ከሆነ፣ እምነትን ክደዋልና ከማያምኑትም የባሰ ናቸው። የወንጌል ተናጋሪዎች ለማንኛውም የተበላሸ መርህ ወይም ምግባር እጅ ከሰጡ፣ እነርሱም የጸጋን ትምህርቶች አምነናል ብለው ከማይመሰክሩት ሰዎች የባሰ ናቸው።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6