1ኛ ቆሮንቶስ 5

AMHNIVአማርኛ13 ጥቅሶች2:41 አዳምጥ
አዳምጥ 2:41 · መደበኛ · አስደናቂ በBiblight ይክፈቱ

1በመካከላችሁ የዝሙት ርኵሰት እንዳለ በርግጥ ይወራል፤ እንዲህ ያለው ርኵሰት በአረማውያን ዘንድ እንኳ ታይቶ የማይታወቅ ነው፤ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው አለና።

2ደግሞም ታብያችኋል! ይልቅስ ሐዘን ተሰምቶአችሁ፣ ይህን ድርጊት የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ልታስወግዱት አይገባምን?

3ምንም እንኳ እኔ በአካል አብሬያችሁ ባልሆንም፣ በመንፈስ ግን ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ልክ አብሬያችሁ እንዳለሁ ሆኜ፣ ይህን ባደረገው ሰው ላይ አሁኑኑ ፈርጄበታለሁ።

4በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በመንፈስ ከእናንተ ጋር ስለ ምሆን፣ በጌታችን በኢየሱስ ስምና በመካከላችሁ በሚገኘው በጌታችን በኢየሱስ ኀይል፣

5ሥጋው ጠፍቶ መንፈሱ በጌታ ቀን ትድን ዘንድ፣ እንደዚህ ዐይነቱ ለሰይጣን ይሰጥ።

6መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ብዙውን ሊጥ እንደሚያቦካው አታውቁምን?

7አሁን ያለ እርሾ እንደሆናችሁ ሁሉ አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ የፋሲካ በጋችን የሆነው ክርስቶስ ተሠውቶአልና።

8ስለዚህ በዓሉን ግፍና ክፋት በሞላበት እርሾ፣ በአሮጌ እርሾ ሳይሆን፣ እርሾ በሌለበት ቂጣ በቅንነትና በእውነት እናክብር።

9ከሴሰኞች ጋር እንዳትተባበሩ በመልእክቴ ጽፌላችሁ ነበር፤

10እንዲህም ስል በጠቅላላው ከዚህ ዓለም ሴሰኞች ወይም ስግብግቦችና ቀማኞች፣ ወይም ከጣዖት አምላኪዎች ጋር አትተባበሩ ለማለት አይደለም፤ እንደዚያማ ቢሆን ከዚህ ዓለም ጨርሶ መለየት ያስፈልጋችሁ ነበር።

11ነገር ግን አሁን የጻፍሁላችሁ፣ “ወንድም ነኝ” እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋር እንዳትተባበሩ ነው፤ ከእንደዚህ ዐይነቱ ሰው ጋር ምግብ እንኳ አትብሉ።

12ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ባሉት ሰዎች ላይ ለመፍረድ እኔን ምን አገባኝ? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?

13ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ባሉት ላይ የሚፈርድ ግን እግዚአብሔር ነው፤ እንግዲህ፣ “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱት።”

ማብራሪያ

5:1-8 ሐዋርያው በቆሮንቶሳውያን ችላ የተባለን አስከፊ ጥፋት አስተውሏል። የቡድን መንፈስና የክርስቲያናዊ ነጻነት የተሳሳተ ጽንሰ ሐሳብ በደለኛውን ከውግዘት ያዳኑት ይመስላል። ወንጀሎች በወንጌል አማኞች ዘንድ አንዳንድ ጊዜ መፈጸማቸው፣ እንዲያውም አሕዛብ እንኳ የሚያፍሩባቸው መሆናቸው፣ በእውነትም እጅግ ያሳዝናል። መንፈሳዊ ኩራትና ሐሰተኛ ትምህርቶች እንደነዚህ ያሉ ውርደቶችን ለማምጣትና ለማስፋፋት ያግዛሉ።

የኃጢአት ውጤቶች ምንኛ አስከፊ ናቸው! ክርስቶስ በሌለበት ቦታ ሰይጣን ይገዛል። አንድ ሰው በክርስቶስ በማይሆንበት ጊዜ፣ እርሱ በሰይጣን መንግሥት ሥርና በሥልጣኑ ሥር ይሆናል።

ሙሉ ማብራሪያውን ያንብቡ ድምፅ፣ ሙሉ ማብራሪያ እና ከመስመር ውጭ ንባብ

ትርጉሞች8 · 6

AMHEVG በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና። አማርኛ ENGNIV It is actually reported that there is sexual immorality among you, and of a kind that does not occur even among pagans:… English BCV ኣብ ኣህዛብ እኳ ተገይሩ ዘይፈልጥ ምንዝርና፥ ኣብ ማእኸልኩም ከም ዘሎ፥ ብፍላይ ካባኻትኩም፥ ሰበይቲ ኣቦኡ ዘእተወ ኸም ዘሎ፥ ይውረየኩም ኣሎ። ትግርኛ GAZBIB Amma immoo halalummaan warra saba Waaqayyoo hin ta'in keessatti illee salphaatti hin ilaalamne, isin gidduu akka jiru d… Afaan Oromoo BCV GIZ እስመ ይሰማዕ በላዕሌክሙ ዝሙት ወዝሙትኒ ዘከመዝ ዘኢይገብርዎ አረሚ ጥቀ ሀሎአ ዘአውሰበ ብእሲተ አቡሁ። giz GAZGAZ Amma immoo halalummaan warra saba Waaqayyoo hin ta'in keessatti illee salphaatti hin ilaalamne, isin gidduu akka jiru d… Afaan Oromoo BCV aksum ኣብ ኣህዛብ እኳ ተገይሩ ዘይፈልጥ ምንዝርና፥ ኣብ ማእኸልኩም ከም ዘሎ፥ ብፍላይ ካባኻትኩም፥ ሰበይቲ ኣቦኡ ዘእተወ ኸም ዘሎ፥ ይውረየኩም ኣሎ። ትግርኛ SWAHSUV Yakini habari imeenea ya kuwa kwenu kuna zinaa, na zinaa ya namna isiyokuwako hata katika Mataifa, kwamba mtu awe na mk… Kiswahili